ፌደራል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ሕጋዊ አሰራሩን ባልጠበቀ ሁኔታ
ለአሰልጣኞች አበል 19. 2 ሚ. ብር ክፍያ እንደፈጸመ ተገለጸ
ፌደራል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ሕጋዊ አሰራሩን ባልጠበቀ ሁኔታ ለአሰልጣኞች አበል 19 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ክፍያ እንደፈጸመ ተገልጿል። በተጨማሪም፣ ገንዘብ ሚኒስቴር በማያውቃቸው ሁለት የባንክ ሂሳቦች ከ86 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አድርጎ መገኘቱ ተነግሯል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ ረቡዕ ታሕሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. በፌደራል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ የስራ አፈጻጸም ላይ ባካሄደው የኦዲት ሪፖርት ግምገማ፤ ገንዘብ ሚኒስቴር በማያውቃቸው ሁለት የባንክ ሂሳቦች ከ86 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አድርጎ መገኘቱ ተጠቅሷል።
ከዚህም ባሻገር የዩኒቨርስቲው አስተዳደር በበጀት ዓመቱ ሕጋዊ አሰራሩን ባልጠበቀ ሁኔታ ለአሰልጣኞች አበል 19 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ክፍያ ፈጽሟል ተብሏል።
በተጨማሪም፣ በሚመለከተው አካል ሳይጸድቅ፣ ዩኒቨርስቲው ቀድሞ የነበረውን የቀለብ ተመን 1 ሺሕ 500 ብር በማድረግ፣ ከመመሪያ ውጪ ለተማሪዎች ቀለብ የሚሆን የምግብ ግብዓት በድምሩ 20 ሚሊዮን 330 ሺህ 91 ብር ከ69 ሳንቲም ግዢ ያለአግባብ መፈጸሙን የኦዲት ግኝት ሪፖርቱ አመላክቷል። ሪፖርቱ ሲቀጥልም፣ ከተለያዩ ድርጅቶች ከመመሪያ ውጪ ያለውድድር 38 ሚሊዮን 207 ሺሕ 419 ከ58 ሳንቲም የቀጥታ ግዢ ማከናወኑና ክፍያ መፈጸሙን ጠቅሷል።
የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት አቶ መስፍን አበበ ለቋሚ ኮሚቴው አባላት በሰጡት ማብራሪያ፤ የመጀመሪያው የባንክ ሂሳብ ከቀድሞ ጊዜ ጀምሮ ሲንቀሳቀስ የነበረ መሆኑን አስታውቀዋል። ይኸው የባንክ ሂሳብ የዩኒቨርስቲው በጀት በፊደራል ፖሊስ ስር በነበረበት ወቅት ስለመከፈቱ አውስተው፣ ዩኒቨርስቲው በበጀት ራሱን ሲችል ሌሎች የባንክ ሂሳቦችን እንደከፈተ ገልጸዋል።
“የባንክ ሂሳቦቹን ስንከፍት ገንዘብ ሚኒስቴርን አለማስፈቀዳችን ስህተት ነው። ነገር ግን ሆን ብለን አካውንቶቹንና በዚያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ገንዘቦችን ለመደበቅ አልሰራንም።” ያሉት አቶ መስፍን፤ የመጀመሪያው የባንክ ሂሳብ እንዲዘጋ ሲደረግ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር ለሁለተኛው የባንክ ሂሳብ ፈቃድ እንዲሰጥ ጥያቄ መቅረቡንም አስረድተዋል።
ከአሰልጣኞች አበል ጋር በተገናኘ ምላሽ የሰጡት አቶ መስፍን “በ2015 ዓ.ም. ገበያ ላይ ባለው የዋጋ ንረት ሳቢያ፣ ሙሉ በሙሉ የሰራዊታችንን ባለሞያዎች ማሰራት የማንችልበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር።” ብለዋል። በዚህም ሌሎች የስፖርት ስልጠና ተቋሞች እንዴት ሰራተኞቻቸውን እንደሚያስተዳድሩ ጥናት ተደርጎ፣ በስራ አመራሩ ተገምግሞ፣ በዩኒቨርስቲው ቦርድ ውሳኔ እንደተሰጠበት ተናግረዋል።
“ነገር ግን ቦርዱ የሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ መሆኑን የተረዳንበት መንገድ ስሕተት መሆኑን ከፌደራል ዋና ኦዲተር የመጡ ባለሞያዎች ሲያስረዱ ለመረዳት ችለናል። የአሰልጣኞቹ የደመወዝ ክፍያቸው የወረደ ነበር።” ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ለቋሚ ኮሚቴው አባላት ገልጸዋል። ተጨማሪ ክፍያውን ለማስፈቀድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ደብዳቤዎች መላካቸውን ያነሱ ሲሆን፣ ነገር ግን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ገብተው ማስረዳት እንዳልቻሉ ነው የጠቀሱት።
የተጨማሪ ክፍያውን ሃሳብ የገንዘብ ሚኒስቴርና የኦዲት ባለሞያዎች ሃሳቡን በአወንታ እንደተቀበሉት፣ ነገር ግን የአሰራር ስሕተት በመፈጠሩ እርሳቸው በገንዘብ ሚኒስቴር የገንዘብ መቀጮ እንደተጣለባቸው አመልክተዋል፣ ፕሬዝዳንቱ በማብራሪያቸው።
“እንደተቋሙ መሪነቴ ለሚወሰድብኝ እርምጃ እኔ ዝግጁ ነኝ” ያሉ ሲሆን፣ አሁንም ግን የአሰልጣኖቹ የተጨማሪ ክፍያ ጉዳይ ዕልባት እንደሚሻ አጽንዖት ሰጥተው አስገንዝበዋል።
ስለተማሪዎች የቀለብ ተመን ማብራሪያ የሰጡት አቶ መስፍን፣ ከዚህ ቀደም በመንግስት ስንዴ፣ ስኳርና ዘይት የድጎማ ዋጋ ተደርጎ ለዩኒቨርስቲው ይቀርብ እንደነበር በማውሳት፣ ስንዴ በኩንታል በ780 ብር፣ ዘይት በሊትር 15 ብር እና ስኳር በኪሎ እስከ 22 ብር ሲቀርብ መቆየቱን አመልክተዋል። ይሁንና ኦዲቱ በተሰራበት ወቅት የስኳር ዋጋ 56 የነበር ቢሆንም፣ አሁን 105 ብር መድረሱን፤ ስንዴ በ2015 ወደ 3 ሺሕ ብር ገደማ እንደነበር፣ አሁን ግን 8 ሺሕ ብር መሆኑን ተናግረዋል።
ተቋማቸው አሁን ባለው የገበያ ተመን መሰረት ከቀድሞው ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጉንና የምግብ ዝርዝር (ሜኑ) አውጥቶ ለገንዘብ ሚኒስቴር እና ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም፣ መልስ እንዳልተሰጠው ገልጸዋል። “በገበያ ዋጋ ግዢ እየተደረገ ምገባ እየቀጠለ ነው” ያሉት አቶ መስፍን፣ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ምላሽ ሊሰጥ ካልተቻለ ግን ስልጠናው ቆሞ ተማሪዎች እንዲበተኑ “ሊደረግ ይችላል” በማለት አሳስበዋል።