በዋሺንግተን ዲሲ 60 ሰዎች የጫነ አውሮፕላን አየር ላይ ከጦር ሄሊኮፕተር ጋር ተጋጨ
አሜሪካን ኤርላይንስ የተሰኘው አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን አየር ላይ ሳለ ከሄሊኮፕተር ጋር መጋጨቱን የፌዴራል አቪየሽን አስተዳደር አስታወቀ።
አውሮፕላኑ 60 መንገደኞች እና አራት የበረራ ሠራተኞች ጭኖ እንደነበር የታወቀ ሲሆን ሄሊኮፕተሩ ደግሞ ሶስት የአሜሪካ ወታደሮችን ጭኖ እንደነበር ተነግሯል።
የአውሮፕላን አደጋው የደረሰው ፖቶማክ የተባለ ወንዝ አቅራቢያ መሆኑን የዲሲ እሳት አደጋ መሥሪያ ቤት ገልጿል።