"ሰላማችንን በማጽናት ልማታችንን እናስቀጥላለን" የዱርቤቴ ከተማ ነዋሪዎች
በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ዱርቤቴ ከተማ አሥተዳደር የተገነቡ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ተጠናቅቀው ተመርቀዋል።
ከምረቃ ሥነ ሥርዓቱ በተጨማሪ አመራሩ፣ ኅብረተሰቡ እና በአካባቢው የሚገኙ የመከላከያ አመራሮች በልማት እና በሰላም ጉዳዮች ላይ ከሕዝብ ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ የተሳተፉት የከተማዋ ነዋሪዎች በሰላም መስፈን እና በልማት ቀጣይነት ላይ አስተያየት ሰጥተዋል።
የመልካም አሥተዳደር ችግር ሲፈጠር ሕዝብ ለጦርነት ይዳረጋልና ያጋጠመን ችግር እንዲቃለል አመራሩ ጠንክሮ መሥራት ያስፈልጋል ተብሏል።
የመከላከያ ሰራዊት ባልተመቸ ሁኔታ ለሕዝብ ሰላም ሲል መስዋዕትነት እየከፈለ ነው ያሉት ነዋሪዎች ሁላችንም ለሰላም ብንሠራ ይህ ሁሉ ችግር አይደርስብንም ነበር፤ አሁንም ለሰላም ትኩረት እንስጥ ብለዋል።
የሰሜን ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሰፋ ጥላሁን ለተመረቁት እና በአዲስ ግንባታቸው ለተጀመሩ የልማት ሥራዎች መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተው መከላከያ ሰራዊት ነው ብለዋል። ምስጋናም ይገባዋል ነው ያሉት።
የልማት ሥራዎቻችን እንዳይቆሙ እንሠራለን። በዞኑ ለዱርቤቴ - ቁንዝላ - ሻውራ 260 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ፤ ለአዴት - ሰከላ 62 ኪሎ ሜትር መንገድ እና ለባሕር ዳር - ዘጌ መንገድ ሥራዎች በርካታ ቢሊዮን ብር መመደቡን ገልጸዋል። እነዚህ መንገዶች ተጠናቅቀው ለኅብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ሰላም ያስፈልጋል ነው ያሉት።
ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የሰላምን ጠቀሜታ ተረድቶ ለሰላም ጠንክሮ መሥራት ይገባልም ብለዋል።