በፖሊስ ተቋም ለረዥም አገልግሎት ዘመናቸውን አጠናቀው በጡረታ ለወጡ አመራሮች የምስጋና መርሐ ግብር ተዘጋጅቶላቸዋል።
በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ስር ከወረዳ እስከ ዞን መምሪያ በተለያዩ አመራርነት ያገለገሉ የፖሊስ መኮንኖች የጦረታ ጊዚያቸውን አጠናቀው በመውጣታቸው የብሔረሰብ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ለነበራቸው አርዓያነትና አገልግሎት የምስጋና ፕሮግራም ተዘጋጅቶላቸዋል።
የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አሰተዳዳሪ አቶ ኃይሉ ግርማይ ብሔረሰብ ዞኑ አሁን ያለው አንፃራዊ ሰላም የተገኘው የፖሊስ ተቋሙ እና የፀጥታ መዋቅሩ በከፈለው መስዋዕትነትና በሰራው መልካም አስተዋፅኦ መሆኑን ገልፀው በጡረታ የተገለሉት መኮንኖችም ለአመታትም ሆነ በአሁኑ ሰዓት ለዞኑ ሁለንተናዊ ሰላም ለነበራቸው አስተዋፅኦ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
የብሔረሰብ አስ/ር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ደጀን ወዳጅ በበኩላቸው ከልጅነት እስከ ዕውቀት ለረጅም ጊዜ በፖሊስ ተቋማችን አገልግለው በክብር በጡረታ የወጡ አመራሮቻችን በነበራቸው ቆይታ ለሰሩት መልካም አርዓያነት የምስጋና ፕሮግራም የተዘጋጀው ከወታደርነት እሰከ ኮማንደርነትና ከተመሪነት እስከ አመራርነት በነበረው ሂደት የሚገጥማቸውን ፈተናዎች አልፈው በክብር ለጡረታ መድረስ ትልቅ መታደል ስለሆነም ከነዚህ አመራሮች ትግስትን ፣ህዝባዊነትን፣ ሚዛናዊነትን መውሰድ ይገባናል ብለዋል።