ማስታወቂያ!!! ለአድማ መከላከል ፖሊስ
================
የአማራ ክልል ፖሊስ በበጀት ዓመቱ ተቋሙን በሰዉ ኃይል አቅም ለማጠናከር አቅዶ እየሰራ ይገኛል ። የሰለጠነ የሰዉ ኃይል የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነዉ። ስለሆነም ከተያዘዉ የሰዉ ኃብት ልማት እቅድ አዲስ የፖሊስ አባላትን ማሰልጠን በመሆኑ በርካታ ወጣቶችን በመመልመል ወደ ተቋሙ መቀላቀል ይፈልጋል ።
በመሆኑም ወጣቶች የተከፈተዉን የስራ ዕድል በመጠቀም ህዝብን የማገልገል ክብር መገለጫ ወደሆነው የፖሊስነት ሙያ መስፈርቱን የምታሟሉ በየአቅራቢያችሁ በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እያሳሰብን የተቀመጡ መስፈርቶች በተመለከተ፦
በክልሉ ፖሊስ መተዳደሪያ ደንብ ቁጥር 175/2010 የተቀመጡ የምልመላ መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆኖ፦
----------------------------
የምልመላ መስፈርት/መመዘኛ
----------------------------
1. ዜግነቱ ኢትዮጲያዊ የሆነ/ች
2. ለፌዴራሉና ለክልሉ ሕገ-መንግስንቱና ሕገ-መንግስቱን መሰረት አድርገው ለወጡ ሕጎች ተገዥና ታማኝ የሆነ/ች፣
3. ቢያንስ 6ኛ ክፍልና ከዚያ በላይ ያጠናቀቀ/ች
4. ከማናቸውም ደባል ሱሶች የፀዳ/ች፣ መልካም ስነ ምግባር ያለው/ት
5. ከሚኖርበት ቀበሌ አስተዳደር የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
6. ለፖሊስነት የሚያበቃ ሙሉ ጤናማ መሆኑ/ኗ በህክምና የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ወይም የምትችል፣
7.ዕድሜው/ዋ ከ18 እስከ 28 ዓመት፣
8. ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ች፣
9. ቁመት ለወንድ 1.65 ሜትር በላይ የሆነ፣ ለሴት 1.60 ሜትር በላይ የሆነች፣
10. ክብደት ለወንድ 50-70 ኪ.ግ፤ ለሴት 45-65 ኪ.ግ
11. የ7 ዓመት የሥራ ውል ግዴታ በመግባት ሥልጠናው ሲጠናቀቅ በየትኛውም የክልሉ አካባቢ ተመድቦ/ድባ ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ/ች፣
12. ከአሁን በፊት በወንጀል ተከሶ/ተከሳ ያልተቀጣ/ች ወይም የወንጀል ክስ የሌለበት ወይም የሌለባት፣
13. ከአሁን በፊት በማንኛውም የፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት ተቋም ሥልጠና ያልወሰደ/ሰደች፤ አባል ሆኖ/ና የማያወቅ ወይም የማታውቅ እንዲሁም የትኛውም የትጥቅ ትግል ተሳትፎ የሌለው/ላት
14. ያላገባ እና ያልወለደ ወይም ያላገባች እና ያልወለደች፣
15. ደሞዝ 5,283 የቀለብ አበል 2200 ቀድምሩ 7,483 ተቋሙ ነፃ ህክምና ያመቻቻል።
ማሳሰቢያ፦
ማንኛውም ዕጩ ተመልማይ በምዝገባ ወቅት ከላይ ከተገለፁት መመዘኛዎች በተጨማሪ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
1. የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና የማይመለስ 1 ፎቶኮፒ፣
2. ከ2 ዓመት በላይ ነዋርነትን የሚያመለክት የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ ካርድ ይዞ መቅረብና መመዝገብ ይጠበቅበታል፣
3. መዝገባው በሥራ ቀንና በሥራ ሰዓት በክልሉ በሚገኙ የወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤትና ጣቢያዎች ይሆናል፡፡