አሽሙር መሆኑ ነው ...? ከፌስቡክ መንደር ነው ያገኛሁት። እና...መልስ እንስጠው አይደል? እናንተ ካላችሁማ ሐተታ ነገር እንወርውር:-
1- ከመሰረቱ ኢየሱስ ማንንም ባሪያዎቼ ብሎ የመጥራት ስልጣኑ የለውም። ምክንያቱም እርሱ ራሱ "ባሪያ" ስለሆነ። (ኢሳይያስ 42፥1 | ሱራ 19፥30)። ስለዚህ ባሪያ የሆነ አካል ሌላውን ወንድሜ ወይም እህቴ ብሎ እንጂ "ባሪያዬ" ብሎ በፍጹም መጥራት አይችልም። ለዚያም ነው ኢየሱስ በወንጌል ላይ ምዕመናንን ወንድሞቼ ብሎ የሚጠራቸው (ማቴዎስ 12፥50)። ስለዚህ "ባሪያዬ" ብሎ እንዲጠራህ አትጠብቅ !
2- ለአምላክ ባሪያ መሆንና ባሪያ ተብሎ መጠራት ልዕቅናና ክብር እንጂ በፍጹም ውርደት አይደለም። ውርደቱ ለፍጡር ባሪያ መሆን ነው። ለዓለማቱ ፈጣሪ ባሪያ መሆን ምነኛ መታደል ነው ! ምናልባት ግን ባሪያ መባሉ ውርደት ከመሰለህ:-
▣ ኢየሱስ የእ/ር ባሪያ ተብሏል። ❲ኢሳያስ 42፥1❳
▣ ገብርኤል የእ/ር ባሪያ ተብሏል። ❲ሉቃስ 1፥38❳
▣ ሙሴ የእ/ር ባሪያ ተብሏል። ❲ዘኁልቁ 12፥7❳
▣ ኢዮብ የእ/ር ባሪያ ተብሏል። ❲ኢዮብ 1፥8❳
▣ ዳዊት የእ/ር ባሪያ ተብሏል። ❲1ዜና 17፥7❳
▣ ዮሐንስ የእ/ር ባሪያ ተብሏል። ❲ራዕይ 19፥10❳
▣ ጳውሎስ የእ/ር ባሪያ ተብሏል። ❲ቲቶ 1፥1-2❳
አጠቃላይ ምዕመኑስ ቢሆን "ባሪያ" አይደል እንዴ ?
“ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ፤ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ፥ አመስግኑት፥”
— መዝሙር 135፥1
3- ባይሆን ኢየሱስ «በጎቼ» ብሎ ስለሆነ የሚጠራችሁ በግልጽ በግ መሆናችሁን አምናችሁ ተቀበሉ። ማለቴ በግ ነን" በሉ! ምን ችግር አለው ?!
በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤”— ዮሐንስ 10፥27
ወንድም ሳላህ
https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg