Фильтр публикаций


ሶላት ሰግደን ስናሰላምት ከጎኔ ያለው ልጅ ክርኑ ላይ ትልቅ መስቀልና Jesus is God የሚል ተነቅሶ አየሁ። ነገሩ ገባኝና ❝በቅርቡ ሰልመህ ይመስላል❞ አልኩት። ❝አወ❞ አለኝ። ከዚያ ትንሽ አበረታታሁትና ንቅሳቱን ለማጥፋት ብሎ ራሱን እንዳይጎዳ መክሬው ተለያየን።

ከዚያ የአላህ ስራ ደነቀኝ። ይህ ልጅ መስቀልና ኢየሱስን የተነቀሰው በልቡ ያለውን እምነት በገፁም ላይ ለማጥበቅ ነው። ሲነቀስ ክርስትናን እለቃለሁ ብሎ ፈፅሞ አያስብም። ነገርግን ቀልብን እንዳሻው ገለባባጩ አላህ ክህደቱን ቆዳው ላይ ቢነቀሰውም ልብን አንፅቶ ኢስላምን ወፈቀው። ሙሽሪኮች እስከፍፄያቸው ሊክዱት ቆርጠው ግንባራቸው ላይ መስቀል ቢነቀሱ እንኳን አላህ በደግነቱ ያሰልማቸዋል። ይህ ደግነትና ችሎታ ከአላህ በቀር ከማን ይገኛል?

(ምስል ከፌስቡክ)

https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg




ዓሊሟ በዱቤ የሚታከምባት ኡማ!

▪️ ለሸይኽ ዐብዱለጢፍ እስካሁን የተሰበሰበው ብር 499,000 (አራት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሽ) ብር ነው። አጠቃላይ የሚፈለገው $8500 (ስምንት ሽ አምስት መቶ የአሜሪካን ዶላር ) ነው። ይህ ማለት 1,037,000 (አንድ ሚሊዮን ሰላሳ ሰባት ሽህ) የኢትዮጲያ ብር ገደማ ነው። ከዚህ ላይ ግማሹን እንኳን መሰብሰብ አልተቻለም!!

▪️ ሸይኻችን ከእስር ቤት ሲወጡ በስጦታ የተበረከተላቸው መኪና ይሸጥ ቢሉም እያሰባሰቡ ያሉ ሽማግሌዎች በጭራሽ እኛ ሙስሊሙን ይዘን አሰባስበን እንከፍላለን እንጅ መኪናው አይሸጥም በማለት የህዝቡን ትብብር እየጠበቁ ነው!

▪️ ጉዳዩ እንዲህ ነው ፦ ህመሙ ወደ ካንሰር የመለወጥ እድል የነበረው እጢ በመሆኑ እናሳክማችሁ ብለው ወደ ቱርክ የወሰዷቸው ወንድምና እህቶች ከህዝቡ ሰብስበን እንከፍላለን በሚል መተማመን ከሰዎች በብድር አንስተው ነበር የከፈሉት።

▪️ መጀመሪያ $4000 የተገመተ ህክምና ኋላ ላይ $7500 ተጨማሪ ተጠየቀበት። ይህ ሁሉ ሲሆን ሸይኻችን አያውቁም ነበር። ከዚያ የተወሰኑ ቅርብ ሰዎች ጉዳዩን ሲነግሯቸው ነበር «መኪናዬ ይሸጥ» የሚል ሀሳብ ያመጡት ።

ይህም ጠቅላላ ህክምናው $11,500 ዶላር ሲሆን $2500ው በወንድሞች ስለተከፈለ ለህዝብ የተጠየቀው $8500ው ብቻ ነው። የአንድ መርፌ ዋጋ $300 (36,600 ብር ) ሆኖ ህክምናው እንደቀጠለ ነው። መርፌውም የሚቆም ሳይሆን በየ3ወሩ የሚቀጥል ነው።

▪️ ወደርሳቸው አካውንት ገቢ እንዳይደረግ የተደረገውም በዚሁ ምክንያት ብቻ ነው። ከአካውንትህ አውጣና ዱቤ ክፈል እንዴት ይባላል? ለሸይኽ አይደለም ለተርታ ሰውስ ነውር አይደለም? ስለሆነም በኮሚቴ አካውንት እንዲሰበሰብ ተወሰነ።

▪️ አሰባሳቢ ኮሚቴዎቹ በእምነታቸው ድፍን የሰንበቴ ከተማ ነዋሪ የሚመስክርላቸው ዓሊሞችና ሽማግሌዎች እንዲሁም የሸይኹ የቅርብ ጓደኞች ናቸው።

ስለሆነም ሙስሊሙ ኡማ ይህንን ተገንዝቦ «ሀብታሞች ገቢ ያደርጋሉ» ብለን ሳንዘናጋ ትንሽም ብትሆን ሁሉም የራሱን ገቢ እያደረገ ሸይኻችንን እናሳክም!

የከሸፍን ትውልዶች ሆነን እንጅ ወላሂ በዚህ መልክ ለሸይኻችን ስፅፍ ክብራቸውን ዝቅ ያደረግኩ እየመሰለኝ ነው!

የንግድ ባንክ አካውንት ፦
1000392652788
የአካውንት ስም ፦
YEJILE TIMUGA W/COMMUNITY SUPPORT
(የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮሚዩኒቲ ሰፖርት)

አሰባሳቢ ኮሚቴዎች ፦
1) ሸኽ ጡሃ ሸኽ መሀመድ
2) ሸኽ ሁሴን ሀሰን ሱሩር
3) ሸኽ አህመድ አሊ ሃሰን

ሼር ማድረግም ትብብር መሆኑ አይዘንጋ!


የሙሥሊሙን ሙሥሊማት እንኳን ለ1445ኛው ዓ.ሂ የዒድ አል-ፊጥር በዓል አሏህ በሰላም አደረሳችሁ..!

ዒድኩም ሙባረክ .!
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال....


#3ልጆቼን_ሳልሞት_አገናኙኝ
(ሼር ማድረግ ሶደቃ ነው ወገን። ወገኑን የሚረዳ የአላህ እርዳታ ከሱ ጋር ነው።)
~
ወ/ሮ ሐሊማ ሰይድ እባላለሁ ሰሜን ወሎ ወልድያ ከተማ ነው የምኖረው። ከባለቤቴ ሙሀመድ ሁሴን (አባናኖ) ጋር ተጋብተን አ. አ. እንንኖር ነበር ከዛም አረብ ሀገር በመሄድ #ሁለቱን_ልጆቻችንን ወለድን። #ሶስተኛዋ አ. አ. ተወለደች።
ልጆቼ
1ኛ አብዱልመጅድ ሙሀመድ ሁሴን
2ኛ ፎዝያ ሙሀመድ ሁሴን
3ኛ መሬም ሙሀመድ ሁሴን

አ.አ. አየር ጤና አካባቢ እንኖር የነበረ ሲሆን ባለመግባባትችን እና በኑሮው መክበድ ምክንያት በ1994 ተመልሼ ወደ አረብ አገር ስሄድ ልጆቼን አክስታቸው ጋ ሰጥቼ ብሄድም አባታቸው ከአክስታቸው ቀምቶ ወሰዳቸው።

አረብ ሀገር እያለሁ ለልጆቼ የምችለውን እያደረኩ የነበረ ቢሆንም ለምን ጥለሽ ሄድሽ በሚል ልጆቼን ከ1997 ጀምሮ ሊያገናኘኝ አልቻለም።

ትልቁ ልጄ አብዱልመጅድ በ1997 አ.አ ዳንዲቦሩ ትምርት ቤት እየተማረ ትምርት ቤቱ እየሄድኩ አገኘው የነበረ ቢሆንም በሌላ ጊዜ ስሄድ ትምርት ቤቱን ለቋል ተብሎ ላገኘው አልቻልኩም።

ለማግኘት ብዙ ግዜ አ.አ ተመላለስኩ እንኖርበት የነበረው ሰፈር ጠየቅኩ ላገኛቸው አልቻልኩም። በእናትነት አንጀት ይህን ሁሉ አመት እነሱን እያሰብኩ አለሁ አባታቸው አልፎ አልፎ ቢደውልም ልጆቹን ግን እንዳገኛቸው አይፈቅድም።

ሲደውል ልጆቹ ትልቁ ልጄ አብዱልመጅድ ጂማ ዩንቨርሲቲ መካከለኛዋ ፎዝያ ጎንደር ዩንቨርሲቲ እንደተማሩ ነግሮኛል።
ልጆቼን ከ 20 አመት በላይ ሳላገኛቸው እዬኖርኩ ነው እባካችሁ ይህን የምታዩ ሁሉ ሳልሞት ልጆቼን እንዳገኛቸው አግዙኝ።

ስልክ
0921568570
0910633833


Репост из: religionandphylosophy
ሳዑዲ አረቢያ ከሁሉም ቦታ እና ወደ ኢትዮ እናደርሳለን  ይዘዙ ።

  0 54 798 4638 📞

ቴሌግራም https://t.me/Sarah_online_shopping
https://t.me/Sarah_online_shopping


አሽሙር መሆኑ ነው ...? ከፌስቡክ መንደር ነው ያገኛሁት። እና...መልስ እንስጠው አይደል? እናንተ ካላችሁማ ሐተታ ነገር እንወርውር:-

1- ከመሰረቱ ኢየሱስ ማንንም ባሪያዎቼ ብሎ የመጥራት ስልጣኑ የለውም። ምክንያቱም እርሱ ራሱ "ባሪያ" ስለሆነ። (ኢሳይያስ 42፥1 | ሱራ 19፥30)። ስለዚህ ባሪያ የሆነ አካል ሌላውን ወንድሜ ወይም እህቴ ብሎ እንጂ "ባሪያዬ" ብሎ በፍጹም መጥራት አይችልም። ለዚያም ነው ኢየሱስ በወንጌል ላይ ምዕመናንን ወንድሞቼ ብሎ የሚጠራቸው (ማቴዎስ 12፥50)። ስለዚህ "ባሪያዬ" ብሎ እንዲጠራህ አትጠብቅ !

2- ለአምላክ ባሪያ መሆንና ባሪያ ተብሎ መጠራት ልዕቅናና ክብር እንጂ በፍጹም ውርደት አይደለም። ውርደቱ ለፍጡር ባሪያ መሆን ነው። ለዓለማቱ ፈጣሪ ባሪያ መሆን ምነኛ መታደል ነው ! ምናልባት ግን ባሪያ መባሉ ውርደት ከመሰለህ:-
▣ ኢየሱስ የእ/ር ባሪያ ተብሏል። ❲ኢሳያስ 42፥1❳
▣ ገብርኤል የእ/ር ባሪያ ተብሏል። ❲ሉቃስ 1፥38❳
▣ ሙሴ የእ/ር ባሪያ ተብሏል። ❲ዘኁልቁ 12፥7❳
▣ ኢዮብ የእ/ር ባሪያ ተብሏል። ❲ኢዮብ 1፥8❳
▣ ዳዊት የእ/ር ባሪያ ተብሏል። ❲1ዜና 17፥7❳
▣ ዮሐንስ የእ/ር ባሪያ ተብሏል። ❲ራዕይ 19፥10❳
▣ ጳውሎስ የእ/ር ባሪያ ተብሏል። ❲ቲቶ 1፥1-2❳

አጠቃላይ ምዕመኑስ ቢሆን "ባሪያ" አይደል እንዴ ?

“ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ፤ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ፥ አመስግኑት፥”
  — መዝሙር 135፥1

3- ባይሆን ኢየሱስ «በጎቼ» ብሎ ስለሆነ የሚጠራችሁ በግልጽ በግ መሆናችሁን አምናችሁ ተቀበሉ። ማለቴ በግ ነን" በሉ! ምን ችግር አለው ?!

በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤”— ዮሐንስ 10፥27

ወንድም ሳላህ
https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
◾️ ኢየሱስ ንጹህ መባሉ ፈጣሪ ያደርገዋልን?

🎙 ኡስታዝ አቡ ሐይደር

https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg


አሏህ የማይምረው ወንጀል ቢኖር ሽርክን ነው
። የእሬቻ በዓል ሽርክ ነውና ከማክበር በአሏህ እንጠበቃለን ። እኛ ሙሥሊሞች ነን ።


https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg


እደለኛ ሰው ማለት.....!

በሌሊቱ ወቅት የሱረቱል በቀራን የመጨረሻ ሁለት አንቀጾች ያነበበ ሰው በአላህ ፍቃድ ሌሊቱን ከመጥፎ ነገር ሁሉ እንደሚጠበቅ ተረድቶ ሲያበቃ አንቀፆቹን አዘወትሮ ያነበባቸው ሰው ነው።

እደለኛ ሰው ማለት.....!

ፈርድ የሆኑ ስላቶችን ከሰገደ በኋላ አያተል ኩርሲይን ካነበበ ጀነትን መግባት ሞት እንጂ ምንም እንደ ማይከለክለው ተረድቶ አዘወትሮ አያተል ኩርሲይን ያነበበ ሰው ነው።

እደለኛ ሰው ማለት.....!

ከመተኛቱ በፊት አያተል ኩርሲይን ያነበበ ሰው ለሊቱን ሙሉ እስኪያነጋ ከአላህ የተመደበ ጠባቂ እንደሚጠብቀውና ሸይጣንም እንደማይቀርበው አውቆ ከመተኛቱ በፊት አያተል ኩርሲይን አዘወትሮ ያነበበ ሰው ነው።

እደለኛ ሰው ማለት.....!

ሱረቱል ኢኽላስን ሶስት ጊዜ ማንበብ ሙሉ ቁርዓንን ከማኽተም ጋር እንደሚስተካከል ተረድቶ ይህችን ሱራ አብዝቶ ያነበበ ሰው ነው።

እደለኛ ሰው ማለት.....!

ለሴትና ለወንድ አማኞች ሁሉ ዱዓዕ ያደረገ ሰው በአያንዳንዱ አማኝ አላህ ዘንድ አጅር እንደሚመዘገብለት ተረድቶ ለሙዕሚኖች ሁሉ አብዝቶ ዱዓዕ ያደረገ ሰው ነው።

እደለኛ ሰው ማለት.....!

ሱብሃነሏህ
ወል ሀምዱ ሊላህ
ወላ ኢላሃ ኢለሏህ
ወሏሁ አክበር

ማለት ፀሀይ ከወጣችበት ሁሉ የተሻለና የበለጠ መሆኑን ተረድቶ እነዚህን ውድ ቃላት አብዝቶና ደጋግሞ ያላቸው ሰው ነው።

እደለኛ ሰው ማለት.....!

ይህንን ካወቀ በኋላ የሰራበትና ሌሌሎችም እንዲያውቁና እንዲተገብሩ በማሰታወስና በማካፈል የአጅሩ ተካፋይ የሆነ ሰው ነው።


https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg


በሙሥሊምነታችን የሚመጣብንን ችግር በስልጤነት፣ በኦሮሞነት፣ በአማራነት፣በትግሬነት ወዘተ መፍታት አንችልም። መፍታት የምንችለው በሙሥሊምነት ብቻ..!

https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg


መጅሊስ መውሊድን አከበረ ማለት መጅሊሱ ቢድዓ ሰራ ማለት እንጅ መውሊድ ሱና ወይም መሽሩዕ ሆነ ማለት አይደለም።

https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg


ብዙ ሠለምቴዎች ከሠለሙ በኃላ በአቂዳቸው ይጠነክሩ ዘንድ በአስሓቡል የሚን የትምህርት ገበታ አለ ። ይህንን አስመልክቶ በመቶ የሚቆጠሩ የሠለምቴዎች ስብስብ በሥሩ ይገኛሉ ።

የሚማሩበት የአስሓቡል የሚን የትምህርት ዘርፍ ።
ሠለምቴዎች አዲሥ እሥልምናን እንደተቀበሉ ሥለ ሶላት ማስተማር ።

ቁርኣን ከሑሩፍ እስከ ማኽተም ።
በኦላይን ትምህርት መሳተፍ የምትፈልጉ እህቶች ከሥር በተዘረዘሩት አድራሻ ማናገር ይችላሉ።

http://t.me/Menar_001
http://t.me/Bint_0
https://t.me/Quran_is_life_Sari_A
https://t.me/OBintMahmud

ወደ እሥልምና የመጡበትን የሒዳያ ሰበቦዎን ማካፈል እና ለሌሎች ትምህርት ይሆን ዘንድ በእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራማችን እንግዳ መሆን ከፈለጉ ፦

http://t.me/Muslim_negn9
http://t.me/nuni7274
ወይም https://t.me/Selmeta

አስሐቡል የሚን Page
https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg


እንደ ቀላል አትዩት‼

ልጅቱ እንዲህ ትላለች

        ከወራት በፊት ከቤት ልወጣ አሰብኩና ከነበሩኝ ሽቶዎች የበለጠ መልካም መዐዛ ያለውን ለመቀባት ወሰንኩ ፤ በእርግጥ ሴት ልጅ ሽቶ ተቀብታ መውጣት እንደሌለባትና ሽቶ ተቀብታ ከቤት መውጣቷ ከባድ ወንጀል እንደሆነ አውቃለሁ ፤ ነገር ግን ማንም ወንድ አያሸተውም ትኩረታቸውንም አልስብም እንዲሁም ከሴት ጓደኞቼ ጋር ስገናኝ ከኔ መልካም ሽታ እንዲያገኙ ብዬ በማሰብ ነበርና ለጥንቃቄም ብዬ ሁለት ሶስት ጊዜ ብቻ ነበር የተቀባሁት። የሆነው ሆኖ ከቤት ውስጥ ሆኜ በአፕሊኬሽን ኡበር ታክሲ ጠራሁና መንገዴን ጀመርኩ። ሹፌሩ እጅግ ዝምተኛና ስርአት ያለው ሰው ነበር ፣ መድረስ ከፈለግኩበት ስፍራም እንደደረስኩ ክፍያዬን ፈፅሜ ወረድኩ። ከታክሲ ከወረድኩ ሰላሳ ደቂቃዎች በኃላ ሞባይል ስልኬ ላይ መልዕክት ደረሰኝ ፤ ቁጥሩ ለኔ እንግዳ ነበር ፤ ማነው  የማላውቀው ሰው ደሞ መልዕክት የላከብኝ ብዬ እራሴን እየጠየቅኩ  መልዕክቱን ከፈትኩት፤
መልዕክቱ እንዲህ የሚል ነበር፦

『በጣም ውብ ነሽ በተለይ የተጠቀምሽው ሽቶ ደግሞ መዓዛው ልዩ ነው።』

ወይ ጥፋቴ ! ለካስ መልዕክቱን የላከው ያደረሰኝ የታክሲ ሹፌር ሆኗል ፤ በቃ ይህንን መልዕክት ሳነብ ሰውነቴን ሁሉ ነዘረኝ አለቀስኩም ፤ እጅግ ተፀፀትኩ ፤ ወደ ቤትም ተመልሼ ረከአተይን ሰገድኩና  ወደ ጌታዬ ተፀፅቼ መሀርታን ጠየቅኩት ፤ ፊት ለፊቴ የመጣው ያ የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ንግግር ነበር ፤ እንዲህ የሚለው ንግግራቸው፦ 【የትኛዋም ሴት ሽቶ ተቀብታ ሰዎች እንዲያሸቱላት (ትኩረታቸውን ለመሳብ) በአጠገባቸው ካለፈች እርሷ ዝሙተኛ ናት።】

እናም እህቶቼ ነገሩ ከባድ ነው እንደምናስበው ቀላል አይደለምና እንጠንቀቅ !


http://t.me/AshaBuleyamine


🍄 ሱረቱል~ አል-ካህፍ 🍄
………🍃🌸🍃………

﷽ {إنّ اللهَ وملائكتَهُ يُصَـلُّونَ على النبي يا أيها الذين آمنوا صَلُّوا عليه وسلِّمُوا تسليما} اللهم صلِ و سلم على نبينا محمد ﷺ
…………🍃🌸🍃…………
http://t.me/AshaBuleyamine


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
‏﷽
‏۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى
‏النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا
‏عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ۝ ﷺ

#አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ: _የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡
#እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ _ላይ የአክብሮት እዝነትን _አውርዱ፡፡ የማክበርንም _#ሰላምታ ሰላም በሉ "
_(ሱረቱ አል- አሕዛብ -

http://t.me/AshaBuleyamine


#ግጥም
ዛሬማ ምን አለ ባይሰግዱ ባይፆሙ፣
ይቸግራል እንጂ አላህ ፊት ሲቆሙ።

ዛሬማ ምን አለ ቢጠጡ ቢሰክሩ፣
ይቸግራል እንጂ ሙተው ሲቀበሩ

ዛሬማ ማን አለ የሚያጋልጥህ፣
ከቀብር ስትገባ ይታያል ጉድህ።

ዛሬማ ማን አለ የሚጋልጥሽ፣
ከቀብር ስትገቢ ይታያል ጉድሽ።

#ሸይኽ #ሙሐመድ #ወሌ አሕመድ ረሒመሁላህ
  
http://t.me/AshaBuleyamine


አሚን🌹


🌺


➧መልካም_ጓደኛ

ሁለት ውብ የሂወት ኡደቶችን ይለግሰሀል…"አንደኛው አዚህ ዱንያ ላይ ሲሆን" "ሁለተኛው ደግሞ ጀነት ውስጥ ይሆናል"

መልካም_ጓደኞች «ወደ አሏህ መንገድ… ይጠሩሀል…» «ከጠፋህባቸው… ይፈልጉሀል…» ከተዘናጋህ… አስታውሱሀል»

«…በዱአቸው ውስጥ…ያካቱሀል»
«ልክ እንደ ከዋክብቶች… መርከብህ መንገድ ከሳተች…ይመሩሀል…» «ነገ ከአሏህ አርሽ ስር…ኢንሸአላህ…አብረው ይጎዳኙሀል…» «ጀነት ውስጥ ፈልገውህ ካጡህ…

አሏህን ወደነሱ እንዲቀላቅልህ ይለምኑልሀል» "አሏህ ሶሊሆቹን አድርጎ ከሶሊሆቹ ያወዳጀን ከሶሊሆቹ ጓደኞቻችን አይነጥለን በያሉበት ይጠብቅልን "
አሚን🌹

https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg

Показано 20 последних публикаций.