💚የፍቅር ሚዛን
💛የፍቅርን እውነተኛ ጣዕም ለማወቅ ሁለት ሰዎች እኩል መንገድ መምጣት መቻል አለባቸው። እኩል መምጣት ቢያቅታቸው እንኳን ተቀራራቢ መንገድ መጓዝ ግድ ይላቸዋል። አንዱ ብቻ መንገዱን ገስግሶ ቢመጣና ሌላው ከቆመበት ሳይንቀሳቀስ ቢጠብቅ የፍቅር ሚዛን ይዳፋል።
❤️ፍቅር ጤናማ የምትሆነው ሚዛናዊ ስትሆን ብቻ ነው። ፍቅር በየጊዜው ዘንበል ቀና ብትልም ፈጽሞ ወደ አንዱ ብቻ መውደቅ የለባትም። ወደ አንዱ ከወደቀች፤ አንዱ ተሸካሚ ሌላው ተጫዋች ይሆናል። ተሸካሚው የፍቅርን አበሳ፤ ተጫዋቹ የፍቅርን ጨዋታ ብቻ ይመለከታሉ። እይታቸው የተለያየ ስለሚሆን፤ ፍቅርን በአንድ አቅጣጫ አይመለከቷትም። ታዲያ እንዴት ሊግባቡ ይቻላል? በፍጹም አይግባቡም።
💚በሰው ስሜት እንዳንጫወት፤ የፍቅርን መንገድ ከመጀመራችን በፊት፤ ምን ያህል እርቀት መጓዝ እንደምንችል እናስብ። ከሚወደን ሰው ጋር መኖር በተጫዋቹ ቦታ መቀመጥ ፤ ከምንወደው ሰው ጋር መሆን በተሸካሚው ቦታ መሆን እንዳይሆንብን።
💛የፍቅርን ሚዛናዊነት አይቶ ጨዋታውን ለማጣጣም አፍቃሪ እና ተፈቃሪ ሆነን ሳይሆን፤ ሁለት አፍቃሪዎች ሆነን መቅረብ አለብን። እንደ ሚዛን ጨዋታ፤ ጨዋታውን ለማጣጣም አንዴ እላይ አንዴ እታች ቦታ እየተለዋወጥን የፍቅርን ሚዛን መጠበቅ ግድ ይለናል።ፍቅር የባላይ ልሁን ለሚል ሰው አትሆንም፤ ከላይ ብቻ ተሰቅሎ ሚዛኑን ሌላው ላይ ማዳፋት ከፍቅር ጨዋታ የራቀ ነው።
❤ፍቅር እኔ ብቻ ልሸከማት ለሚልም አትሆነም፤ ምክንያቱም ጣዕሟን ለማጣጣም ስለሚከብደው። ምናልባት በፍቅር ሚዛን ላይ ከሆንን ፤ ግንኙነታችን እንቃኘው፤ ማነው ሸክሙን የተሸከመው፤ ማነው ጨዋታውን እያጣጠመ ያለው? በሰው ስሜት እንዳንቀልድ ለፍቅር ሚዛናዊ ለመሆን እንሞክር። የሚወዱን ሰዎች ሊወደዱ ይገባቸዋል፤ እኛ ሚዛኑን መጠብቅ ካልቻልን ከፍ ሊያደርጋቸው ለሚችል ለሌላ ሰው ቦታውን እንልቀቅላቸው። የምንወዳቸው ሰዎችም ሚዛኑን መጠበቅ ካቃታቸው፤ ፍቅር ለሚገባው፤ ዝቅ ካልንበት ከፍ ለሚያደርገን ሰው ቦታውን ቢለቁልን መልካም ነው።
ውብ ምሽት❤️
.....✍️ t.me/Asresee ......✍️