‼️አስገራሚ እውነታዎች:- ካንሰር
• ሁሉም ሰው በካንሰር ሊጠቃ ይችላል፡፡
• ከ100 በላይ የካንሰር አይነቶች አሉ፡፡
• ከግማሽ በላይ የሚሆኑ የካንሰር አይነቶችን መከላከል ይቻላል፡፡
• 90 በመቶ የካንሰር መንስኤ አካባቢያዊ ሲሆን 10 በመቶ ደግሞ ዘረ መላዊ ነው፡፡
• በዓለማችን በካንሰር ምክንያት ከሚፈጠረው አጠቃላይ ሞት ውስጥ ትምባሆ ማጨስ 25 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ ይይዛል፡፡
• 90 በመቶ የሳምባ ካንሰር መንስኤ ሲጋራ ማጨስ ነው፡፡
• አንዲት ሲጋራ ውስጥ ከ7 ሺህ በላይ ኬሚካሎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከ70 በመቶ የሚበልጡት ካንሰር አምጪ ናቸው፡፡
• በዓለማችን በካንሰር ምክንያት ከሚፈጠረው አጠቃላይ ሞት ውስጥ አልኮል መጠጣት ከ3 እስከ 5 በመቶ ድርሻ ይይዛል፡፡
• ዓለም ላይ ሴቶችን በብዛት የሚያጠቃው የካንሰር አይነት የጡት ካንሰር ነው፡፡
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በጡት ካንሰር የመያዝ እድልን ከ25 - 30 በመቶ ይቀንሳል፡፡
• ዓለም ላይ በየቀኑ ከ27 ሺህ በላይ ሰው በካንሰር ይሞታል፡፡ ይህም በዓመት ከ10 ሚሊዮን በላይ ይሆናል፡፡
• በካንሰር ምክንያት ከሚሞተው የዓለም ህዝብ ውስጥ 70 በመቶ የሚሆነው ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች የሚኖር ነው፡፡
• ወንዶችን በብዛት ከሚገድሉ የካንሰር አይነቶች ውስጥ የሳምባ ካንሰር፣ የጉበት ካንሰር፣ የጨጓራ ካንሰር፣ የአንጀት ካንሰር እና የፕሮስቴት እጢ ካንሰር ይጠቀሳሉ፡፡
• ሴቶችን በብዛት የሚገድሉ የካንሰር አይነቶች ውስጥ የጡት ካንሰር፣ የሳንባ ካንሰር፣ የአንጀት ካንሰር፣ የመሐጸን በር ካንሰር እና የጨጓራ ካንሰር ይጠቀሳሉ፡፡
• ካንሰር የዓለም ኢኮኖሚን ክፉኛ እየጎዳ ይገኛል፡፡ የዓለም ሀገራት በአመት ከ1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ለካንሰር ህክምና ያወጣሉ፡፡
• ትምባሆ ባለማጨስ፣ አልኮል ባለመጠጣት፣ ጤናማ አመጋገብ በመከተል እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ብቻ የካንሰር ተጋላጭነትን እስከ 30 በመቶ መቀነስ ይቻላል፡፡