መንገዱ የሚጀምረው አሁን ካለህበት ቦታ ነው
በሕይወትህ ውስጥ ለውጥ መደረግ እንዳለበት ካወቅክ፣ ከዓላማህ በጣም የራቅክ ወይም እንዴት እዚያ እንደምትደርስ ገና ያልገባህ ብትሆንም እንኳን ችግር የለውም፡፡
ገና እየጀመርክ ቢሆንም ችግር የለውም፡፡
ገና ከታች ብትሆንና መንገድህ በግልጽ እየታየህ ባይሆንም ችግር የለውም፡፡
ገና በተራራህ ግርጌ ያለህና፣ ለማሸነፍ በሞከርክ ቁጥር እየወደቅክ ብትሆንም ምንም አይደለም፡፡
አብዛኛው የፈውስ ጉዞ የሚጀመረው ከዝቅታ ስፍራ ነው። ይህ የሚሆነው ዝቅታ ላይ ስትሆን በድንገት ብርሃን ስለሚታይህ፤ መጥፎዎቹ ቀናት በአስማት ወደ አንድ የደስታ አይነት ስለሚለወጡ ወይም የሆነ ሰው ከራስህ እብደት ስለሚያድንህ አይደለም፡፡ ዝቅታ የለውጥ መነሻ የሚሆነው፤ ብዙ ሰዎች “እንደዚህ አይነት ስሜት እንደገና ሊሰማኝ አልፈልግም፡፡" ብለው የሚወስኑበት ቦታ ስለሆነ ነው።
✍Brianna weist
📚@Bemnet_Library