በሕይወት ውስጥ ብቸኛው ችግርህ፣ አንድ ነገር ሊሆን በሚገባው መንገድ ሊሆን አልቻለም ብለህ ማሰብህ ነው፡፡ አንድ ነገር ሊሆን ይገባዋል ብለህ ባሰብከው መንገድ ካልሆነ፣ ምናልባት ያ ነገር የሆነ ሰው በሚፈልገው መንገድ ሆኖ ያ ሰው ተደስቶበት ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙ ሰዎች በአንድ ላይ “በፈጣሪ እናምናለን” ይላሉ፤ ስለዚህ ምናልባት ያ ነገር በእነርሱ መንገድ ሆኖ ይሆናል፡፡ በመሰረታዊነት ሁሉም ነገር አንተ ሊሆን ይገባዋል በምትለው መንገድ አይሆንም፡፡
እስቲ አንተ የምታስብበትን መንገድ ተመልከት ፤ ከሁለት አመት በፊት የምታስበውና ዛሬ የምታስበው ተመሳሳይ ነው? አይደለም፡፡ ስለዚህ ምናልባት ከሁለት አመት በፊት ትፈልጋቸው የነበሩት እነዚያ ነገሮች ባለመሆናቸው ደስተኛ ነህ፡፡ ነገር ግን ያንን ለማስተዋል ሁለት አመታት ፈጅቶብሃል፡፡ አስፈላጊው ነገር የሕይወት ተሞክሮህ ምን ያህል ጥልቅና አስደሳች መሆኑ ላይ ነው፡፡
📓የሕይወት ኬሚስትሪ
✍️ሳድጉሩ ጃጋዲሽ
📖@Bemnet_Library