ብልሁ ንጉስ
በአንድ ወቅት የዊራኒ ከተማን የሚያስተዳድር አንድ የተከበረና ብልህ ንጉስ ነበር፡፡ ንጉሱ በግርማው ይፈራ፣ በጥበቡም ይወደድ ነበር፡፡ በከተማው እምብርት የሚገኘው ጉድጓድ በቀዝቃዛና የሚያብረቀርቅ ውሃ የተሞላ ነው፡፡ ሌላ የውሃ ጉድጓድ ስለሌለ ንጉሱንና ባለሟሎቹን ጨምሮ ሁሉም የከተማው ነዋሪ ከዚህ ጉድጓድ ነው የሚጠጡት፡፡
አንድ ምሽት ሁሉም በእንቅልፍ ተይዘው ሳለ አንድ ጠንቋይ ወደ ከተማው ይገባና ወደ ጉድጓዱ ውስጥ ሰባት የማይታወቁ ጠብታዎች ጨምሮ «ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ከዚህ ውሃ የሚጠጣ ያብዳል» በማለት ተናገረ፡፡
በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ከንጉሱና ከግል አገልጋዩ በቀር ሁሉም ነዋሪዎች ከውሃው በመጠጣታቸው ጠንቋዩ አስቀድሞ እንደተናገረው ሁሉም አበዱ፡፡
የዛን ዕለት... ቀኑን ሙሉ በጠባብ መንገዶችና በገበያ ስፍራዎች የሚመላለሱ ሰዎች ‹‹ንጉሱ አብዷል፡፡ ንጉሱና ባለሟሉ አዕምሯቸውን ስተዋል፡፡ በእብድ ንጉስ መመራት የለብንም፡፡ ከዙፋኑ ልናወርደው ይገባል» ሲሉ አንሾካሾኩ፡፡
የዛን ዕለት ምሽት ንጉሱ በአንድ የወርቅ ዋንጫ የጉድጓድ ውሃ እንዲመጣለት አዘዘ፡፡ ከዚያም ለራሱ ግጥም አድርጐ ጠጣና ለባለሟሉ እንዲጠጣ ሰጠው፡፡ ይሄን ጊዜ በዊራኒ ከተማ ሃሴት ሆነ፡፡ ንጉሱና ባለሟሉ አዕምሯቸው ተመለሰላቸው ሲሉም አሰቡ፡፡
✍️ካህሊል ጂብራን
📚@Bemnet_Library