ክፍል ሁለት 2
"ምን? ማለት? እንዴት ሊሆን ይችላል? ለምን? የሚሉ ቃላት ከአፌ በድንጋጤና በብስጭት ይወጡ ነበር። ምንም ሳልላት ወዴት እንደምሄድ ሳላውቅ እየሮጥኩ ወጣሁ። ጓደኛዬን በጣም ነበር የምወዳት። እሷ ለኔ ከእህትም በላይ ነበረች:: ያለምንም ምክንያት እንዲህ ልታደርግብኝ አትችልም። ማሰብ ያቆምኩኝ ያክል ተሰማኝ። እሺ ምንድነው የማደርገው? ያለኝ አማራጭ ደግሜ እውነቱን መንገር ነው። "
" ' እግዚአብሔር መልካም ነው። እኛ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን እንፀልያለን ደግሞም ዳኑን እኛ እራሳችን እናናግረዋለን። አሁን ፈተና ስለደረሰ ራስሽን አረጋግተሽ ለማጥናት ሞክሪ።' ብለው እኔን ማረጋጋቱ ተያይዘውታል አብረውኝ የሚያገለግሉ ጓደኞቼ። እኔ ግን ማረጋጋትም ቀስ ብሎ ማሰብም አልቻልኩኝም። ዳኒ እኔን አለማመኑ ቢያበሳጨኝም በተደረገው ክፉ ስራ ማዘኑን ሳስብ ያሳዝነኛል። እሱም እውነት አለው። ስለዚህ የቻልኩትን ማድረግ አለብኝ ብዬ ወሰንኩኝ። የመጨረሻ ምርጫዬ ጓደኛዬ ኤልሳ ናት። ያኔ ሆስፒታል ተኝቼ 'ጥፋቱ የኔ ነው' ያለችኝ ምክንያት በመጠየቅ ሰበብ እሷን አግኝቼ ለዳኒ የተደረገው ሁሉ እንድትነግረውና እኔ ምንም ነገር እንዳላደረኩኝ እንድታስረዳው ልጥይቃት ስልክ ደወልኩላት። እያለቀሰች እናገረችኝ። እኔ ግራ የገባኝና ያናደደኝ የሷ ማልቀስ ነው።የምንገናኝበትንና ሰዓት ወስነን ስልኩ ተዘጋ!"
"ከእሷ ቀድሜ ስለነበር የተገኘሁት እሷ ስትመጣ ሳያት መሆን የሌለብኝ ስሜት ተሰማኝ...ጥላቻ...። ' ማርቲ ማድረግ የሌለብኝን ነገር አድርጌያለሁ። ይቅር በይኝ!' ብላ ንግግሯን ስትጀምር በቅድሚያ ትክክለኛውን ነገር ንገሪኝ ቀጥሎም እንዴት ልትረጂኝ እንደምትችዪ አሳውቂኝ። ብዬ ተቆጣዋት! ኤልሳም እሷ እክክለኛውን ነገር እንደምትነግረው ቃል ገባችልኝ። እኔም ድጋሚ ልታገኘኝ ከፈለገች ይህን ካደረገች በኋላ እንደሆነ ነግሬያት ተለያየን።"
"እኔ ምንም ነገር ውስጤ አልከበደብኝም። እኔ ጋ እውነት አለ። ጥፋት አላጠፋሁም። ቢሆንም ግን ዳኒ እውነቱን ካወቀ በኋላ ብንለያይም አይጨንቀኝም።" ትላለች ማርታ። በዚህ ሰዓት በራስ መተማመንም የዳኒ ናፍቆትም በንግግሯ ውስጥ ይነበባል።
"ከሁለት ቀናት በኋላ የእጅ ስልኬ ጮኸ" ትለናለች ማርታ....እስቲ እንከታተላት
"ሄለው ማን ልበል? ስል 'ማርቲዬ ደህና ነሽ? ሔለን(የተቀየረ ስም) ነኝ' ሔለን አብራኝ የተማሪዎች ህብረት የምትመራ መልካም እህት ናት። 'ዛሬ ዳኒን አግኝተን አውርተን ነበር ሀሉን ነገር በስርዓት ተነጋግረናል። ለዕረፍት ቤተሰብ ጋ ስለሄደ ከሁለት ቀን በኋላ ተመልሶ እንደሚመጣና እንደሚያገኝሽ ተስማምተናል። ስለዚህ ጠብቂው። ሁሉም ነገር ተስተካክሏል እሺ ማርቲ አታስቢ። በቃ እንገናኛለን' ብላኝ ስልክ ዘጋን። የሆነ ደስታ ተሰማኝ ትላንት የሆነውን ነገር ረሳሁት።ዳኒ መጥቶ እውነትም እስከምንነጋገርና ወደ ቀድሞ ፍቅራችን እንደምንመለስ ናፍቄያለሁ።"
"ቀኑ አልፎ በሦስተኛው ቀን በአካል ተገናኘን። ውስጤን ናፍቆት ንዴት ሃዘን ይሰማኛል።ምክንያቱ ብዙ ነው። የመጀመሪያ ጥያቄዬ የነበረው የሱን ደህንነትና ለምን ስልኬ እንዳላነሳ ነበር የጠየኩት። ዳኒም ' ማርቲ ሁሉንም ነገር ደርሼበታለሁ ኤልሳም ነግራኛለች። አንቺን አለማመኔ አሳፍሮኝ ነው ስልክ ያላነሳሁት። አሁን ምንም ነገር ልታስረጂን አልፈልግም ሁሉን አውቄያለሁ። ምንም ወሬ ሳላበዛ ይቅርታ ብቻ አድርጊልኝና ፍቅራችንን እንቀጥል።' ሲለኝ ምንም ማውራት አልፈለኩም ምክንያቱም ራሱ ጥፋቱን አምኗል። ኤልሳንም ደውዬ ይቅር ብዬሻለሁ አልኳት። "
"ከብዙ ቀናት በኋላ ዳኒ 'እራት ካልጋበዝኩሽ' አለኝ። እኔም ደስ አለኝ። እሺ አልኩት። ነገር ግን የእራቱ ግብዣ ጓደኛው በተከራየው ቤት ውስጥ እንደሆነ ሲነግረኝ ውስጤ መሄድ እንደሌለብኝ ቢነግረኝም መጥፎ ነገር ሊፈጠር አይችልም በሚል የእራት ግብዣውን 12:00 ለማድረግ ተስማማን።ነገር ግን ማንም ሰው አብሮሽ እንዳይማጣ ሲለኝ ተጠራጥሬ ነበር።"
12:00 ላይ ጓደኛው ቤት ጋ ስደርስ ወጥቶ ወደቤት አስገባኝ። ቤቱ በሚያምር ሁኔታ አድምቆታል። ሰላም ተባብለን አንድ ወንበር ነበረች እሷ ላይ ልቀመጥ ስል 'በፍፁም አይሆንም እዚ ጋ ነው መቀመጥ ያለብሽ' ብሎ አልጋው ላይ አስቀመጠኝ። እሱም ተቀመጠ። የተዘጋጀውንም እራብ በላን። ከምሽቱ 1:00 ላይ እጄን መንካትና ሰውነቴ ማሸት ሲጀምር ብድግ ብዬ ተንሳሁ። ምን እያደረክ ነው እዚ'ኮ ብቻችንን ነን። ጌታን መበደል የለብንም በቃ እራት በላን አይደል እንሂድ ስለው እጄን ስቦ አስቀመጠኝና 'የምነግርሽ ነገር አለ' አለኝ። እሺ ምንድነው ዳኒ የምትነግረን? ' ትወጂኛለሽ' ብሎ ሲጠይቀኝ ተናደድኩኝ። 'በእርግጥ ድንግል ነሽ? እኔ እስካሁን ማመን አልቻልኩኝም። እዛ እላጋ ላይ አብሮሽ የተቀመጠው ወንድምሽ ነው ብዬ ለማመን እስካሁን ከብዶኛል። ስለዚህ #ድንግልናሽን_ካልሰጠሽኝ_እጣላሻለው ደግመንም አብረን አንሆንም። አንቺ በእርግጥ ድንግል ከሆንሽ ይኸው ዛሬ አይቼ ልመን' ሲለኝ ፈራሁኝ። ሁለት ፍርሃት። አንደኛ ጌታን ልበድል መሆኑ ሁለተኛ ዳኒን ላጣው በመሆኔ። ግራ ገባኝ። ትሰማለህ ዳኒ? በጣም እወድሃለሁ አፈቅርሃለሁ ታምኜልሃለሁ። ድንግል ነኝ ስልህ ልታምነኝ ይገባ ነበር። ነገር ግን አላመንከኝም። እንድታምነኝ #ዝሙት ሰርቼ አላሳምንህም! ስለዚህ በጣም አዝናለሁ። ድንግልናዬን እንዳላጣ ብዬ ሳይሆን ዋጋ ከፍሎ ያዳነኝና የራሱ ማደሪያ ያደረገኝን ጌታ አልጋ ላይ ተኝቼ ዝሙት ሰርቼ አልበድለውም። ቅድስናዬ አስጠብቄ ጌታን አስደስቼው ክብረ ንፅህናዬ ጠብቄ እስከትዳር እኖራለሁ። ለአንተ ይቅርታ አድርጌልሃለሁ። ከዚህ በኋላ ግን እኔና አንተ ማቼውም ፍቅረኛሞች መሆን አንችልም። ብዬው ልወጣ ስል እጄን ያዘኝና አልጋው ላይ ጣለኝ። እፍን አድርጎ ያዘኝ። ነገር ግን እንዴትም ብዬ ያለ የሌለ ኃይሌን ተጠቅሜ እጁን ንክስ አድርጌው በአንድ እግር ጫማ ከዛ ቤት እየሮጥኩኝ ወጣሁ። ጌታ ታደገኝ።" በማለት እንባና ሲቃ በተሞላ መልኩ ታሪኳን አጫወተችኝ። እንዲህ ያስለቀሰኝ በእንደዚህ አይነት ህይወት ያለፈች እህቴ ትዝ ብላኝ ነው። የሷ ታሪክ ሌላ ጊዜ እነግርሃለሁ" ብላ ሌላ ታሪክ ልትነግረኝ ቃል ገብታልኝ ታሪኳን ቀጠለች።
በመጨረሻም ትለናለች ውድ እህታችን " እሱም ሌላ ሱስ ውስጥ ገብቶ ከጓደኛዬ ኤልሳ ጋር አብረው ጓደኝነት ጀመረው ነበር እኔም በሰላም ተመረኩኝ። ከምርቃቴ ሦስት አመት በኋላ በጣም የምወደውና የሚወደኝ ውድ ባል አገባሁኝ። #ድንግልናዬን_ለባሌ ሰጠሁት ቆንጆም ልጅ ወለድን። የዳንኤል ታሪክ ስሰማ ከኤልሳ ጋር አብረው እንዳልቀ ጠሉና ሌላ ሴት እንዳገባ ነው"
" ስለዚህ #ድንግል_ለባል_እንጂ_ለጓደኛ_አይሰጥም" በማለት ማርቲ ታሪኳን በዚህ አጠናቀቀች። እኛም እሷ ከተነገርችው ንግግር አንዱን ወስደን የታሪኩ መቋጫ እናድርግ......
💢 #ድንግልና_ለባል_እንጂ_ለጓደኛ_አይሰጥም! 💢
💍 @Biblicalmarriage 🌷
ለአስተያየት 👉 @Biblicalmarriage_bot
የሚያሸልም ጥያቄ 3:40 ላይ ይጠብቁን! ታሪኩን ያላነበበ መልሱን በፍፁም ሊያገኘው አይችልም!
❤️ @Biblicalmarriage ❤️