የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያወጣው የዶላር ሽያጭ ጨረታ ማጠናቀቁን አስታወቀ።
- አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካኝ 135.6 ብር ዋጋ መሸጡን አስታወቋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት መሰረት፣ የአንድ የአሜሪካ ዶላር አማካኝ የምንዛሪ ዋጋ 135 ነጥብ 6185 ብር መሆኑን ይፋ አደረገ። በዚህ ጨረታ የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ጨምሮ 27 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተሳትፎ እንደነበር ገልጿል።
ማዕከላዊ ባንኩ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝና ከዋጋና ከውጭ ምንዛሪ መረጋጋት ጋር በሚስማማ መልኩ ተጨማሪ ጨረታዎችን እንደሚያካሂድ አስታውቋል። ይህ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ የገንዘብ ገበያውን ለማረጋጋትና የውጭ ምንዛሪ ጥገኝነትን ለማሻሻል የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑ ተጠቁሟል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ወደ ትግበራ ከገባ ካለፈው ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም አንስቶ የአሁን የውጭ ምንዛሬ ሽያጭ ጨረታ ሲወጣ የአሁኑ ለ2ኛ ጊዜ መሆኑ ታዉቋል ።