የባንኩን ሴት አመራሮች ለማብቃት እንደሚሰራ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሴት አመራሮችን ለማብቃት ጥረት እንደሚያደረግ የባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር እመቤት መለሰ ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም በዋና መስሪያ ቤቱ በተለያየ የኃላፊነት ደረጃ ላሉ ሴት አመራሮች በተዘጋጀው ስልጠና ላይ አስታወቁ፡፡
የሴት አመራሮችን የመሪነት ክህሎት ለማሳደግ በተዘጋጀው ስልጠና ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር እመቤት በፋይናንስ ተቋማት ከፍተኛ የሆነ የሴት አመራሮች እጥረት መኖሩን ጠቅሰው በባንኩ ውስጥ ያለውን ክፍተት ለመሙላት ሴቶችን አብቅቶ ወደ አመራርነት ማምጣት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል፡፡
ስልጠናው ሴቶችን ወደ አመራር ለማምጣት እና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እንዲሁም በአመራር ላይ ያሉ ሴቶችን ብቃታቸውን ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር እመቤት በባንኩ ውስጥ የሚታየውን የሴት አመራሮች እጥረት ለማሻሻል ስራዎች እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
ሴቶች ወደ አመራርነት እንዳይመጡ በርካታ ተግዳሮቶች ቢኖሩም እራሳቸው ሴቶች ፈተናዎችን ተቋቁመው ወደ አመራርነት ለመምጣት ብቃታቸውን ማሳደግና ተወዳዳሪ መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
ስልጠናው ተወዳዳሪ፣ ተነሳሽነት እና ሞራላቸው የተገነባ ሴቶችን ወደ አመራርነት በማምጣት ተቋሙን ውጤታማ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የጎላ ድርሻ እንዳለውም ነው ፕሬዝዳንቷ በመክፈቻ ንግግራቸው ያመላከቱት፡፡
ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆየውን ይህን ስልጠና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና የአዲስ አበባ ቻምበር ኦፍ ኮሜርስ በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡