"በቅድሚያ ራሳችንን እናሸንፍ"
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ
ዳሸን ባንክ ጠንካራ የአገልግሎት ባህልን ለማሳደግ በማለም ያዘጋጀውን ዕቅድ ላሳኩ ቅርንጫፎች ዕውቅና ሰጠ።
ባንኩ “ሆኖ መገኘት” በሚል መሪ ሃሳብ ያስጀመረው የአገልግሎት ባህልን የመተግበር ዕቅድ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች ዕውቅና ሰጥቷል፡፡
በእውቅና መርሃ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ባንኩ “ሆኖ መገኘት” በሚል መሪ ቃል የአገልግሎት ባህልን የመተግበር ዕቅድ ነድፎ እየሰራ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡
“ዛሬ የተሰባሰብነው ቅርንጫፎቻችን ላስመዘገቡት ስኬት ዕውቅና ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ደንበኞቻችንን በሁሉም ስራዎቻችን ተቀዳሚ የምናደርግበት የአገልግሎት ባህል ለማስረፅ ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ ለማረጋገጥ ጭምር ነው” ብለዋል፡፡
ለኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ዘርፍ አዲስ የሆነው “ሆኖ መገኘት” የአገልግሎት ባህል (Stay Relevant Service Culture) የመገንባት ፕሮግራም ዳሸን ባንክ ታዋቂ የሆነ አማካሪ ድርጅት በመቅጠር ያዘጋጀው መርሃ-ግብር እንደሆነም ዋና ስራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የታደመው አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገ/ስላሴ የረጅም ዓመት የአትሌቲክስ ህይዎት የስኬትና የፈተና ተሞክሮውን አካፍሏል ።
ለምናልመው ግብ ፅናትና ተግቶ መስራት ወሳኝ መሆኑን ያነሳው አትሌት ሃይሌ ለደንበኞች አገልግሎት ከፍተኛ ትኩረት መስጠት ውጤታማ እንደሚያደርግ አስረድቷል።
በዳሸን ባንክ ቺፍ ኤክፒሪየንስ ኦፊሰር እየሩሳሌም ዋጋው በዛሬው ዕለት ዕውቅና ያገኙ ቅርንጫፎች የትኞቹን መለኪያዎች አሟልተው እንደተመረጡ አብራርተዋል።
በቀጣይም ዕቅዱን ለማሳካት ጠንክረን መስራት ይገባል ብለዋል።