ዳሸን የገዘፈ ስሙን ተጠቅሞ ደንበኞች የሚተማመኑበት ባንክ ሆኖ እንደሚቀጥል አስታወቀ
አንድ እርምጃ ወደ ፊት ቀድሞ የሚገኘው ዳሸን ባንክ ይህንን ግዙፍ ስም እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ደንበኞች የሚተማመኑበት ባንክ ሆኖ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡
ይህ የተገለፀው ከጥር 20-25 ቀን 2017 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ሲከበር የቆየው የዳሸን ባንክ የደንበኞች ሳምንት የመዝጊያ ሥነ ስርዓት በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በተከናወነበት ወቅት ነው፡፡
የዳሸን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በመርሃ-ግብሩ ለተገኙ የባንኩ ደንበኞች፣የባንኩ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች ባደረጉት ንግግር ምንም ፈታኝ ነገሮች ቢኖሩም ለዳሸን ባንክ መጪው ጊዜ ብሩህ ተስፋ ያለው መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
የዳሸን ባንክ ደንበኞች ሳምንት ሲከበር የተለያዩ እንቅስቀሴዎች ሲከናወኑ እንደነበር ያስታወሱት አቶ አስፋው፣ ጥር ለባንኩ ትልቅ ወር እንደሆነ፣ ይህም ትልቅ ራዕይ ያላቸው 11 ባለሃብቶች ሃብታቸውን አውጥተው ዳሸን ባንክን የመሰረቱበት እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
ዳሸን ባንክ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ዕድገቱን እየተከተለ መሪ ቃሉን ሲቀይር ሁለት ነገሮች ታሳቢ እንደሚደረጉ ያብራሩት አቶ አስፋው፣እነዚህም ደንበኞችና ደንበኞች የሚስተናገዱበት ስልት ቴክኖሎጂን መርህ ያደረገ እንዲሆን የሚሉት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
“ደንበኛን ማመስገን” በሚል ቃል ሲከበር የቆየውን ይህንን ልዩ የደንበኞች ሳምንት በዳሸን ባንክ በዋናነት ለማክበር ያስፈለገው ደንበኞችን ለማክበር፣ ለማመስገንና አልፎ ተርፎም ቤተሰብ ሆነው የተወዳጁት ደንበኞች በአገልግሎቱ ያላቸውን ገንቢ አስተያየት ለመቀበል መሆኑን አቶ አስፋው ገልጸዋል፡፡