በትግራይ ክልል ከ11 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበጋ መስኖ እየለማ ነው
*********************
በትግራይ ክልል ከ11 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመጀመሪያ ዙር የበጋ መስኖ እየለማ መሆኑን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የእርሻና የተፈጥሮ ሃብት ቢሮ አስታውቋል፡፡
በክልሉ 69 ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ለማልማት መታቀዱንም የቢሮው የመስኖ ልማት ዳይሬክተር አቶ ሃይለ ታደለ ተናግረዋል፡፡
ከመስከረም ወር መጨረሻ ጀምሮ በይፋ በተጀመረው የበጋ መስኖ ልማት አትክልት እና የተለያዩ ሰብሎች እየለሙ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በመስኖ ልማቱ 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱንም አስታውቀዋል፡፡
ለበጋ መስኖ ልማቱ 150 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ መቅረቡን የገለጹት ዳይሬክተሩ እስካሁን 19 ሺህ ኩንታሉ ለአርሶ አደሮች መከፋፈሉን አንስተዋል፡፡
በመስኖ ልማቱ ከ228 ሺህ በላይ የክልሉ አርሶ አደሮች፣ ወጣቶች እና ሴቶች ተሳታፊ እንደሚሆኑም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡