የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ዕለት 22 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የተደረገበትንና በአንዴ ከ1 ሺህ 300 በላይ ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚያስችል ለበረራ ሙያ ባልደረቦች የተገነባ ባለ 8 ወለል ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ሕንፃ ለምረቃ አብቅቷል።
ይህ በ48 ሺህ ካሬሜትር ላይ ያረፈ እጅግ ዘመናዊ ሕንፃ በአንድ ዓመት ከአንድ ወር ውስጥ ግንባታው የተጠናቀቀ ሲሆን፤ በውስጡም ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ የሆነ፣ በኤሌክትሪክ ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ የተገጠመለት፣ እንዲሁም ድንገተኛ የእሳት አደጋን መቋቋም እንዲያስችል ተደርጎ በዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ የተገነባ ነው።
ይህ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ሕንጻ ቻይና ጂያንግሱ በሚባል ሕንጻ ተቋራጭ ድርጅት እና K2N አርክቴክቸር እና ኢንጅነሪንግ አማካሪ ድርጅት የተገነባ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የቻይና ጂያንግሱ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሰራተኞች ምቹ የስራ አካባቢ ከመፍጠር ባሻገር የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሟላት በ2ኛ ዙር የቤት ግንባታ ፕሮግራም ለ5 ሺህ ሰራተኞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ እያከናወነ መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ ጠቅሷል።