38ኛውን የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ካለፉት ጊዚያት በላቀ ደረጃ ለማስተናገድ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ
**********************
በአዲስ አበባ ለሚካሄደው የዘንድሮ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ እየተደረገ ያለውን ዝግጅት የተሳታፊ አገራት ቀዳሚ ልዑካን ቡድን አባላት ጎብኝተዋል።
የቡድኑ አባላት በጉብኝታቸው፤ ብሔራዊ ቤተመንግሥት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የክብር ሳሎን፣ አዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን ሴንተር እና የአፍሪካ ሕብረት ዋና መሥሪያ ቤትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል አዚዛ ገለታ (ዶ/ር) ጉብኝቱ ለጉባኤው ኢትዮጵያ እያደረገች ስላለው ዝግጅት ተሳታፊ አገራት በቂ መረጃ እንዲያገኙ ያስችላል ብለዋል።
ለዘንድሮው የሕብረቱ ጉባኤ ኢትዮጵያ በላቀ ደረጃ ዝግጅት በማድረግ የተሳካ መስተንግዶ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ዳይሬክተር ጄነራሏ ተናግረዋል።
በጉብኝቱ የተሳተፉ እንግዶች ኢትዮጵያ ስኬታማ ጉባኤን ለማካሄድ የሚያስችል ዝግጅት ማድረጓን እንደተገነዘቡ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።