👉የብርጭቆ ውኃው ነገር
ሶስት አመለካከቶች አሉ፡-
👉1. ግማሽ ድረስ ውኃ ያለበትን ብርጭቆ በማየት ግማሽ ሙሉ መሆኑ ላይ በማተኮር የሚያመሰግኑ፡፡
የሞላው ነገራችን ላይ በማተኮር ፈጣሪን ስናመሰግንና ለዚያ ነገር መዋጮ ያደረጉትን ሰዎች እውቅና ስንሰጥ ብሩህና የጠራ ምልከታ ስለሚኖረን የጎደለውን የመሙላት አቅም እናገኛን፡፡
👉2. ግማሽ ድረስ ውኃ ያለበትን ብርጭቆ በማየት ግማሽ ጎዶሎ መሆኑ ላይ በማተኮር የሚነጫነጩ፡፡
የጎደለው ነገራችን ላይ በማተኮር ፈጣሪን ስናማርርና ለዚያ እንደዳረጉን ያሰብናቸውን ሰዎች ስንወቅስ ያለንን ጋማሹን እንኳን መጠቀም እስከማንችል ድረስ ጨለምተኞች እንሆናለን፡፡
👉3 ሙሉ ውኃ ያለው ብርጭ ቢያዩም እንኳን ድንገት አንድ ሰው ይደፋዋል ብለው የሚጨናነቁ፡፡
ሁሉ ነገር ሞልቶልን እንኳን ገና ለገና ይሆንብናል እና ይደርስብናል ብለን ስለምናስባቸው ነገሮች የመጨናነቅ ልማድ ካለን አንዱንም ነገር ሳናጣጥመው እንደፈራንና እንደሰጋን ዘመናችንን እናቃጥላለን፡፡
ዋናው ቁም ነገር ያለንና የሌለን ነገር ሳይሆን ባለንም ሆነ በሌለን ነገር ላይ ያለን አመለካከት መሆኑን አትዘንጉ፡፡
ብሩህ ቀን ተመኘሁ!
https://t.me/eec1227