Ethiopian Educational channel


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Образование


እንኳን ደና መጣችሁ
በዚህ ቻናል ላይ የሚያገኙት
1. ትምህርታዊ መረጃ መስጠት
2.የሳይኮሎጂ አስተማሪ ምክሮችንና አነቃቂ ንግግሮች
3.መፃህፍቶች በpdf እና የእንግሊዝኛ ንግግር ይለቀቃሉ!!!
በዚህ ቻናል ሀይማኖታዊ እና ፓለቲካ ነክ አይለቀቅበትም !
https://t.me/EEC1227

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций




         ✏️✏️✏️   የግጥም ቅምሻ✏️✏️✏️
  ዝምታ ወርቅ ነው

መናገርን ፈርቶ ዝምታን የሚመርጥ
ለሰው ጅል መስሎ ብልጥ
እምቅ መልእክት ያለው ከማውራት የሚበልጥ

ሰውን ከማስከፋት ዝምታን መምረጡ
ከመናገር በላይ ምላሽ አለው ውስጡ

ዝምታኮ እንቁ ነው ያስከብራል ደግሞ
ከመሳቅ ይበልጣል በአፍ ሰውን አስታሞ

መናገር ያስታማል ቃላት ካልመረጡ
ያለማስታወል ቃል መርዝ አለው በውስጡ

ታዲያ በዚህ ጊዜ መናገር ሲያስገድል መናገር ሲያሳስር
ዝምታን የመምረጥ ይህ ነው ትልቅ ሚስጥር

ሲናገሩ አስተውል ስማቸው ሚሉትን
ቁም ነገር የሌለው የሃሳብ ብትንትን
ታዲያ በዚህ ጊዜ ዝምታ ወርቅ ነው እላለሁ በየቂን

አታውራ ዝም በል ከመናገር ይልቅ
ባለማውራት በኩል ራስህን ደብቅ

መናገር ካለብህ መልስ ስጥ ለነሱ
በንግግር ምርኮ እንዲለሰልሱ
በሙሉ ትህትና መልስ ስጥ ለነሱ
👉https://t.me/eec1227


Репост из: እንማር
✅ ወርሃ የካቲት እለተ ቅዳሜ 2009 አመሻሽ ላይ ፍፁም ፀጥታ በሰፈነበት ምሽት የምናዘወትርበት መናፈሻ ዉስጥ ቁጭ ብለናል፡፡

እሷም እግሯን ዘርግታመሬት ላይ ኮቷን አንጥፋ እኔም ጭንቅላቴን እግሯ ላይ አስደግፌ የለበስኩትን ሹራብ አንጥፌ በጀርባዬ ተኝቻለሁ ፡፡ አይኖቼን ከእሷ ላይ መንቀል አልቻልኩም፡፡

አንደ ሁል ጊዜዬ ዛሬም አይኗን አሻቅቤ በ ስስት መመልከት ጀምራለሁ፡፡ እሷም እጆቿን ደረቴ ላይ ለጥፋ በምወድላት ፈገግታዋ ታጅባቁልቁል ትመለከተኛል፡፡

ትንሽ ቆየች እና ጣቶቿን ወደ ከዋክብቱ እየጠቆመች “እነዚህ ሁሉ ከዋክብትና ጨረቃ ባይኖሩ ምን
የሚፈጠር ይመስልሀል?” አለችኝ፡፡ ምንም ሳላቅማማ “ድፍንያለ
ጨለማ ይሆናል” ብዬ መለስኩላት….....
,
,
እሷም በ እረጅሙ ከተነፈሰች በሗላ “ውዴ ድፍን ያለ ጨለማ
ቢሆን እንኳ አንተን ከመመልከት አያግደኝም…በዚች ምድር ሳለሁ
ልቋቋመው የማልችለው አጋጣሚ ቢኖር አንተን ካጣሁ ነዉ "
በብላ ፀጉሬን

በጣቶቿ እያሻሸች አዘቅዝቃ አየችኝ ፡፡ እኔም በፍፁም መገረም
እና ደስታ ዉስጥ ሆኜ

“ቆይ… እኔን ብታጪ ምን ትሆኛለሽ?” አልኳት፡፡

ወዲያው እግሮቿን ቀጥ አደረገች እና እጆቿን ደረቴ ላይ ጣል አድርጋ አይኖቿን ጨፍና “አንተን ካጣሁ በህይወት መኖር
አልችልም” አለችኝ ፡፡

ቀን ቀንን ወልዶ ዘመን ተለዉጦ ያ ፍፁም ነዉ ያልኩት ፍቅሯም
ተቀይሮ ይኸው አንተን ካጣሁ እሞታለሁ ያለችኝ ልጅ  ሌላ ሰው አግባታ መኖር ከጀመረች አመታት አለፉ


✅✅@Enmare1988
✅✅@Enmare1988


Learn more !!


🙏🙏🙏Thank you America 🙏🙏
በእውነትም ጥሩ ሀገር ነሽ🌼🌼🌼🌼
አሜሪካ በሰሜን ወሎ ቡግና ወረዳ ለተከሰተው ድርቅ እና የምግብ እጥረት ምግብ እየተላከ መሆኑን አስታወቀች

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ የተከሰተውን ድርቅ እና የምግብ እጥረት ተከትሎ እርዳታ ወደ ስፍራው እየተላከ መሆኑን አስታውቋል።

ኤምባሲው በኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገፁ እንዳስታወቀው በወረዳው እንደተከሰተ ከሰሞኑ እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች ላይ ክትትል አድርጓል።

"የኢትዮጵያ ህዝብን ለመደገፍ አጋሮቻችን ምግብ እና አልሚ ምግቦችን ወደተጠቁት ስፍራዎች እየላኩ ነው" ያለው ኤምባሲው ሁኔታውን በቀጣይም በመከታተል ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚሰራ አስታውቋል።

መሠረት ሚድያን ጨምሮ አንዳንድ ሚድያዎች ከሰሞኑ በሰሜን ወሎ ቡግና ወረዳ ስለተከሰተው ድርቅ ሲዘግቡ ቆይተዋል።

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው እና በርሀብ እጅግ የተጎዱ ህፃናት ምስልም በማህበራዊ ሲዘዋወር ነበር።
@EEC1227


ይህ አዲሱ $DOGS በመባል እየተነገረለት የሚገኘው Paws ኤርድሮፕ ላስጀመራቹ Earn ውስጥ በመግባት In Game የሚለው ውስጥ የተለያዩ ታስኮችን መስራት ትችላላቹ

ለዛም ነጥቦችን ይሰጣቹሃል - ደግሜ የምነግራቹ Tap Tap የሚደረግ ኤርድሮፕ ስላልሆን እቤት ውስጥ በምታገኟቸው ስልኮች በሙሉ አንድ በጀመራቹት አካውንት ወደ ሌላኛው ሊንካቹን እየላካቹ ጀምሩት

ላልጀመራቹ 👉https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=sF0kbzMZ


ትሻሻላለህ፣ ትቀየራለህ!

የአየር ሁኔታውን መቀየር አትችልም ነገር ግን አለባበስህን መቀየር ትችላለህ፣ ችግሮችህን ማስቀረት አትችልም ነገር ግን እራስህን ማበርታት ትቸላለህ፣ ጊዜውን ማስተካከል አትችልም ነገር ግን ከጊዜው ጋር መራመድ ትችላለህ፣ በአንዴ ተነስተህ መንግስት መቀየር፣ አሰራሩን ማሻሻል አትችልም ነገር ግን እራስህን በፈለከው መንገድ መገንባትና ማሻሻል ትችላለህ። ከአቅም በላይ የሆኑ፣ የማንቆጣጠራቸው፣ በእነርሱ ላይ ስልጣን የሌለን፣ እኛ ሳንሆን እነርሱ የሚመሩን ምድራዊ ጌቶችና በእግዚአብሔር ፍቃድ የሚዘወሩ ነገሮች አሉ። ከዚህም አንፃር በእነርሱ ከማማረርና ከመናደድ ይልቅ እራሳችንን መመልከት ይኖርብናል። እውነት ነው ህይወት ከባድ ነች፣ የክብደቷ ልኬት ግን ሚዛኑ በእኛ እጅ ላይ ነው። "ሁሉም ነገር ይቻላል" ሲባል በሰው አቀምና እውቀት የሚገደብ መሆኑንም መረዳት ተገቢ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ቀላሉን መመኘት አቁመህ ለከባዱ መዘጋጀት ስትጀምር፣ ምቾትን መጠበቅ አቁመህ በማይመች ሁኔታ ውስጥ እራስህን ለማመቻቸት ስትጥር፣ ከምታየውና ከምትሰማው በላይ በእራስህ ተስፋ ከተመራህ፣ የአምላክን መልካም ፍቃድ ከጠበክ በእርግጥም ትሻሻላለህትቀየራለህታድጋለህ። ሃሳብና ምኞትህ ሁሉ ገደብ አላቸው፣ ከገደባቸው የማለፍ አቅሙ ግን ይኖርሃል። ማውጣት ማውረዱ፣ ማሰብ ማሰላሰሉ አይቀርልህምና ማድረግ ስለምትችለው ብታስብ፣ መቀየር ስለምትችለው ብታሰላስል ደግሞ ብዙ ነገር የመቀየር እድሉ ይኖርሃል። ከቢሆነ ኖሮ ሃሳብ ተላቀቅ፣ ቅዠት ከተቀላቀለበት ሃሳብ ውጣ፣ ከአቅምህ በላይ የሆኑ ነገሮች ላይ ማተኮር አቁም። ነፃ ፍቃድ አለን ፍቃዳችን ግን በገዛ ፍላጎትና ምርጫችን የተገደበ ነው፤ ማንም የተሰጠው የተለየ ክህሎት አለው፣ የክህሎቱ ውጤት ግን በእራሱ ውሳኔና ተግባሩ ላይ የተመሰረተ ነው።

አዎ! ልክን አውቆ መኖር፣ እንደ አቅም መራመድ፣ የሚችሉት ላይ ማተኮር ትልቅ ስጦታ ነው። ምንም ማድረግ አልችልም ከማለታችሁ በፊት የምትችሉትን ሁሉ ስለማድረጋችሁ እርግጠኛ ሁኑ። ነገሮች ከአቅማችሁ በላይ መሆናቸውን የምታውቁበት ብቸኛ መንገድ ሙከራችሁ ስታዩ ብቻ ነው። እጅን አጣጥፎ ተቀምጦ ከህይወት ክብደት ማምለጥ አይቻልም፤ ንግግርን ችላ ብሎ፣ ለመግባባት ዝግጁ ሳይሆኑ ቀርቶ የሰመረ የፍቅር ህይወት መመስረት አይቻልም፤ እራስን ገድቦ፣ ማንነትን አሳንሶ፣ እራስን ወደኋላ እየገፉ ለውጤት መብቃትና እራስን ማሻሻል አይቻልም። ከአቅምህ ጋር የሚሔድ ምርጫን ምረጥ፣ በመረጥከው ምርጫ ደስተኛ ስለመሆንህ እርግጠኛ ሁን፣ ባሰብከው ሰዓት ያሰብከው ስፍራም እንደሚያደርስህ ተማመንበት።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምንጭ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!


የድግግሞሽ አዙሪት

በየቀኑ እየተነሳችሁ ከቤት ወጥታችሁ በሚኖራችሁ ስምሪት፣ የምትሰሩት ስራ፣ የምትውሉበት አካባቢ፣ የምታገኟቸው ሰዎችና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ከሰለቻችሁና የትም እንደማያራምዳችሁ ካሰባችሁ “የድግግሞሽ አዙሪት” ውስጥ እንዳላችሁ ላስታውሳችሁ፡፡

የድግግሞሽ አዙሪት ምልክቶች፡-

1. ተስፋ መቁረጥ፣

2. ሁሉም ነገር የማስጠላት ስሜት፣

3. ነገሮች እንደማይለወጡ ማሰብ፣

4. ኋላ የመቅረት ስሜት እና የመሳሰሉት ስሜቶች ናቸው፡፡

ከዚህ አዙሪት ለመውጣት መውሰድ የምንችላቸው እርምጃዎች፡-

1. ራእያችን ወይም የሕይወታች ዋና ዓላማ ምን እንደሆነ መለየት፣

2. ከራእያችን አንጻር ወደ አዲስ ነገር ለመግባት መወሰን፣

3. በወሰንነው ውሳኔ ዙሪያ በየእለቱ የሚወሰዱን ትንንሽ እርምጃዎች መጀመር፣

4. የጀመርነውን እርምጃ በፍጹም አለማቆም፣

5. በምክር ሊያግዘን የሚችል ሰውን በመለየት ምክርን መቀበልና የመሳሰሉት ናቸው፡፡


ቀን 09/04/2017 ዓ.ም
የስልጠና ጥሪ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ የቀዳማይ ልጅነትና ዘርፈ ብዙ ጉ/ትግበራ ዳይሬክቶሬት ስልጠና ስለሚሰጥ ከዚህ በታች ስማችሁ የተዘረዘረው የቅድመ 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ዋና ር/መ/ር እና የቅድመ 1ኛ አስተባባሪ ነገ በ10/04/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ገላን ቁ.2 ት/ቤት እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
1  ትንቢተ ኤርሚያስ 
2  የማነብርሃን 
3  ጄ/ዋቆ ጉቱ ቁ.2
4  ቡርቃ ቡሩሩ 
5  ህዳሴ 
6  ጋራ ፉሪ 
7  ጀሞ 
8  አዲስ ተስፋ 
9  ወይራ 
10   አዲስ ህይወት 
11  ጀ/ዋቆጉቱ ቁ 1






ጓደኛ በመጋዝ ዶላር የሚሰጥ ኤርድሮኘ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/FinchAirdropBot?start=529385


ሳያስቡ ከመኖር እያሰቡ መኖር ይሻላል
ሳያምኑ ከመሞት እያመኑ መሞት ይሻላል።
ስለዚህ ሀይማኖት የግል ቢሆንም ሀይማኖት ከሌለው ሰው ሀይማኖት ያለው ይሻላል!@EEC1227


TOP 8️⃣ ትምህርትዎን እና የአጠናን ስልቶን ለማሻሻል የሚረዱ  የተረጋገጡ የጥናት ዘዴዎች💯፡

1️⃣.  የፖሞዶሮ ቴክኒክ⏳ (Pomodoro technique) - የጥናት ክፍለ ጊዜዎን በ25ደቂቃ ልዩነት ⌚ይከፋፍሏቸው ከዚያም አጭር እረፍት ያድርጉ። ይህ ዘዴ ትኩረትን ለመጠበቅ እና ለብዙ ሰአታት በማጥናት የሚመጣን ድካም እና መሰላቸትን  ይከላከላል.💆🏻‍♂️

2️⃣ ንቁ ትዝታ(Active recall)፡- "ማስታወሻዎችን በቸልተኝነት ከመገምገም ይልቅ መረጃን  በማስታወስ እውቀትዎን ለመፈተን ይሞክሩ "። ይህ ዘዴ  ያነበብነው አይምሮአችን ውስጥ ለረዥም ጊዜ እንድቆይ እና ግንዛቤአችንን  ለማጠናከር ይረዳናል.🙋

3️⃣. ክፍተት ያለው መደጋገም(Space Repetition)፡ ይህ ዘዴ የክፍተት ተፅእኖን ይጠቀማል, ይህም መረጃ በጊዜ ልዩነት ውስጥ እንደገና ሲጎበኙ በተሻለ ሁኔታ እንደሚቆይ ይጠቁማል.🙇

4️⃣. የአዕምሮ ካርታ(Mind mapping)🧘🏻‍♂️፡ "ተዛማጅ ጽንሰ-ሀሳቦችን እና ሀሳቦችን የሚያገናኙ ምስላዊ ንድፎችን ይፍጠሩ"። የአእምሮ ካርታዎች መረጃን ለማደራጀት እና የተሻለ ግንዛቤን እና ትውስታን ያመቻቻል።

5️⃣ የኮርኔል ዘዴ(Cornell Method)፡ ማስታወሻዎችዎን በሶስት ክፍሎች ይከፋፍሏቸው፡ 🖇️ለትምህርት ማስታወሻዎች ዋናው ክፍል፣ 🖇️ለቁልፍ ቃላት እና ጥያቄዎች ክፍል እና 🖇️ማጠቃለያ ክፍል። ይህ ዘዴ ንቁ ተሳትፎን እና ውጤታማ ግምገማን ያበረታታል.🔖

6️⃣ ፌይንማን ቴክኒክ(Feynman Technique)👨‍🏫፡-" አንድን ፅንሰ-ሀሳብ ለሌላ ሰው እያስተማርክ ይመስል በቀላል አነጋገር አስረዳ "። ይህ ዘዴ በመረዳትዎ ላይ ክፍተቶችን ለመለየት እና መማርን ያጠናክራል.

7️⃣. ሙከራን ተለማመዱ(Practice Testing)፡ "የተግባር ጥያቄዎችን ወይም ጥያቄዎችን በመጠቀም እራስዎን በማቴሪያል ላይ ዘወትር ይሞክሩ"። ይህ ዘዴ መልሶ ማግኘትን ያሻሽላል እና ተጨማሪ ግምገማ የሚያስፈልጋቸው ቦታዎችን ይለያል።📝

8️⃣. ምስላዊ ምስሎች(Visual Imagery)🤹፡ ከመረጃ ጋር ለማያያዝ የአዕምሮ ምስሎችን ወይም ምስላዊ ምስሎችን ይፍጠሩ። የእይታ ምልክቶች ትውስታን ለማስታወስ እና መማርን የበለጠ አሳታፊ ያደርጉታል።

#️⃣ያስታውሱ💁ሁሉም ሰው የተለያየ የመማር ምርጫዎች አሉት፣ ስለዚህ በእነዚህ ቴክኒኮች ይሞክሩ እና ከግል ፍላጎቶችዎ ውጤታማ በሆነ የጊዜ አያያዝ እና የአደረጃጀት ስልቶች ያዋህዷቸው።


ያልተደራጀ እሳቤ የተዘባረቀ ሕይወትን ይወልዳል

1.  ከዚህ በፊት አስበንባቸው የተውናቸውን ነገሮች እንደገና እያሰቡ በመተው ዑደት ውስጥ መመላለስ፡፡

2.  አንዴ በብርታት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በተስፋ መቁረጥ ስሜት መካከል መዋዠቅ፡፡

3.  የሌሎች ሰዎችን እንቅስቃሴና ስኬት መሰል ተግባር ስንመለከት መነሳሳት፡፡

4.  በነገሮች ላይ እርግጠኛ አለመሆንና መወላወል፡፡

5.  አንድን ነገር ከየት ጀምረን ወደ የት እንደምንወስደው እርግጠኛ አለመሆን፡፡

6.  በሃሳብ ደረጃ የምናውቃቸውን ነገሮች ወደተግባር ለመለወጥ መቸገር፡፡

7.  በአንድ ጊዜ ብዙ ነገር ላይ ለመስራናት ለመለወጥ መሞከር፡፡

ምንጭ:Dr. Eyob Mamo
@eec1227


ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...

👉ምትሰበስቡት ነጥብ ቀጥታ ወደ ቶክን ይቀየራል
👉ፕሮጀክቱ ለጥቂት ግዜ የሚቆይ ስለሆነ አያሰላቻም
👉 አጨዋወቱ እንስሶችን በተሰጣችሁ Feed መመገብና Upgrade ማድረግ ነው
👉ብዙ ሰው ስላልበዛበት በግዜ ብትጀምሩ ይመረጣል

ለመጀመር
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref6759116211


Репост из: Bemnet Library
ራስን ማወቅና መሆን የእውቀቶች ሁሉ መሰረት ነው

"ሶቅራጥስ"

ሰው ማን መሆኑን እስካለወቀ ድረስ ደስተኛ መሆን አይቻለውም

"ፐብሊቢያንስ ሲረስ

ሰው የአመለካከቱ ውጤት ሲሆን ማንነቱም የአመለካከቱ ነፀብራቅ ነው

ዶ/ር ኖርማን ቬሰንት ፔሲ

📚 @Bemnet_Library


እውነት ግን ትወጂኛለሽ፧ ካንጀትሽ ከልብሽ ጓዳ ትተሽኝ አትኮበልዪም፧ ብታመም ወይም ብጎዳ?

እውነት ግን ትወጂኛለሽ?

እውነት ግን ታፈቅሪኛለሽ?

ዘላለም ነሽ ከኔ ጋራ፧ወይንስ ሌላ ታያለሽ?

ተዪው

:

ለመልሱ አትብሰልሰዪ ለመልሱ አትጨነቂ

ሰው እንጂ አምላክ አይደለሽ…

እንኳንስ የዘላለሙን የነገን እንኳን አታወቂ!
❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  𝓑𝓱
                         
                       @  የፍቅር ቃል
                     


Репост из: የፍቅር ቃል ❤️‍🩹
ሰላሜ ልበልሃ
ደስታዬ ልበልሃ
ኩራቴ ልበልሃ
እምነቴ ልበልሃ
ህይወቴ ልበልሃ
የፍቅር እህል ውሃ
የት ደረሰ ስለው አጥቼው ከሌላ
ሊያኗኑረኝ መቷል መውደድ ባንተ ገላ
ከመንፈስህ ገዳም ገባሁ እንደ መና
ካካልህ አልፌ ከነብስህ ልገናኝ

✍🏿Fikreaddis Nekatibeb

🥀🥀🥀
@የፍቅር ቃል
@burakpoem


....እኔ ወድሻለሁ...
እኔ ወድሻለሁ
ታስሮ እንደመፈታት
እንደጣኦስ ውበት
እንደዝሆን ብርታት
ዳዊትን ከጎልያድ
ደርቦ እንደመምታት፤

እኔ ወድሻለሁ
ጦም ውሎ እንደመጉረስ
ወልዶ እንደመታረስ
ቶምቦላ እንደመድረስ
ካላሙዲ ንብረት
ግማሽ እንደመውረስ፤

እኔ ወድሻለሁ

እንደመቅደስ እጣን
እንዳፍለኛ ስልጣን
እኔ ያንች ቡዳ
ያንች ልዝብ ሰይጣን።

    በዉቀቱ ስዩም
             
   @የፍቅር ቃል
  

Показано 20 последних публикаций.