👉ኖህ ሪል ስቴት ከ750 በላይ የመኖሪያ አፓርታማዎችን እና የንግድ ቤቶችን ዛሬ አስረከበ።
ኖህ ሪል ስቴት ከ750 በላይ የመኖሪያ አፓርታማዎችን እና የንግድ ቤቶችን ዛሬ ጥቅምት 16/2015 ዓ.ም አስረከበ።
ሰሚት አከባቢ የተገነባው "ኖህ ኤርፖርት ድራይቭ ሳይት" የተሰኘ ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ለቤት ባለቤቶች የተላለፉት መኖሪያ ቤቶች ከ75 ካሬ አስከ 128 ካሬ ስፋት ያላቸው መሆናቸው በቤት ማስረከቢያ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
ቤቶቹ ከባለ 2 እስከ ባለ 3 መኝታ ክፍሎች ያሏቸው 750 በላይ አፓርታማ የመኖሪያ ቤቶች፣ 32 በላይ ቪላ ቤቶች እና 45 የንግድ ሱቆች ናቸው።
ኖህ ሪልስቴት ዛሬ ያስረከባቸው መኖሪያ ቤቶች መዋኛ ገንዳ፣ የከርሰ ምድር ውሃ እንዲሁም የስፖርት ማዘወተሪያ ያካተቱ መሆናቸው ተጠቅሷል።
የኖህ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ አዋሽ ኖህ ሪል ስቴት ስፋት የመኖሪያ አፓርታማዎችን በጊዜ እና በጥራት በመገንባትና በማጠናቀቅ ኩባንያው የደንበኞቹን እምነት ያተረፈ ኩባንያ ነው ብለዋል።
ኩባንያው በቅርቡ በእንቁላል ፋብሪካ "ኖህ አስኳልን" 750 በላይ መኖሪያ ቤቶችን በአዋሬ ሴቶች አደባባይ "ኖህ ቪክትሪ ሳይት" 152 ቤቶችን ለቤት ባለቤቶች እንደሚያስረክብ ጠቅሷል።
የድርጅቱ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ዘሪሁን በበኩላቸው "አዲስ አበባን ውበት በሚመጥን መልኩ እስከ 2020 ዓ.ም አብዛኛውን የከተማችን ነዋሪዎች ተደራሽ የሚያደርጉና ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው ቤቶች ገንብቶ ለማስረከብ እየሰራን እንገኛለን" ብለዋል።
በቀጣይ ወር በቦሌ ሆምስ በሚባለው አካባቢ ከ5,000 በላይ የሚሆኑ ቤቶችን ግንባታ እንደሚያስጀምሩ ተናግሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ባደረጉት ንግግር በከተማችን ከፍተኛ የሆነ የቤት ፍላጎት አለ ይህ በመንግስት ብቻ ሊሸፈን አይችልም የግል ቤት አልሚዎችን በመደገፍ ለነዋሪው ቤት ፍላጎት መሸፈን አስፈላጊ ነው፣ ዛሬ የተመረቀው የኖህ ሳይት ለከተማችን ቤት ብቻ ሳይሆን ውበትም የሚጨምሩ ናቸው ብለዋል።
ኖህ ሪል ስቴት ባለፉት አስርት ዓመታት በ33 ሳይቶች ከ9,800 በላይ የመኖሪያ ቤቶችን፣ የንግድ ማዕከላትን ከ25,000 በላይ ለሚሆኑ ቤት ፈለጊዎች ገንብቶ አስረክቧል።
@etconp