መስዋዕትነት እስከምን ድረስ?!
መብራት ማጥፋታቸው ሳያንስ (ሆ ሆ ብልሽት ይሁን ምንም ይሁን መብራት ሀይል ሆን ብሎ የሰራው የምናስመስለው ነገር እንዴት እንደሚገርመኝ) እንደልባችን ለኮስ አድርገን የምንጠቀመውም ጋዝ ጠፋ
የምጠላውን ከሰል ለመግዛት ስወጣ ቢታንያ (ሴት ልጄ) ከፀጉር ቤት ስትመለስ ተገናኘን እና አብረን እንግዛ ብያት ተያይዘን ሱቁ ጋር ሄድን።
"የአስር ብር ነው የምፈልገው" አልኩት "መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ የገዛሽው" ሲለኝ ባለሱቁ ሊገዛ የተሰበሰበው ሴት ሳቀብኝ "ኧረ በቅርብ ገዝቻለሁ ምነው?!" አልኩት ውሸቴን "ችርቻሮ ሀያ ብር ከገባ አመት ሊሆነው ነው ብዬ ነው" ሲል ደግመው ሴቶቹ ሳቁ።
"ይሁን የሀያ ብርም ቢሆን ስጠኝ" አልኩት በግዴለሽነት ሻርፔን እያስተካከልኩ ይሄኔ "እማ" አለች ቢታንያ ከጀርባዬ መኖሯንም ረስቼዋለሁ
"አይገርምም ተቃጥሎ ነዶ እንኳን ደግሞ ጠቃሚ መሆን መቻል" አለቺኝ አጠገባችን የተከመረውን ከሰል እያየች "አዪ የልጅ ነገር አይ ቢቱ አሁን ከሰል ብርቅ ሆኖ ነው እንደዚህ የምትራቀቂው" አልኳት ከዛ በላይ አውርታ ድጋሜ እንዳታዋርደኝ ሰግቼ
እሷ እቴ ምኑም አልገባትም "እውነቴን እኮ ነው ይሄ ከሰል እኮ ከመክሰሉ በፊት እንጨት ነበረ ከዛ በፊት ደግሞ ምናልባት ዛፍ ሆኖ ሰዎች ከፀሀይ ተከልለውበታል ጫካ ውስጥ ቆርጠው አንድደውት ሞቀውት ይሆናል አሁን ደግሞ በእሳት ተቃጥሎ እንኳን ደግሞ ለማብሰያ ይሆናል ደግሞ ተቃጥሎ ሲበቃው አመድ እንኳን ሲሆን እቃ የሚያጥቡበት ሰዎች አሉ በተለይ ገጠሩ ላይ"
"ስለዚህ?!" አልኳት ኮስተር ብዬ ደንግጣ ዝም ካለች ብዬ
"እንዴ አልገረመሽም? የሆነ ነገር አልተረዳሽም?!" አለች ገርሟት "ማለቴ ይሄ እንጨትም ሆነ ከሰል ባለፈበት በእያንዳንዱ ደረጃ ጠቃሚ መሆን መቻሉ አይገርምም ከእንጨት ወደ ከሰል ሲቀየር እንደድሮ ጠንካራ አይደለሁም ጠቁሬያሀለሁ በቀላሉ ተሰባሪ ሆኛለሁ ብሎ ጥቅመ ቢስ አልሆነም ከከሰል ወደ አመድም ሲቀየር ዱቄት መሆኑ በነፋስ መበተኑ በሆነ መንገድ ከመጥቀም አላገደውም ምናልባት እኛም ካለንበት ሁኔታ አንፃር ሳይሆን ማድረግ ከምንችለው አንፃር መረዳዳት ብንችል..." አላስጨርስኳትም
"መጥቀሙን ብቻ ነው ያየሽው በመጥቀሙ ውስጥ ራሱን ማጣቱንስ አላየሽም?! እና ራሴን እያጣሁም ቢሆን ለሰው ልጥቀም የሚለው አያሳምነኝም
"ከሰሉን አትወስዱም?!" አለ ባለሱቁ ወገቡን ይዞ
"የወጣንበትን ትተን..." እያልኩ ከሰሉን ገዝተን ተመለስን።
✍ናኒ
https://t.me/justhoughtsss