"ለምንድን ነው የማትወጂውን ወተት አይንሽን ጨፍነሽ የምትጠጭው...."
"አንድ ጓደኛዬ ውስጡ ስላለው nutrient ነግራኝ....".....ሳውቃት ለራሷ እንደነገሩ ነበረች....ካልሞረሞራት አትበላም....በባዶ ሆዷ ውስኪ ስትጨልጥ ለጉበቷ አታዝንለትም ነበር....ፍቅር ከጀመርን በኃላ ነው ስለ organዎቿ አብዝታ መጨነቅ እና መጠንቀቅ የጀመረችው.....
"ቶሎ እንዳላረጅብህ....አሮጊት አገባ እንዳትባልብኝ....".....ስትለኝ እድሜዬን ጠላሁት....የሰባት አመት ታላቄ ናት....እያወቅኩ ነው ያፈቀርኳት......እኔ ስመረቅ ስል እሷ ደግሞ ታናሽ እህቷን ስታስመርቅ ነው የተዋወቅነው....እውነቱን ለመናገር እድሜዋን ካላስታወሰችኝ በቀር ትዝ ብሎኝ አያውቅም....ስሜ እስኪጠፋኝ አፈቅራታለሁ...
አንድ የምፈራው አባባል አለቻት...."ተፈጥሮ ባለጌ ነው....ለወንድ ያደላል....".....ትላለች...."ይብራራ" ብያት ነበረ...
"እድሜያችሁ ሲጨምር ይበልጥ የሚያምርባችሁ ነገር አለ....ያናዳል...."....ብላ ሳቅ አለች....
"አቤት ምቀኝነት....".....አብረን ሳቅን....
"እስከመቼ ትወደኛለህ" ላለቺኝ የመለስኩላት "እስከዘላለም".... ነበር....."እስከዛሬ እስከአሁን እወድሻለሁ" ነው ሚባለው ብላ አረመችኝ እንጂ....
"ነገን አታምኚው....እንዴት አምነሽ ነው የምትጠብቂኝ...."....ብያት አውቃለሁ....
"ተይዤ....".....መልሷ ነው....
እሷን በፍቅር ማሰር...በእሷ መፈቀር ምን ያሀል ደስ እንደሚል....እንደመጠበቅ ያለ እድለኝነት አለ.....?....በመጠበቅ ውስጥ መታመን አለ....መታመን ደግሞ ደስ ይላል...በተለይ በእሷ መታመን....ታምነኛለች....
በሀያ ስምንት አመቴ ድል ባለ ሰርግ አገባኃት...."ታላቁ ሳትሆን አትቀርም....".....ተባለላት....."እናቱን አገባ...."...ተባለልኝ...."አሳድጋው ነው ያገባችው መቼስ....".....ተባለላት...."እንደው ትወልድ ይሆን...."....ያለችው እናቴ ናት....."ለብሯ ብሎ ነው አሉ...."....ያለም አልጠፋም.....እነዚህን ሁሉ ሰዎች በአመቱ ክርስትና ጠራናቸው.....
በድጋሚ ፍቅር ውሎ ይግባ....
✍Shewit
https://t.me/shewitdorkahttps://t.me/shewitdorkahttps://t.me/shewitdorka