ስለሌሎች ስንናገር
ስለኦርቶዶክሳዊ ነገረ ዕውቀት የገባሁትን ቃል አልረሳሁትም። ነገር ግን ይህች ብትቀደም ወደድኩ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ወደ ግሪክ በሔዱበት ወቅት የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የእኛ ፓትርያርክ ቀድሰው አማኞቻቸውን ያቆርቡበት ዘንድ አንድ ቤተ ክርስቲያን በውሰት ይሰጣሉ። የታሰበው አገልግሎት የተፈጸመበትን ይህን ቤተ መቅደስ ግን ግሪኮች ከዚያ በኋላ አልተጠቀሙበትም። እንደተዘጋ ትተውት ቀሩ እንጂ። ይህን ያደረጉበት ምክንያት ደግሞ ኦሪንታል ኦርቶዶክሶች አውጣኪያውያን ናቸው፤ ስለዚህ እነርሱ አርክሰውታል ብለው በማመን ነው። ይህን የሰማሁት የዛሬ 16 ዓመት ወደ ግሪክ ለአገልግሎት ብቅ ባልኩበት ወቅት እዚያው ግሪክ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ነበር።
ግሪኮች ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም ምሥራቅ ኦርቶዶክሶች ስለኦሬንታል ኦርቶዶክሶች የነበራቸው አመለካከት ወይም እምነት ይህ ነበር። ይህ የሆነበት ምክንያትም በ448 ዓ.ም. በአውሳብዮስ ከሳሽነት በፍላብያኖስ ዘቁስጥንጠንያ መሪነት ወደ 40 የሚጠጉ ሊቃነ ጳጳሳት ተሰብስበው ነበር። ክስሱ አውጣኬን ባሕርየ መለኮት ባሕርየ ሥጋን ዋጠው መጠጠው ስለዚህ አንድ ንጥል ባሕርይ (Monophysite) ነው ብሎ አስተምሯል የሚል ነበር። በርግጥ ቀጥታ የተጠየቃቸው ጥያቄዎች ሌሎች ነበሩ። በጉባኤው ላይም አውጣኬ በአካል አልተገኘም ነበር። ላቲኖች እንደሚሉት ከሆነ ያልተገኘው የገዳም አበምኔት እንደመሆኑ መጠን በዓቴን ለቅቄ አልወጣም በማለቱ ነበር። በዚህም ምክንያት ይህን ታምናለህ አታምንም እየተባለ የተጠየቀው በመልእክተኞች ሲሆን መልእክተኞቹም ዮሐንስ የሚባል ቄስ እንድርያስ እና አትናቴዎስ የሚባሉ ዲያቆናት እንደነበሩ መዝግበዋል። እነርሱን ወደዚህ ድምዳሜ የወሰዳቸው ግን ጌታ ሰው ከሆነ በኋላ ሁለት ባሕርይ መሆኑን ታምናለህ? ተብሎ ሲጠይቅ እኔ እንዲህ አልልም ቅድመ ተዋሕዶ እንጂ ደኅረ ተዋሕዶ እንደ ቄርሎስ አንድ ባሕርይ እላለሁ እንጂ ሁለት አልልም በማለቱ እነርሱ ሁለት አልልም አንድ እንጂ ካለ አንደኛው ባሕርይ ጠፍቷል ማለቱ ነው የሚል ትርጉም ራሳቸው ሰልሰጡ ነበር። በዚህም ላይ የጌታ ሰውነት እንደ እኛ አይደለም ብሏል ብለው ዲያቆናቱ የሰጡትን ምስክርነት ይዘው ነበር ያወገዙት፤ እንዳነበብኩት።
አውጣኬ ደግሞ እኔ እንደዚህ ብዬ አላስተማርኩም፤ ያወገዙኝ ያለአግባብ ነው ብሎ ለንጉሡ ቴዎዶስዮስ ካልዓይ ክስ አቀረበ። ንጉሡም የእስክንድርያው ፓትርያርክ ዲዮስቆሮስ ባለበት እንዲታይለት እርሱን በማወገዝ ግንባር ቀደም የነበሩት እና ልዮን፣ ፍላብያኖስ እና ሊሎች አራት ያልህ ደግሞ በዳኝነት በዚህኛው ጉባኤ እንዳይሰየሙ አዘዘለት ። ቅዱስ ዲዮስቆሮስም ሊቃነ ጳጳስት እና ሊቃውንት ተሰብስበው የአውጣኬ ክስሱ እንዲሰማ እና የርሱም መልስ እንዲደመጥ በ449 ዓ.ም. ጉባኤ ጠራ። በጉባኤውም ወደ 127 ጳጳሳትና ሊቃውንት ተገኙ። አውጣኬን እንዲወገዝ ያስተባበሩት እነ አውሳብዮስ ፣ ፍላብያኖስ ግን ቢጠሩም ሳይገኙ ቀሩ። ጉባኤው ግን ተካሔደ። አውጣኬም ተጠየቀ። እርሱም እነርሱ ያወገዙኝ እኔን ብሏል የሚሉትን አላልኩም፤ እኔ አንድ ባሕርይ ነው ብዬ አምናለሁ። እምነቴ ቄርሎስ እንዳስተማረው እንጂ እነርሱ እንደሚሉት አይደለም ብሎ ቃሉን ሰጠ። በዚህ ምክንያት ይህ በቅዱስ ዲዮስቆሮስ የሚመራው ጉባኤ አውጣኬን ከግዝቱ ፈታው።
በዚህ ጊዜ ቀድመው ያወገዙት ሰዎች ዲዮስቆሮስ አውጣኬን ከግዝቱ የፈታው ራሱ ዲዮስቆሮስ እንደ እርሱ ቢያምን ነው ብለው ማስወራት ጀመሩ። እንዲያውም ልዮን ይህን ጉባኤ የሚጠራው ጉባኤ ፈያት እያለ እንደነበር ጽሑፍ ማንበቤን አስታውሳለሁ። አስወርተውም አልቀሩ የ451ዱ ጉባኤ ኬልቄዶን እንዲጠራ እና ሀሳቡ እንኳ በአግባቡ ሳይደመጥ ዲዮስቆሮስ እንዲወገዝ ተደረገ። በዚህ ምክንያት እስከቅርብ ጊዜያት አንዳንዶቹም እስካሁን ድረስ ኦሬንታሎቹን አውጣኬያውያን እንደሆንን ያምናሉ። የሚያስገርምም የሚያሳዝንም ነገር ነው።
አንዳንዶች ሀሳባቸውን በታወቀ መንገድ መቀየር እና ማስተካከል የጀመሩት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ (አሁን ዩኒቨርሲቲ) የመጀመሪያው ዲን የነበሩት ሕንዳዊው V.C. Samuel የተባሉት ሊቅ ለሦስተኛ ዲግሪ መመረቂያ ጥናታቸው መጽሐፍ ሆኖ ከታተመ በኋላ ነበር። የኒህ አባት መጽሐፍ “the Council of Chalcedon Re-Examined” – ‘ጉባኤ ኬልቄዶን እንደገና ሲመረመር’ በሚል ርእስ በሠሩት ጥናት ላይ ይህን ንጥል አንድ ብቻ ባሕርይ /monophysite/ የሚለውን እንኳን ዲዮስቆሮስ ሊቀበለው ይቅርና አውጣኬም ስለማለቱ ማረጋገጫ አላቀረባቸሁም። እርሱ ያላለውን ብሏል ብላችሁ አወገዛችሁት እንጂ እርሱ እንዲህ ነው የማምነው ብሎ ልክ አርዮስ፣ ንስጥሮስ፣ መቅዶንዮስ እንዳደረጉት አልተከራከረም ፤ ሀሳቡንም አላስረዳም። እርሱ እናንተ የምትከስሱበትን ለማለቱ ማስረጃ የላችሁም። አላልኩም ፤ እኔ የማምነው እንደ ቄርሎስ ነው ስለማለቱ ግን ማስረጃ አለ። ኦሪነታሎች አንድ ባሕርይ የሚለውን የምንጠቀመውም በተዋሕዶ እንጂ እናንተ እንደምትሉን ሞኖፊሳይት አይደለንም፤ አይመለከተንም፤ ይህን ለማረጋገጥ ከፈለጋችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስሟን ብቻ ብትመለከቱ ይበቃችኋል። ተዋሕዶ የሚለውን የስሟ መጠሪያ አድርጋዋለችና የሚለውን ሀሳብ በሰፊ ጥናት ካሳዩ በኋላ ብዙ ሊቃውንቶቻቸው ስለኦሬንታሎች ያላቸውን የተሳሳተ አመለካከት አስተካክለዋል።
በቅርብ ጊዜ ደግሞ የእኛው ቀሲስ ዶክተር መብራቱ ኪሮስ የማስተርስ ጥናቱን በዚህ ዙሪያ በመሥራት የኦሬንታሎቹ እምነት ምሥራቆቹ እንደሚሉን እንዳልሆነ ጥሩ አድርጎ አስረድቷል። የቀሲስ ዶክተር መብራቱ ትኩረቱ ታሪኩ ላይ ሳይሆን ቀጥታ ነገረ እምነታችን ወይም ዶክትሪኑ ላይ ነው። የቀሲስን ጥናት የፈለገ “Miaphysite Chrystology: An Ethiopian Perspective” በሚል ረእስ አፈላልጎ ማግኘት እና ማንበብ ይቻላል። እነዚህን ሁለቱን እንደምሳሌ አነሣሁ እንጂ ሌሎችም ይኖራሉ።
ይህም ሆኖ ብዙዎች ገዳማውያኑ እና ዓለም አቀፍ ጥናቶችን ለማወቅ ወይም እኛን ኦሬንታሎችን ቀርበው እምነታችንን በትክክል ያልተርዱት ግን እስካሁን ድረስ እኛን የሚያዩን አውጣኬያውያን አድርገው ነው። እንዲያውም አንድ ወንድም እንደ ነገረኝ በአቶስ ተራራ (Mount Athos) የኖሩት እና አሁንም ያሉት በኃይለኛ ምናኔ እና ብቃት የሚመሰገኑት የግሪክ ኦርቶዶክስ አባቶች እስካሁን ድረስ ኦሬንታሎችን አጥፋ የሚል ጸሎት ሁሉ አላቸው ብሎ ነግሮኛል። እኔም ራሴ ባለፈው ዐሥር ዓመት ውስጥ አሜሪካን ሀገር ያለ አንድ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መካነ ድር ላይ የአውጣኬን እምነት የያዙ ቤተ ክርስቲያኖች አሁንም አሉ፤ ለምሳሌ የኮፕቲክ እና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብሎ ጽፎ አንብቤ እንዴት በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ሰዎች በቀላሉ መረጃ በሚያገኙበት እንዲህ ትጽፋለህ ብዬ ጽፌለት ጽሑፉን የጻፈው ቄስ ይቅርታ ጠይቆ አስተካክሏል።