በአዲስ አበባ ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ አካባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ‼️
በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ አካባቢ ዛሬ ሌሊት 10:35 ሰዓት አካባቢ በመኖሪያና ንግድ ቤቶች ላይ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማዋ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
በእሳት አደጋው በሰውና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት እንዲሁም የአደጋው መንስዔ ተጣርቶ እንደሚገለጽ ኮሚሽኑ አስታውቋል።
አደጋ የደረሰበት ስፋራ በከተማ ደረጃ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብለው ከተለዩ የመኖሪያና የንግድ አካባቢዎች አንዱ መሆኑ ተጠቁሟል።
ቤቶቹ የተገነቡበት ግብዓት፣ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታው እንዲሁም ቦታው የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎችን ለማስገባት ምቹ አለመሆኑ የእሳት አደጋው እንዲሰፋ ምክንያት መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቅሷል።
እሳቱን ለመቆጣጠር የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች፣ የጸጥታ አካላት፣ የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸውም ተገልጿል።
@Esat_tv1