✅#_የነብያት_ታሪክ ✅
〰🍃#_ነቢየሏህ_ሱለይማን_ዐለይሂ_ሰላም〰🍃
ክፍል4⃣7⃣
ዳዉድ ከሞተ በኋላ ዙፋኑን የዳዉድ ልጅ የሆነው ጥበበኛው እና ብልሁ ሱለይማን ወርሶታል።ግዛቱንም በጥሩ ሁኔታ በማስተዳደር ላይ ይገኛል።
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ ከእለታት አንድ ቀን ሱለይማን እጁን ወደ ጌታው በመዘርጋት፦"ጌታዬ ሀፅያቴን ይቅር በለኝ።ከኔ በኋላ ለሚመጣ ትውልድ በሙሉ የማይገባ የሆነንንም ንግስናን ስጠኝ" በማለት ተመፀነ።
አላህም ለያንዳንዱ ነቢያት ዱዐቸውን እንደሚቀበለው ሁላ የሱለይማንንም ዱዓ አላህ ተቀብሎት፤ ንፋስን ሱለይማን ወደሚያዘው መንገድ እንዲነፍስ፣ሰይጣናትንም በሱለይማን ቁጥጥር ውስጥ አድርጓቸው እሱ ያዘዛቸውን እንዲፈፅሙ፣ ግዴታ አደረገባቸው።
በመቀጠልም የወፎችን እና የእንስሳቶችንም ቋንቋ በሙሉ አሳወቀው።ሱለይማንም አላህ በሰጠው ወደር የለሽ ፀጋ አላህን አመሰገነው።
ከእለታት አንድ ቀን ሱለይማን ወታደሮቹን(ሰይጣናትን፣ጂኒዎችን፣ ሰዎችን...ብዙ እንስሳቶችን) ሰብስቦ በመጓዝ ላይ ሳለ አንዲት ጉንዳን ለሌሎች ጉንዳኖች፦"እናንተ ጉንዳኖች ሆይ !!! ሱለይማን እና ወታደሮቹ እየመጡ ነው። ሳያውቁ በእግሮቻቸው እንዳይጨፈላልቋችሁ፤ ወደየቤታችሁ ግቡ" በማለት ስትናገር ሰማት።
ይሄን ሲሰማ ሱለይማንም ፈገግ አለ'ና፦"ጌታዬ ሆይ! ያቺን በእኔና በወላጆቼ ላይ የለገስካትን ጸጋህን እንዳመሰግን እና የምትወደውንም በጎ ሥራ እንድሠራ ምራኝ፡፡ በችሮታህም በመልካሞቹ ባሮችህ ውስጥ አግባኝ" አለ።
ሱለይማን ሰራዊቶቹን ከሰበሰበ በኋላ የቀሩትን ማጣራት ጀመረ።ሁሉም መጥቷል ግን አንድ ሁድሁድ የተባለ ወፍ አልታየው ከዚያም፦"ሁድሁድ ለምን አይታየኝም!!! ወይስ ራቅ ብሎ ሄዶ ነው? ብርቱን ቅጣት በእርግጥ እቀጣዋለሁ፡፡ ወይም በእርግጥ ዐርደዋለሁ፤ ወይም ግልጽ በኾነ አስረጅ(ምክንያት) ይመጣኛል"አለ።
ከዚያም በማግስቱ ሁድሁድ መጣ'ና ሱለይማን ፊት ቆመ።ሱለይማንም የት እንደነበር ሲጠይቀው ሁድሁድ፦"እኔ ሰበእ የሚባል አካባቢ ሄጄ ነበር።አንድ ሁሉ ነገር የተሟላላትንም ንግስት አገኘሁ፣ትልቅ የሆነም ዙፋን አላት።
ነገር ግን እሷንም ሆነ ህዝቦቿን ለአላህ መስገድ ሲገባቸው ለፀሀይ ሲሰግዱ ተመለከትኳቸው" አለው።
ሱለይማንም፦"እስቲ ይህን ደብዳቤ ይዘህ እሷ ዘንድ ወስደህ ጣለው።ከዚያም ራቅ ብለህ ምን እንደሚከሰት ተመልከት።እውነት እንደተናገርክ እና እንደዋሸህ እናያለን" አለው
ሁድሁድም የሱለይማንን ደብዳቤ ይዞ ወደ ሰበእ ምድር ይከንፍ ጀመር። ልክ የሰበእን ምድር እንደረገጠ ወደ ንግስቲቱ ቤተ መንግስት በመግባት ንግስቲቱ ፀሎት ላይ ባለችበት ሁኔታ ሱለይማን የላከውን ደብዳቤ ጣለላት።
ንግስቲቱም ፀሎቷን አጠናቅቃ ቀና ስትል ይህን ደብዳቤ መሬት ላይ ወድቆ አገኘችው።ደብዳቤውንም ከፍታ ስታነበው፦"ይህ ከሱለይማን የሆነ መልዕክት ነው።በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤ በእኔ ላይ አትኩሩ፡፡ ታዛዦችም ኾናችሁ ወደኔ ኑ!" የሚል መልዕክት አነበበች።
ይህን መልዕክት እንዳነበበችውም ወዲያው አማካሪዎቿን እና የጦር መሪዎችን በመሰብሰብ ስለጉዳዩ አማከረቻቸው።እነሱም ጉዳዩ ካዳመጡ በኋላ፦"እኛ የበርካታ ወታደሮች ባለቤት ስንሆን ከባድ ጉልበትም አለን። መብቱ ያንች ነው የፈለግሽውን እዘዢን እኛ እንፈፅመዋለን" አሏት።
እሷም፦"ንጉሶች አንድን ከተማ ገብተው ከወረሩ ያን ከተማ እንዳልነበረ አድርገው ያበላሹታል።የከተማይቱንም የተከበሩ ነዋሪያንን ያዋርዳሉ። ስለዚህ እኔ አገልጋዮቼን በርካታ ስጦታዎችን አስጭኜ ወደ ንጉስ ሱለይማን ዘንድ እልካለሁ።ከዚያም ስጦታውን የወሰዱት አገልጋዮች በምን እንደሚመለሱ አያለሁ" ብላ በመወሰን የአማካሪዎቿን ሀሳብ ውድቅ አደረገች።
በማግስቱም የንግስቲቱ አገልጋዮችም የተጫነላቸውን የስጦታ መዐት ጭነው ብዙ ከተጓዙ በኋላ የሱለይማንን ግዛት ሲገቡ በሚያዩት ነገር ሁሉ በጣም ተደመሙ።
ልክ ከተማዋን እንደደረሱም የጫኑትን ስጦታዎች እየነዱ ወደ ሱለይማን ቤተ መንግስት ገቡ።ሱለይማንም ስጦታውን እንደተጫነ መልሱላት ብሎ እሷ እና ህዝቦቿ በአላህ የማያምኑ ከሆነ መቋቋም የማይችሉትን ወታደር አሰልፎ እንደሚመጣባቸው መልዕክት ላከ።
ስጦታውን ያመጡት መልዕክተኞች ስጦታውን ይዘው ከቤተ መንግስት ግቢ ልክ እንደወጡትም ሱለይማን ሰራዊቶቹን ሰብስቦ፦"እናንተ መኳንንቶች ሆይ! ንግስቲቱ እና የንግስቲቱ ህዝቦች ሙስሊሞች ኾነው ሳይመጡኝ በፊት የንግስቲቱን ዙፋን እዚህ የሚያመጣልኝ ማንኛችሁ ነው" ሲል ተናገረ።
በስብሰባው ጂኖች...ሸይጣኖች...ብዙ ፍጥረታት ነበሩ'ና አንድ በጣም ሀይለኛ ጂን ቆመ'ና፦"አሁን ቁጭ ካልክበት ዙፋን ከመነሳትህ በፊት እኔ ሰበእ ሄጄ የንግስቲቱን ዙፋኑን ላምጣልህ፤ እኔም ታማኝ እና ሀይለኛ ነኝ" አለው።
አንድም የአላህን ስሞች ሁሉንም ጠንቅቆ የሚያውቅ እና ዱዓው ሙስተጃብ የሆነ ሰውዬ በመሀከላቸው ብድግ አለ'ና ለሱለይማን፦"እኔ አይንህ ከመርገብገቡ በፊት ዙፋኑን ፊትህ አስቀምጥልሀለሁ" አለ'ና ሱለይማን የአይኑን ቆብ ዘግቶ እስኪከፍት ድረስ የንግስቲቱ ዙፋን ፊትለፊቱ ቁጭ ብሎ አገኘው።
ሱለይማን ይሄን ሲመለከት፦"ይህ ከጌታዬ ችሮታ ነው፡፡ የማመሰግን ወይም የምክድ መኾኔን ሊሞክረኝ (ቸረልኝ)፡፡ ያመሰገነም ሰው የሚያመሰግነው(ጥቅሙ) ለራሱ ነው፡፡ የካደም ሰው ጌታዬ ከእርሱ ተብቃቂ ቸር ነው" በማለት ጌታውን አመሰገነ።
ከዚያም ሱለይማን ጂኖችን፦"ባህር ላይ መስታወት በማንጠፍ እዚያ መስታወት ላይ ይሄን ዙፋን አስቀምጡበት" አላቸው።ጅኖችም በሱለይማን ትዕዛዝ መሰረት ባህር ላይ መስታወት በማንጠፍ ዙፋኑን መስታወቱ ላይ አስቀመጡት።
ንግስቲቱ የሱለይማንን ግዛት ገብታ የግዛቱን ስፋት እየተመለከተች በጣም ተገረመች።በመጨረሻም ሱለይማን ንግስቲቱን ከተቀበላት በኋላ ባህር ላይ ወዳስገነባው ቤተ መንግስት በመውሰድ፦"ያንች ዙፋን እንዲህ አይነት ነው?" አላት።
እሷም፦" አዎን ልክ እራሱን ይመስላል" አለችው።
እሱም፦"በይ ሂጂ ዙፋንሽ ላይ ቁጭ በይ" አላት።
እሷም መስታወት መሆኑን አላወቀችም ባህሩን ብቻ አይታ ዙፈኗ ጋ ልትሄድ ልብሶቿን ወደ ላይ ስትሰበስብ ሱለይማንም፦"ባህሩ እኮ አንችን አያገኝሽም ይህ ባህር ከላዩ መስታወት ተነጥፎለታል። ሂጂ ግቢ" አላት።
ያን ግዜ ንግስቲቱ ሱለይማን ነቢይ እንጂ ተራ ንጉስ አለመሆኑን በመረዳት፦"ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ፡፡ ከሱለይማንም ጋር ሆኜ ለዓለማት ጌታ ለአላህ ታዘዝኩ" አለች።
ከዚያም ሱለይማን በንግስና ሆኖ ብዙ አመታትን ኖረ።ሱለይማን አንድ ባህሪ አለው..እሱም አንድ ቦት ሲሰግድ ከአቅራቢያው አንድ ችግኝ ከተመለከተ፦ስምሽ ማን ነው?" ይላታል።
ችግኋም፦" እኬሌ" ብላ ስሟን ትነግረዋለች።
ሱለይማንም፦" ለምንድነው የተፈጠርሽው?" ሲላት
ችግኟም የተፈጠረችለትን አላማ ትነግረዋለች።
ከእለታት አንድ ቀን ሱለይማን ሰግዶ ቁጭ ባለበት አንዲትን ችግኝ
ተመለከተ'ና፦.......
ክፍል 4⃣8⃣ ኢንሽዓሏህ
ይ.......ቀ.......ጥ......ላ......ል፡፡
የነብያት ታሪክ ብቻ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ይሄን ቻናል ሸር በማድረግ ላልደረሳቸው በማድረስ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን
👉 @yenebyat_tarik
👉ሌለኛው ቻናላችን👉 @eslamic_dawa
👉ግሩፖችን👉 @eslamicdawa