የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአዳማ ከተማ በጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት መከላከል ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ
አዳማ ፤ ታኅሣሥ 25/2017 ዓ.ም (ኢ.መ.ብ.ባ)
ባለሥልጣኑ በአዳማ ከተማ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለተውጣጡ ሰልጣኞች በጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት መከላከል፣ በመሰረታዊ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባርና መርሆዎች፣ በሃቅ ማጣሪያ መንገዶች እና በሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ዙሪያ ነፃ ሰልጠና ሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የስትራቴጅ ጉዳዮች አቅም ግንባታ መሪ ስራ አሰፈፃሚ ወ/ሮ የሺወርቅ ግርማ፤ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ የተሻለ እንዲሆን ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ጥናትና ምርምሮችን ከማድረግ ጀምሮ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ስልጠናው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት መከላከል እንዲሁም በሃቅ ማጣሪያ መንገዶች ላይ ግንዛቤያቸውን በማሳደግ ኃላፊነትን የተላበሰ የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት በመፍጠር የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ያለመ እንደሆነ አያይዘው ገልፀዋል።
አስተያየታቸውን የሰጡን ሰልጣኞች በበኩላቸው፤ የጥላቻ ንግግርንና ሐሰተኛ መረጃን ለመከላከል የሚያስችል ስልጠና መሰጠቱ ጥሩ እንደሆነ በመግለፅ የስልጠናውን ተደራሽነት ማስፋት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸውልናል።
በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ የጥላቻና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭቶችን ለመከላከል የሁሉም ርብርብ እንደሚያስፈልግም ሰልጣኞቹ ጨምረው ገልጸዋል።
👉 በመገናኛ ብዙኃን እና በማስታወቂያ ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ በ9192 ነፃ የስልክ መስመር ደውለው ማሳወቅዎን አይርሱ፡፡