በኃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ለሥርጭት የሚቀርብ ማንኛውም ኘሮግራም የሚከተሉትን ማክበር ይኖርበታል፡-
• ሕገ መንግስቱን፣ የመገናኛ ብዙኃን አዋጁን እና ሌሎች የሀገሪቱን ሕጎች ማክበር ይኖርበታል፣
• በኃይማኖት ተከታዮች መካከል የእርስ በእርስ ግጭት ማነሳሳት፣ የሌሎችን ኃይማኖታዊ አስተምሮ ወይም እምነት ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ ማንኳሰስ ወይም በሀይማኖት ተከታዮች መካከል አለመቻቻል እንዲፈጠር መቀሰቅስ ወይም የሃይማኖት እኩልነትን መፃረር የለበትም፣
• ማንኛውም የሰው ዘርን፣ ቋንቋን፣ ብሔርን፣ ኃይማኖትን ወዘተ መሰረት በማድረግ የወንጀል ድርጊት እንዲፈጸም፣ ሰላምና ፀጥታ እንዲደፈርስ መቀስቀስ የለበትም፣
• ከማህበረሰቡ ባህልና ሥነ ምግባር የተቃረነ፤ የማህበረሰቡን ጤና የሚጎዳ፣ ማህበረሰቡን በሀሰት የሚያሳስት ይዘት ማሰራጨት የለበትም፣
በመገናኛ ብዙኃን እና በማስታወቂያ ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ በ9192 ነፃ የስልክ መስመር ደውለው ማሳወቅዎን አይርሱ፡፡
#ብቁ_መገናኛ_ብዙኃን_ለማህበረሰባዊ_ንቃት
#የጥላቻ_ንግግርና_ሐሰተኛ_መረጃን_በጋራ_እንከላከል
የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይጎብኙ፦
ድረ ገጽ
www.ema.gov.etፌስቡክ
https://www.facebook.com/ethiopian.media.authority/ኤክስ (X)
https://twitter.com/ethmediaauth?lang=enሊንክዲን
https://www.linkedin.com/in/ethiopian-media-authority-711169219?utm_source=share&utm_campaign=share_via&utm_content=profile&utm_medium=android_app