ፕሬዚዳንት ፑቲን በዩክሬን የኃይል መሰረተ ልማት ላይ ጥቃት እንዳይፈጸም ትዕዛዝ ሰጡ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው አቻቸው የሩሲያ-ዩክሬንን ጦርነት ማስቆም በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ረጅም የስልክ ውይይት ከሦስት ዓመታት ጦርነት በኋላ በኃይል እና በሌሎች መሠረተ ልማቶች ላይ የሚደረጉ ጥቃቶችን የሚያስቆም ከፊል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ተስማምተዋል።
ይህን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ፑቲን በዩክሬን የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት እንዲቆሙ ወዲያውኑ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ከክሬምሊን የወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሜር ዜሌንስኪ በበኩላቸው ሩሲያ የኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ የምታደረገውን ጥቃት ማቆሟን አሜሪካ ካረጋገጠች ዩክሬንም በ30 ቀናት የተገደበ ተመሳሳይ እርምጃ እንምትወስድ ተናግረዋል።
ፑቲን እና ትራምፕ ባደረጉት ውይይት በቀጣይም በባሕር ላይ የሚደረገው ጦርነት የሚቆምበትን መንገድ ለመፈለግ በመካከለኛው ምሥራቅ የተጀመረውን ድርድር ለመቀጠል መስማማታቸውን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል፡፡
ክሬምሊን በዩክሬን ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ለኪዬቭ የሚደረገው የውጪ ወታደራዊ እና የመረጃ ድጋፍ ሙሉ በመሉ መቆሙ ቁልፍ ቅድመ ሁኔታ ነው ብሏል።
የሁለቱ ሀገራት የወደፊት ግንኙነት “በርካታ የኢኮኖሚ ስምምነቶችን” እንዲሁም ከሰላም ጋር ተያይዞ ጂኦፖለቲካዊ መረጋጋትንም ያስገኛል ሲል ኃይት ሀውስ አስታውቋል።
@Ethiopiafastnews