ኢትዮ ፈጣን ዜና - Ethio Fast News 🇪🇹


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Спорт


የሀገር ውስጥ እና ውጪ ዜናዎችን በፍጥነት እና በጥራት የሚያገኙበት ቻናል
Ethiopian Fast news 24/7

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Спорт
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: PERFECT ስፖርት በኢትዮጵያ™
🇪🇺የዩኤፋ ኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎች

⏰እረፍት

🇺🇦 ዩክሬን 0-➊ ቤልጅየም 🇧🇪
🥅ሉካኩ

🇳🇱 ኔዘርላንድ ➊-➊ ስፔን 🇪🇸
🥅ጋክፖ 🥅ኒኮ ዊልያምስ

😀 ጣልያን ➊-0 ጀርመን 🇩🇪
🥅ቶናሊ

🇭🇷 ክሮሽያ ➋-0 ፈረንሳይ 🇫🇷
🥅ቡድሚር
🥅ፔሪሲች

🇩🇰 ዴንማርክ 0-0 ፖርቹጋል 🇵🇹

😀 ኮሶቮ ➊-➊ አይስላንድ 😀
🥅ዴሎቫ 🥅ኦስካርሰን

😀 ቡልጋርያ ➊-➋ አየርላንድ 😀
🥅ፔትኮቭ 🥅አዛዝ
🥅ዶሀርቲ

😀 ስሎቫኪያ 0-0 ስሎቬንያ 😀

😀 ግሪክ 0-➊ ስኮትላንድ 🏴󠁧󠁢󠁳󠁣󠁴󠁿
🥅ማክቶሚናይ

🇦🇹 ኦስትሪያ ➊-0 ሰርብያ 🇷🇸
🥅ግሪጎሪች

@Perfect_sport_et
@Perfect_sport_et


Репост из: Profile picture
🚨✅ ቤቲንግ መበላት ላማረራችሁ ጥሩ TIP የምታገኙበት ቻናል ተከፍቷል አሁኑኑ ተቀላቀሉ👇

https://t.me/+7ZOmNi9fCxg2ZDc0
https://t.me/+7ZOmNi9fCxg2ZDc0


Репост из: Add Best ➊ & ➋
💔 ️የተወለዱበትን ወር ቶሎ ይምረጡ እና በ Zodiac ሳይንስ ስለራስዎ በደንብ ይወቁ 😍😍😍 የፍቅር ሁኔታዎንም ይጠቁማል
👏 100% ትክክል የሆነ ✅

Add your channel 10k+➾ @promotion_k7




ነገር ግን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለፉት ሁለት ዓመታት ተጨማሪ ጦርነትን በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ ስራ አከናውነዋል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሰጠው የሁለት ዓመት ጊዜ በማለቁ የህግ ማሻሻያ የሚፈልግ ጉዳይ አለ። ህግ ሲሻሻል ደግሞ የነበሩ አፈጻጸሞች መገምገም አለባቸው።

በዚህም የፕሪቶሪያውን ስምምነት ባከበረ መልኩ መጠነኛ ለውጥ ከተካሄደ በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስራውን እያከናወነ ህዝቡን ለምርጫ የሚያዘጋጅ ይሆናል።

ይህን በተመለከተም ከጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶች እየተደረጉ ነው። በዚህ ሂደት ስራዎች ተገምግመው የግለሰቦች መቀያየር ሊኖር ይችላል። "

@Ethio_fastnews
@Ethio_fastnews


🚨ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ፕሪቶሪያ ስምምነት ምን አሉ ?

" ስራዎች ተገምግመው የግለሰቦች መቀያየር ሊኖር ይችላል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፦ " የፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረተ ልማቶችን በመመለስ የትግራይ ህዝብ አገልግሎት እንዲያገኝ አድርጓል ፤ ያም ሆኖ አሁንም በበቂ ሁኔታ ያልተፈጸሙ ጉዳዮች አሉ።

ከዚህም አንደኛው የታጣቂዎች ተሃድሶ (ዲዲአር) ስራ ነው። ይህ በዋናነት የሚጎዳው የትግራይ ህዝብን ነው። ወጣቶች በታጣቂ ስም ከመቀመጥ ወደ ልማት መሰማራት አለባቸው። በየወሩ ለልማት መዋል የነበረበት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለዚህ ስራ ይወጣል። 

ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው በመመለስ ረገድም በራያና ጸለምት ጥሩ ስራ ተከናውኗል። በሌሎች አከባቢዎች ግን በተፈለገው ልክ አልሆነም። ይህ የሆነውም ሰብዓዊ ስራ እና ፖለቲካ የሚቀላቅሉ ኃይሎች በመኖራቸው ነው።

@Ethio_fastnews
@Ethio_fastnews


🚨" የባህር በር ጥያቄን ማንሳት ነውርነቱ አቁሟል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ ለቀይ ባህር ስትል ኤርትራን የመውረር ፍላጎት እንደሌላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ፍላጎት እንነጋገር፣ ሰጥቶ በመቀበል መርህ፣ ህዝቦች በሚጠቀሙበት መርህ እንወያይ የሚል ነው ብለዋል።

የኤርትራ ህዝብ የሚያስፈልገው ልማት ነው፣ ተባብረን መልማትና መስራት እንጂ አንዱ አንዱን መውጋት የእኛ እቅድ አይደለም ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ ላይ ማንም ሀገር ወረራ ሊፈጽም እና ከጀመርነው ህልም ሊያስቆመን ይችላል የሚል ስጋት የለብንም ብለዋል፡፡

በቂ ዝግጅት ስላለን ማንም አያስቆመንም፣ ዝግጅት የምናደርገውም ጦርነትን ለማስቆም ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

የባህር በር ጥያቄን ማንሳት ነውርነቱ አቁሟል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አቋምም በዓለም ላይ ትልቅ ሀገር ሆኖ የባህር በር የሌለው የለም ስለሆነም በሰጥቶ መቀበል መርህ ሊሆን ይገባል የሚል ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ አጀንዳ ለመስጠት የመጣ ሳይሆን ባለፉት ዓመታት ትኩረት የተሰጠው እና በመደመር መጽሐፍ ላይ የተካተተም ነው ብለዋል፡፡


@Ethio_fastnews
@Ethio_fastnews


የእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን (መጋቢት 11/2017 ዓ.ም)

@Ethio_fastnews
@Ethio_fastnews


🚨NGAT

የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ብሔራዊ የመግቢያ ፈተና (NGAT) ነገ መጋቢት 12/2017 ዓ.ም ከጠዋት 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ይሰጣል፡፡

ፈተናው በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚገኙ የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከል በምትሔዱበት ወቅት የመፈተኛ User Name እና Password እንዲሁም ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

በምዝገባ ወቅት ፕሪንት ያሉትን ፎቶዎን በግልፅ የሚያሳይ Test Admission Ticket (TAT) መያዝም አይዘንጉ፡፡

ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከመጀመሩ 30 ደቂቃ በፊት በፈተና ማዕከል መገኘት የሚጠበቅበት ሲሆን፤ ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዞ በፈተና ማዕከል መገኘት ፈፅሞ የተከለከለ ነው፡፡

@Ethio_fastnews
@Ethio_fastnews


Репост из: PERFECT ስፖርት በኢትዮጵያ™
ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎች !

🇪🇺በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር

04:45 |⚽️ ክሮሺያ ከ ፈረንሳይ 🇫🇷
04:45 |🇳🇱 ኔዘርላንድ ከ ስፔን 🇪🇸
04:45 |🇩🇰 ዴንማርክ ከ ፖርቹጋል 🇵🇹
04:45 |😀 ጣልያን ከ ጀርመን 🇩🇪

🌍 በአለም ዋንጫ ማጣሪያ (አፍሪካ)🌍

10:00 |🇲🇿 ሞዛምቢክ ከ ዩጋንዳ 🇺🇬
01:00 |🇸🇱 ሴራሊዮን ከ ጊኒ ቤሳው 🇵🇬
01:00 |🇿🇼 ዚምባቡዌ ከ ቤኒን 🇧🇯
01:00 |🇨🇻 ኬፕ ቨርዴ ከ ሞውሪሽየስ 🇲🇺
01:00 |🇲🇼 ማላዊ ከ ናሚቢያ 🇳🇦
04:00 |🇱🇾 ሊቢያ ከ አንጎላ 🇦🇴
04:00 |🇬🇦 ጋቦን ከ ሲሼልስ 🇸🇨
04:00 |🇬🇲 ጋምቢያ ከ ኬንያ 🇰🇪

@Perfect_sport_et
@Perfect_sport_et


Репост из: PERFECT ስፖርት በኢትዮጵያ™
ትናንት የተደረጉ ጨዋታዎች

🌍በአለም ዋንጫ ማጣሪያ (አፍሪካ )🌍

🇸🇿 ኢስዋቲኒ 0-0 ካሜሮን 🇨🇲

🇱🇷 ላይቤሪያ 0-➊ ቱኒዝያ 🇹🇳

🇨🇫 ሴንትራል አፍሪካ ሪበፕሊክ ➊-➍ ማዳጋስካር 🇲🇬

🏆በሴቶች የአውሮፓ ሻምፕዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ

🇩🇪 ወልፍስበርግ ➊-➍ ባርሴሎና 🇪🇸

🇬🇧 ማንችስተር ሲቲ ➋-0 ቼልሲ 🇬🇧

@Perfect_sport_et
@Perfect_sport_et


አዲስ የመዳበሪያ ፋብሪካ በቀጣዩ አመት እንደሚከፈት ተገለፀ፡፡

የመዳበሪያ አቅርቦት ችግርን ለመፍታት በሚቀጥለዉ ዓመት የመዳበሪያ ፋብሪካ በኢትዮጵያ እንደሚከፈት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ የማዳበሪያ ፋብሪካ ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተባበር ይከፈታል ብለዋል፡፡

ከግሉ ዘርፍ ጋር መክፈት ካልተቻለ መንግስት ብቻውን ይህን በሚቀጥለዉ ዓመት እዉን ያደርገዋል ሲሉ ለምክርቤቱ አባላት አስታዉቋል፡፡

ኢትዮጵያ ከፍተኛ ወጪ በማዉጣት በገፍ በየዓመቱ ከዉጭ ከምታስገባቸዉ መካከል የአፈር መዳበሪያ አንዱ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጲያ በቀን 150 ሺ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ከውጭ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ 24 ሚለየን ኩታል ገደማ የአፈር ማደበሪያ እንደ ሀገር ያስፈልገናል ብለዋል፡፡

በቀን 1መቶ ሃምሳ ሺ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባው በምላሻቸው ገልጸዋል፡፡

ይህ ብቻም አይደለም ለእያንዳንዱ አርሶ አደር በወታደር አጅበን እናደርሳለን ፤ ታዲያ ይህ ሁሉ ችግር የሚፈታው የማዳበሪያ ፋብሪካ ሲፈከት ነው ብለዋል፡፡

@Ethio_fastnews
@Ethio_fastnews


ኢትዮጵያ አሁን ያላት የመጠባበቂያ ገንዘብ በታሪኳ ይዛው አታውቅም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህንን ያሉት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት የ 100 አመታት ታሪክ ውስጥ እንደ አሁን መጠባበቂያ /RESERVE/ ገንዘብ ይዛ አታውቅም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካማክሮ ኢኮኖሚው በኋላ በነበራት ድርድር በእዳ ሸግሽግ 3.5 ቢለዮን ዶላር ገዳማ እዳ ሽግሽግ ማግኘቷንም ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ስምንት ወር ከ564 ቢሊዮን ብር ገቢ ተደርጓል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሁን እንጂ ሰፋፊ ድጎማዎች እና የደሞዝ ጭማሪ በማደረጋችን ወጪያችን ከገቢያችን በልጧል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መጠባበቂያ ውስን ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም በ2011 ዓ.ም ኢትዮጵያ ከነበራት ወይም መጠባበቂያ የአሁኑ በእጥፍ ሆኗል ብለዋል፡፡

ባለፉት ዘመናት ጀምረን ለማንጨርሳቸው ፕሮጀክቶች የተበደርነውን ብድር አግባብ አይደል በሚል የእዳ ሽግሽግ ማደረጋቻንም ገልጸዋል፡፡

ነዳጅ ማዳበሪያ ለክልሎች የሚሰጥ በጀትን ተደማምሮ ገቢያችን ሙሉ ለሙሉ ወጪያችን ባይሸፍንም እየሞከርን ነው ብለዋል፡፡

ኑሮ ውድነቱን ለማርገብ የተለያዩ የመፍትሄ መንገዶችን እየተጠቀመች ነው ይህም እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው ተናግረዋል፡፡

@Ethio_fastnews
@Ethio_fastnews


ኢትዮጲያ ከአፍሪካ አንደኛ ስንዴ አምራች ሀገር ሆናለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ዛሬ መጋቢት 11 2017 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ በተለይ የኢትዮጲያን ግብርና በሚመለከት ካነሱት፤- በሀገሪቱ ከ 7.7 ሚለየን ሄክታር በላይ የስንዴ ሰብል ተሸፍኗል፡፡

በዚህም 3መቶ ሚለዮን ኩታል ምርት ይጠበቃል፡፡ኢትዮጲያ ከአፍሪካ አንደኛ ስንዴ አምራች ሀገር ሆናለች፡፡

ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታ የማታውቀውን እድገት በዚህ ስምንት ወር አስመዝግባለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ሰንዴ ብቻ አይደለም በሌሎች ሰብሎች ውጤታማ ሆነናል፤ በተለይ ለውጡን ተከትሎ በቡና ፤ በሻይ በቅባት እህሎች ውጤታማ ሆነናል ፡፡

በቡና ምርት በተለይ ለውጡን ተከትሎ በዓመት 7 መቶ ሚለየን ዶላር ገደማ ዶላር በዓመት ኤክስፓርት ስናደርግ ቆይተናል፡፡

ባለፈው ዓመት 1.4 ቢለየን ዶላር ቡና ኤክስፓርት ተደርጓል፡፡በዘንድሮ ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት ከ 1.2 ቢለየን ዶላር በላይ ኤክስፓርት አድርገናል፡፡

በሚቀጥሉት አራት ወራት ውስጥ 2 ቢለየን ዶላር ቡና ኤክስፓርት እናደርጋለን ብለዋል፡፡

ኢትዮጲያ ውስጥ ያለው የቡና ኤክስፓርት ውጤታማ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቡና ላይ ስር ነቀል ውጤት መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ እና ምላሹች አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡

@Ethio_fastnews
@Ethio_fastnews


በሀገሪቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በዲጂታል የመመዝገብ (School Mapping) ሥራ ጀምረናል። - ትምህርት ሚኒስቴር

ከሕዝብ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፤ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በሙሉ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ማፕ የማድረግ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በዚህም ትምህርት ቤቶቹ በሚገኙባቸው አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች ብዛትን በማየት የት ነው ትምህርት ቤት መገንባት የሚያስፈልገው የሚለውን በደረጃ ለይተናል ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

በ School Mapping ፕሮጀክቱ አማካኝነት የተጎዱ እንዲሁም ትምህርት ቤት በጣም የሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ተለይተው፥ ዝርዝር እየወጣ መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ ሙሉ ለሙሉ ሲተገበር የትምህርት ቤት አቅርቦት ለሁሉም በእኩል ለማዳረስ ያስችላል ብለዋል።

@Ethio_fastnews
@Ethio_fastnews


📣በጎዳና ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ነጋዴ የሚል ደረት ላይ የሚንጠለጠል ፈቃድ ሊሰጣቸው ነው፡፡

ህጋዊነታቸውን ተከትሎም የሚጠበቅባቸውን #ግብር እንዲከፍሉ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መደበኛ ያልሆነን የንግድ ሥራ ለመምራትና ሥርዓት ለማስያዝ በሚል ባወጣው ደንብ ከዚህ ቀደም ህገወጥ ናችሁ ተብለው ይዋከቡ ለነበሩ ነጋዴዎች ፍቃድ እንዲሰጥ ደንግጓል፡፡

በዚህም መሰረት ማንኛውም በጎዳና ንግድ ላይ የተሰማራ ግለሰብ በሚሰራበት አቅራቢያ ባለ ወረዳ በመሄድ ተመዝግቦ ደረት ላይ የሚንጠለጠል ፍቃድ ማግኘት አለበት ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ላይ የሚሰማራ ነጋዴ በዚህ ደንብ መሰረት ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነት ያገኛል፡፡

የበጀት ዓመቱ ካበቃ በኋላ ባሉት 2 ወራት ጊዜ ውስጥም ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ እስከ ነሀሴ 30 ቀን ድረስ የግብር አስከፋይ መስሪያ ቤቱ ግብሩን ወስኖ እንዲከፍሉ ያደርጋል፡፡

የተሰጠውን ፍቃድ በየዓመቱ ማደስ እንደሚኖርበትና ከስራው ሲወጣም ለሰጠው አካል የመመለስ ግዴታ እንዳለበት ተቀምጧል፡፡

ይህ ደንብ ከየካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል ተብሏል፡፡

@Ethio_fastnews
@Ethio_fastnews


ከምሽቱ 3 ሰአት ተኩል በፊት የንግድ ተቋምን መዝጋት 10 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ደንብ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 አንቀጽ 94 መሰረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡

በደንቡ መሰረት በአዲስ አበባ ንግድ ቤቶች እና ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች እስከ ምሽት ሶስት ተኩል እና አራት ሰዓት አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለባቸዉ፡፡

በተጨማሪም በምሽት ክፍለ ጊዜ የመግቢያ በሩን ዝግ በማድረግ አገልግሎት የሚሰጥ ከሆነ፤የንግድ ተቋሙ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን የሚያሳይ በመብራት የሚሰራ ምልክት በግልጽ በሚታይ ቦታ ላይ ማስቀመጥ እንደሚኖርበት በደንቡ ላይ ሰፍሯል ፡፡

ይህን ደንብ በመተላለፍ የንግድ ተቋሙን ከ 3 ሰአት ተኩል በፊት የዘጋ ለአንድ ጊዜ የጥፋት መጠን የ 10 ሺህ ብር ቅጣት ይጠብቀዋል ተብሏል ፡፡

በተጨማሪም ከምሽቱ 4 ሰዓት በፊት የትራንስፖርት አገልግሎት ማቋረጥ፣ከስምሪት መውጣት አልያም የስምሪትን መስመር ማቆራረጥ 5 ሺህ ብር እንደሚያስቀጣ ተገልጿል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ካወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ በላይ ተሳፋሪውን ማስከፈልም በተመሳሳይ የ 5ሺህ ብር ቅጣት እንዳለዉ ነዉ የሰማነዉ፡፡

@Ethio_fastnews
@Ethio_fastnews



Показано 18 последних публикаций.