የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን ለመምራት ዕጩ የሚሆኑ ግለሰቦችን የሚያቀርብ ኮሚቴ ተቋቋመ
የስራ ዘመናቸውን ከአራት ወራት ገደማ በፊት አጠናቅቀው የተሰናበቱትን የህዝብ ዋና ዕንባ ጠባቂ የሚተኩ ዕጩዎችን የሚያቀርብ ኮሚቴ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተቋቋመ።
▶️ በኮሚቴው ውስጥ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እና የጌዲኦ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ጌህዴድ) የፓርላማ ተመራጮች እንዲካተቱ ተደርጓል።
▶️ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፤ በህግ የተደነገጉ የሰዎች መብቶች እና ጥቅሞች በአስፈጻሚ አካላት መከበራቸውን በማረጋገጥ፤ የህግ የበላይነትን መሰረት ያደረገ መልካም የመንግስት አስተዳደር እንዲሰፍን የማድረግ ዋና ዓላማ ያለው ነው። ተቋሙ የቀረቡለትን የአስተዳደር በደል አቤቱታዎች መሰረት በማድረግ፤ “ስልታዊ ምርመራ” የማካሄድ ኃላፊነትም በአዋጅ ተሰጥቶታል።
▶️ይህን ተቋም ላለፉት ስድስት ዓመታት በኃላፊነት ሲመሩ የቆዩት ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ናቸው። ዶ/ር እንዳለ በድጋሚ ተሹመው፤ ለተጨማሪ ስድስት ዓመታት በኃላፊነት መቀጠል የሚችሉበትን ዕድል የተቋሙ ማቋቋሚያ አዋጅ ቢሰጣቸውም፤ ከዋና እንባ ጠባቂነታቸው መሰናበትን መርጠዋል።
▶️ ያገለገሉበት የስራ ዘመን “ከበቂ በላይ” መሆኑን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተናገሩት ዶ/ር እንዳለ፤ “አሁን ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ምቹ ባለመሆኑ እና ነጻ እና ገለልተኛ ሆኖ ለመስራት አስቸጋሪ” ስለሆነ በኃላፊነት ላለመቀጠል መወሰናቸውን አስረድተዋል።
▶️ ለስራቸው ይከፈላቸው የነበረው ደመወዝ አነስተኛ መሆን፤ በዋና እንባ ጠባቂነት ለሁለተኛ ዙር ላለመሾም ካስወሰኗቸው ምክንያቶች መካከል እንደሚገኝበትም ገልጸዋል።
🔴 ለዝርዝሩ:- https://ethiopiainsider.com/2024/14549/