ከኦሮሚያ ክልል ለሀገራዊ ምክክር የሚቀርቡ አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ሂደት ከነገ ጀምሮ ሊካሄድ ነው
ከኦሮሚያ ክልል በሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ላይ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ሂደት ከነገ ሰኞ ታህሳስ 7፤ 2017 ጀምሮ ለተከታታይ ስምንት ቀናት ሊካሄድ ነው።
በዚሁ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ላይ ስምንት ሺህ የሚጠጉ የማህበረሰብ ክፍል ወኪሎች እና የክልል ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።
በአዳማ ከተማ የሚካሄደው ይህ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት፤ በሀገራዊ ምክክር የተዘጋጁ ተመሳሳይ መድረኮችን ቁጥር 12 ያደርሰዋል። የኦሮሚያ ክልል በወረዳ እና በዞን ብዛቱ “ከፍተኛ ቁጥር” ያለው መሆኑ፤ የአሁኑን የምክክር መድረክ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት የተለየ እንደሚያደርገው ተገልጿል።
በአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረኩ ላይ በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ 356 ወረዳዎች በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉ ተሳታፊዎች እንደሚገኙ፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ዛሬ እሁድ በአዳማ ከተማ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
🔵 ዝርዝሩን ይህን ሊንክ ተጭነው ያንበቡ:- https://ethiopiainsider.com/2024/14606/
@EthiopiaInsiderNews