ትልቁ ኃጢአት
በሰው ልብ የተተከለው ትልቁ ጠላት ትእቢት Pride ነው። ትልቁ ኃጢአት ትእቢት። ትእቢት ራስን ከፍ አደርጎ የማየት፣ ሌላውን የማሳነስ፣ ለእኔ የተሻለው ይገባኛል፣ ሌላውን መናቅ ነው። የሌላው ሕመም የማይገባው፣ የወንድሙ ሳይኾን የራሱ ጥቅምን ብቻ የሚያሰላ ነው።
ትእቢት ሰው አእምሮውን እያገኘ አዕምሮ እያደገ በመጣ ቁጥር ከመሠረቱ በትንሹ እየበቀለች የምትሄድ ናት። አንዲት ቅንጣት ኾና እንደ ዛፍ ተተክሎ ብዙ ቅርንጫፍ ዘርግቶ ሌሎች አስፈላጊ እጽዋትን እንደሚገድል ዛፍ አይነት ነው። በሰው ሕይወት ውስጥ ትእቢት የተለያየ መገለጫ አለው።
ይነስም ይብዛም የትእቢት ተክል የሌለበት የለም። እንደ ጥንካሬው እየገደላት እያቀጨጫት ፈጽሞም ያሸነፋትም ይኔራል። አንድ ጊዜ አንዱን ረድእ አበምኔቱ አንተ ትእቢት አለብህ አሉት። እሱም አባቴ በፍጹም ትእቢት የለብኝም አላቸው። በል ተወው ራስህ ተናገርክ አሉት። ትእቢት የለብኝም ብሎ መናገር በራሱ ትእቢት መኾኑን አስተማሩት።
የትእቢት መገለጫው አጫፋሪዎቹ ብዙ ናቸው። የተሽቀረቀረ (ፋሽን) አለባበስ፣ ተኳኩሎ ተውቦ መታየት፣ በሌላው በጓደኛው ዘንድ የተሻለ መስሎ መታየት፣ ልጅ በሌላቸው ፊት ልጅ መኖሩ የተባረከ አስመስሎ ማውራት፣ ከሌላው ይልቅ የተማረ መኾኑን ማሳየት፣ የትእቢት መልኬቹ ብዙ ናቸው። ድምጼ አናረልኝ ብሎ ሲዘባነን ማየት፣ ተማርኩ ብሎ አፋን በነጠላ ሸፍኖ ሌላውን የጎሪጥ ማየት፣ ማሽሟጠጥ የመሳሰሉት ኹሉ የትእቢት ቅርንጫፎች ናቸው።
የማያምኑ የማይጾሙ የማይጸልዩ ሰዎች ስናይ እኛ የተለየ ቅድስና የተሻለ ለእግዚአብሔር ቅርብ የኾንን፣ ከመሰለን ትእቢት ነው። ብዙ ሰው ትእቢት በምን መልክ እንደ በቀለችበት አያውቅም። ስለዚኽም ትእቢቱን እየተንከባደበ ያሳድጋታል።
አንጀቱ እስኪቆስል ቢጾም፣ ጉልበቱ እስኪላጥ ቢሰግድ፣ እንደ ጊዮርጊስ ብንጋደል፣ ትእቢት እስካለበት ድረስ አይጠቅሙትም። ጽድቅ ያለ ትኅትና አይጠቅምም።
“ጎልያድ በዳዊት ላይ ታበየ ነገር ግን ለውሻ በሚወነጨፍ ትንሽ ደንጊያ ሞተ። ትሑቱ ዳዊት ግን ለእርሱና ለዘሩ እስከዘለዓለሙ ነገሠ። ትሕትና ከትእግስት ይወለዳልና።” ርቱዓ ሃይማኖት
ትልቁ ምግባር ትኅትና Humility ነው። “ትኅትና ማለት ክፉ ላደረገብህ በጎ ስታደርግለት ነው።” ይላል። ዜና አበው 146
ትኅትና ኹሉም ከእኔ ይሻላል ብሎ ማሰብ ነው። ሌላውን ማስቀደም ነው። ትኅትና እስከ መጨረሻው መውረድ ነው። ምንም ሳይኖርኽ ድሃ ነኝ ብትል ትኅትና አይደለም። ምንም ስለሌለኽ ነው። ኖሮኽ እንደሌለኽ ኾኖ ማሰብና መኖር ነው። ክርስቶስ አምላክ ነው። አምላክነቱ ግን በሰዎች መናቅን አላስቀረውም። እመቤታችን የእኛን በደል አልተካፈለችም፣ ሰው አልሰደበች አልተመቀኘች ፣ ገንዘብ አልተበደረች ግን ተሰድባለች፣ ተገፍትራለች። ጸሎቷም
“የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል” አለች። ሉቃ.1:48
እኛን ያዋረደ ኃጢአት ሳይኔርባት በእግዚአብሔር ፊት ራሷን እንደ ባርያ ዝቅ አደረገች። ባርያ የራሱ ፈቃድ የለውም። የጌታው ነው። እመቤታችን እግዚአብሔር ፈቃድን በምልዓት የፈጸመባት ኪዳኑ ናት። ከፍጥረት በላይ ኾና ራሷን ዝቅ ያደረገች፣ የትኅትና አስተማሪያችን ናት።
አድርገኽ እንዳላደረግኽ ስታስብ፣ ሰጥተኽ እንዳልሰጠኽ ስታስብ፣ ጠቅመኽ እንዳልጠቀምኽ ስታስብ የትኅትናን መንገድ ጀምረሃል።
ንዋይ ካሳሁን