መግለጫ ወጥቷል‼
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ዛሬ በአዲስ አበባ የሁለትዮሽ ምክክር አድርገዋል።
ከውይይቱ በኃላ የጋራ መግለጫ ወጥቷል።
📌 በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
📌 በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል ያለውን ወንድማማችነትና ግንኙነት በማጠናከር ላይ ገንቢ ውይይት አድርገዋል።
📌 የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ወደነበረበት ለመመለስ እና በየመዲኖቻቸው ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ውክል እንዲኖር ለማድረግ ተስማምተዋል።
📌መሪዎቹ ለቀጣናው መረጋጋት የሁለቱ ሀገራት የጋራ የእርስ በርስ እምነት ፣ መተማመን እና መከባበር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ትብብር እንደሚያስፈልግ አረጋግጠዋል።
📌 ቀጠናዊ ግንኙነቶችን ለማሻሻል፣ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር እና የጋራ እድገትን ለማስቀጠል በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።
📌 መሪዎቹ የጸጥታ ትብብር ማስቀጠልና ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል። በቀጠናው ፅንፈኛ ታጣቂ ሃይሎች እየፈጠሩ ያሉትን አሳሳቢና እየጨመሩ ያሉ ስጋቶችን በመገምገም መሪዎቹ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የሚደረገውን ትብብር ለማጠናከር ለጸጥታ ተቋሞቻቸው መመሪያ ለመስጠት ተስማምተዋል።
📌 በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ማጠናከር ያለውን ጠቀሜታ ላይ ተወያይተዋል ፤ አጽንኦትም ሰጥተዋል። የበለጠ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ትብብር በማድረግ የንግድ ልውውጥን ለማሳለጥ እና የጋራ ብልጽግናን ለመፍጠር የመሰረተ ልማት ትስስሮችን ለማስፋት ተስማምተዋል።
📌 ለአንካራው ስምምነት በጓደኝነት እና በአብሮነት መንፈስ ቁርጠኝነታቸውን ዳግም ያረጋገጡ ሲሆን በስምምነቱ ላይ የታቀዱትን የቴክኒክ ድርድሮችን ለማፋጠንም ተስማምተዋል።(ቲክቫህ)
#እውን_መረጃ