የሰሞኑ የንግድ ባንክ ክስተት❗️የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ግለሰብ ሁለት ሰዎችን ገድሎ ራሱን እንዳጠፋ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ተነግሯል።በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ካርል አደባባይ አካባቢ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አንድ ግለሰብ ሁለት ሰዎችን ገድሎ ራሱን እንዳጠፋ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ተነግሯል።
ክስተቱ ያጋጠመው ትናንት ማክሰኞ መጋቢት 02/2017 ዓ.ም. ሲሆን፤ ለሦስት ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ሁኔታ የተፈጠረው 'የፍቅር ጥያቄዬ ምላሽ አላገኘም' በሚል ምክንያት መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
አቶ ሽፈራው ረጋሳ የተባለ የባንኩ የጥበቃ ሠራተኛ ለሥራ ባልደረባው የፍቅር ጥያቄ አቅርቦላት ምላሽ ባለማግኘቱ ግለሰቧን እና ከግለሰቧ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለው በሚል የጠረጠረውን ሌላ ባልደረባውን በመግደል ራሱን እንዳጠፋ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
ግለሰቡ የፍቅር ጥያቄ ያቀረበላት ወይዘሪት ሃና ተስፋዬ የተባለች 32 ዓመት ወጣት እና አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የተባለ የሥራ ባልደረቦቹን በጥይት ተኩሶ የገደለው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ እንደገለጹት ወንጀሉን የፈፀመው የጥበቃ ሠራተኛ ካልተራው ሌላ ሠራተኛን ተክቶ በመግባት እና ከምሽት የጥበቃ ሠራተኞች የጦር መሳሪያ በመቀበል ግድያውን ፈፅሟል።
ግለሰቡ ግድያውን የፈጸመው ተጠርጣሪው ወደ ዕለታዊ ሥራቸው እስኪገቡ ድረስ በመጠበቅ መጀመሪያ አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የተባለውን ግለሰብ በሁለት ጥይት መትቶ መግደሉን ኮማንደር ማርቆስ ገልጸዋል።
ግድያው ማክሰኞ መጋቢት 2/2017 ዓ.ም. ጠዋት ከአንድ ሰዓት ተኩል እስከ ለሁለት ሰዓት ሩብ ጉዳይ ድረስ ባላው ጊዜ ውስጥ መፈፀሙን የተናገሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ቃል አቀባይ፤ በሁለቱ ግድያዎች መካከል እስከ 15 ደቂቃ የሚሆን የጊዜ ክፍተት እንደነበረ አመለክተዋል።
ግድያውን የፈጸመው ግለሰብ ባልደረባውን ተኩሶ ከገደ በኋላ ሌላኛዋን የጥቃቱ ሰለባን ከመግደሉ በፊት ከድርጊቱ እንዲቆጠብ መጠየቁን ነገር ግን ፈቃደኛ እንዳልነበረ ተገልጿል።
ግለሰቡ መሳሪያውን እንዲያስቀምጥ እና እጁን እንዲሰጥ በተደጋጋሚ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦለት የነበረ ሲሆን፣ በዚህ መካከልም ወደ ባንኩ አንደኛ ፎቅ በማምራት የፍቅር ጥያቄውን አልተቀበለችም ያላትን በተመሳሳይ ሁኔታ በጥይት መትቶ መግደሉን ፖሊስ ገልጿል።
ግለሰቡ ሁለቱን ባልደረቦቹን ከገደለ በኋላ በያዘው መሳሪያ የእራሱንም ሕይወት እንዳጠፋ የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለቢቢሲ ገልጸው በክስተቱ በአጠቃላይ የሦስት ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል።
ሁለቱ ሟቾች ወ/ሪት ሃና ተስፋዬ እና አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የፍቅር ግንኙነት እንደነበራቸው የሚጠቁም ፎቶግራፎች መገኘታቸውን የጠቆሙት ኃላፊው፤ ፖሊስ በምርመራው ስለግንኙነታቸው እንደሚያጣራ ገልፀዋል።
ከዚሁ ክስተት ጋር በተያያዘ ፖሊስ እያካሄደ ያለውን የምርመራ ሂደት እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ቢቢሲ ስለ ግድያው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኃላፊዎችን ለማነጋገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም።
Via: ቢቢሲ
@Ewun_Mereja@Ewun_Mereja