🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟
⭐️ክፍል 🟰1️⃣0️⃣
ከሆስፒታል ወጣሁ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ምን እንደማስብ አላውቅም ።
ብቻ መንገድ ላይ ግራ ተጋብቼ ስጓዝ ልዑሌ ደወለ ገና ስልኬ ላይ ስልኩ ሲጠራ እደነግጣለሁ ድምፁን ስሰማ የውስጤ ጭንቀት ሁላ ነው ሚጠፋው: ስልኩን ሳየው ፈገግ እንዳልኩ እንኳን ሳይታወቀኝ ፈገግ እላለሁ :
ስልኩን አንስቼ ሄሎ አልኩት እንዴት ነሽ የኔ ቀውስ ምነው ጠፋሽ ለመናፈቅ ባልሆነ አለኝ እየሳቀ ::
ወይ መናፈቅ እያልኩ በውስጤ ለመረሳት ነው እንጂ አልኩት አይ አንቺማ እንዴት ትረሻለሽ እሺ ዛሬስ አንገናኝም እንዴ ? ሲለኝ በጣም ነው የደነገጥኩት ምክንያቱም በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ እሱን ማየት አልችልም እንዴት ብዬ ነው አይኑን የማየው በሌላ በኩል ደግሞ ቢያንስ አይኑን ባየው ሰላም እንደሚሰማኝም አቃለሁ እሺ በቃ ከፈለክ አሁን ከፈለክ ማታ ካፌ ሳልጨርሰው አይ አሁን ይሻላል እስካሁን ምሳ አልበላሁም እሺ የት እንገናኝ አለኝ ::
አንተ ደስ ያለህ ቦታ በቃ ሰፈር ጠብቂኝ እና መጥቼ እወስድሻለሁ ብሎኝ ስልኩን ዘጋው::
የተለመደችው ቦታዬጋ ሄጄ ቁጭ አልኩኝ መጮህ ማልቀስ ተመኘሁ ግን አቅም አነሰኝ ።።
እናቴ እኔን በድህነት አሳደገችኝ እኔ ደሞ ልጄን በድህነት ላሳድገው ነው ?እንደዛ የለፋችልኝ እናቴ ለስራዋ ምከፍላት ይሄንን ነው 😢 እዛ ትንሽ ከተቀመጥኩ ማበዴ ስለማይቀር ተነስቼ እስከ አስፋልቱ በእግሬ መራመድ ጀመርኩ።
ትንሽ እንደተራመድኩ ማክቤል ከሆነች ልጅጋ ተቃቅፈው እየተሟዘዙ ከፊት ለፊቴ መጡ ሳየው ደሜ ነው የፈላው ሄጄ ባንቀው ደስ ይለኝ ነበር ።
ልጅቷ የባለፈዋ ልጅ መስላኝ ነበር ግን አይደለችም ሌላ ናት ልክ ሲያየኝ አንዴ ይስማታል አንዴ ያቅፋታል ብቻ የሚያደርጋትን ነበር ያሳጣው እኔ አንገቴን ደፍቼ ወደፊቴ መራመዱን ተያያዝኩት
አነሱም እኔን እየተከተሉ በሚመስል መልኩ ፍጥነታቸውን ጨምረው ተራመዱ አጠገቤ ሲደርስ ሰላም ነው ሰላሚና አለኝ እያገጠጠና እያፌዘ መልስ ሳልሰጠው ወደፊቴ ሄድኩ።
ትንሽ እንደተራመድኩ ልዑሌ ደውሎ እንደደረሰና እየጠበቀኝ እንደሆነ ነገረኝ ቶሎ ቶሎ ወደፊት መራመድ ጀመርኩ ልክ አስፋልቱጋ ስደርስ ልዑሌ መኪናውን አቁሞ ከመኪናው ወርዶ እየጠበቀኝ ነበር ሲያየኝ ፈገግ አለና ወደኔ መቶ አቀፈኝ ሲያቅፈኝ የሚነዝረኝ ነገር ነው ማይገባኝ ኤሌትሪክ ይዞ የሚዞር ይመስል።
እውነት ለመናገር ስላየሁት በጣም ነው ደስ ያለኝ ግን ፊቴ አሁንም እንደተዘፈዘፈ ነው እጄን ይዞኝ ወደ መኪናው ሊያስገባኝ እያለ የድሮ ፍቅረኛሽን ቦዲይ ጋርድነት ቀጠርሽው እንዴ አለኝ እየሳቀ
ማለት አልኩት ግራ ገብቶኝ እና ለምንድነው ከኋላ ከኋላሽ የሚከተልሽ አለኝ ዞር ስል አቶ ማክቤል 2 እጁን ኪሱ ከቶ ከኋላዬ እየተከተለኝ ነበር እንዴ ጉድ ፈላ ልጅቷን ምን ውስጥ ከተታት አሁን አብራው አልነበረች እንዴ ለራሴም ጥያቄ ፈጠረብኝ ቢሆንም ከልቤ ነበር የሳኩት ልዑሌ የመኪናውን በር ከፍቶልኝ በክብር ካስገባኝ ቡሀላ ወደ መኪናው ገባ።
ማክቤል ቆሞ እያየኝ ነበር በውስጤ እሰይ ቅጥል በል እያልኩኝ እየሳኩ ሳየው ነበር መኪናው መቀሳቀስ ሲጀምር ማክቤልም ተንቀሳቀሰ የትን የምንሄደው አልኩትን ልዑሌን በቀዘቀዘ ድምፅ የት መሄድ ትፈልጊያለሽ ደስ ያለሺን ቦታ ምረጪ አለ አይ አንተ ደስ ያለህ ቦታ ከቻልክ ብቻችንን የምንሆንበት ቦታ ቢሆን ደስ ይለኛል ምሳ ከበላን ቡሀላ የምነግርህ ነገር አለኝ አስቸኳይ ነው አልኩት ።
እና ለምንድነው ድምፅሽ የቀዘቀዘው ዛሬ የደበረሽ ነገር አለ እንዴ ነገሩስ አስቸኳይ ነው እንዴ በጥያቄ ሲያጣድፈኝ እሱን ስነግርህ ታቀዋለህ መጀመሪያ ምሳውን እንብላ መቼስ በጣም እርቦሀላ ......
🔻ክፍል አስራ አንድ ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 @FEGEGTA_BCHA 💔
💔 @FEGEGTA_BCHA 💔
💗የፍቅር ማዕበል💗