“ይሔን ሰው ስትመረምሩ ተጠንቀቁ! እንዳይፅፍባችሁ" አለ የምርመራውን ቢሮ አንኳኩቶ ከፍቶ የገባው የደህንነት ሰው፡፡ ሥፍራው ማዕካላዊ ነበር፡፡ ኮማንደር ተኽላይ መብራህቱ ቢሮ። ኮማንደር ተኽላይ መብራህቱ ማን እንደነበር ምን አሳወቃችሁ?! እሱ የፀረ ሽብር ዲቪዥን ዋና አዛዣ አልነበረምን? እናም አንኳኩቶ የገባው የደህንነት ሰው በቁሙ በለቀቀው ወሬ የመርማሪዎቹ ትኩረት በአንዴ ወደሱ ተሳበ፡፡ እርሱም ወንበር ስቦ ተደላድሎ ተቀመጠ፡፡
ስለኔ የሚያውቃትን ሁሉ አንድ በአንድ ተረተረላቸው፡፡ ቀለማቸውን ቃል መያዣ ወረቀታቸው ላይ አጋድመው ሰሙት፡፡ ወደኔም ገልመጥ እያሉ በግርምት አስጨረሱት፡፡ በግምት ከግማሽ ሰዓት በላይ ወስዶ ሲያበቃ የመረጃውን ምንጭ ጠየቁት " ከራሱ የግል ማስታወሻ የተገኘ ነው" አላቸው፡፡
“እኛም እንየዋ ታዲያ” አሉት። “ጠይቁና ታዩታላችሁ” ብሎ ሊሄድ ተነሳ። ከመሰናበቱ በፊት ግን ሁለት ባለ መቶ ብር ኖት አወጣና ሰጠኝ፡፡ “ከኪስህ ቦርሳ የተገኘ ነው"
ይሔ ሰው በ 2005 የኔን መያዝ ተከትሎ የተካሔደውን የቤት ብርበራ የመራ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት መኮንን ነው፡፡ በዕለቱ የግል ማስታወሻዬን አንድ ጥራዝ ሼልፍ ላይ አግኝቷል፡፡ ከሚፈልግበት ጉዳይ ጋር የሚያገናኘው ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡ ቢሆንም “ታይቶ ለቤተሰብ ይመለሳል” ብሎ ወስዶታል ። ቤተሰቦቼ ግን ተመላልሰው ማግኘት አልቻሉም፡፡ አንዴ “አስቀማጩ የለም” ይባላሉ፡፡ ሌላ ጊዜ “ነገ ኑና ጠይቁ” ይባላሉ። ሌላ ጊዜ ሌላ ቀን ይቀጠራሉ። በመጨረሻ እንደማይመለስ ተነገራቸውና መመላለሳቸውን አቆሙት። መርማሪዎቼም በተደጋጋሚ ጠይቀው እንዳልተፈቀደ ነገሩኝ፡፡
በሰኔ ወር 2010 ከእስር ቤት ተፈታሁ። የግል ማስታወሻዬን አንድ ኮፒ ሰው ጋር አገኘሁት። ይሄ ለንባብ እየቀረበ ያለዉ እሱ ነው። አንብቡት። የአላህን ስራ ታዩበታላችሁ፡፡