ወርቃማ ንግግሮች


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ሰው የለበስክ ሰው እንጂ ልብስ የለበስክ ሰው አትሁን.. ሰውነት የአለም ምርጡ ጌጥህ እሱ ነውና።
አስተያየት እንቀበላለን.. @Golden_SpeechBot
🍂

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


~~

ዲላ ዩኒቨርስቲ «ኒቃብ ለደህንነት ስጋት ነው!» ብሎ ሙስሊም እህቶቻችንን እንዳይማሩ ከልክሏል።
እውነት ለመናገር፤ ኒቃብን እንደ ስጋት ከሚመለከቱ ጽንፈኞች በላይ የሃገር ስጋት የለም።


~

ከአንድ ወጣት ጋር በፍቅር ትወድቃለች። በአንድ ጎጆ ውስጥ ለመኖር ወስነው ከቤተሰብ ጠፍታ ከጎንደር ከእሱ ጋር ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ። እስከዚህች ሰዓት ድረስ ሙስሊም መሆኑን አታውቅም ነበር። ቤተሰቦቹ እንደሚያካብዱና እንደማይቀበሏት ለዛም አክስቱ ጋር እንድታርፍ ሲነግራት ነበር ሙስሊም መሆኑን ያወቀችው!
ኋላ ላይ በየእምነታቸው ሊኖሩ ተስማምተው ጎጆ ተቀለሰ። ከሁለት አመታት በኋላ ግን በአንዲት እህት ( ጎረቤቷ) ሰበብ ከእስልምና ጋር ተዋወቀች! ለእስልምና ተረታችም! በተረታችበት ማግስት ግን ሕይወት መልኳ ሌላ ሆነ!

ክህደት! ህመም! ማጣት ! መገፋት........... የሕይወት መንገዷ ሆነ😥

ለእስልምና የተከፈለ መስዋትነት !......
በፅናት የመቆም ተምሳሌትነት... ብቻ ... ጌታዬ ስንት አይነት ባርያ እንዳለሁ ያየሁባት መንገደኛዬ ነች!


የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት በአክሱም ት/ቤቶች የሒጃብ ክልከላ በመቃወም ነገ በሚደረገው ሰልፍ ሁሉም እንዲገኝ ጥሪ አቅርቧል።

ሸኽ አደም አደም ዓብዱልቃድር ዛሬ በሰጡት መግለጫ መጅልሱ ሒጃብ ከተከለከለበት ከጥቅምት ጀምሮ ጉዳዩ በውይይት እንዲፋታ ለወራት ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ከታች የመጅልሱ መዋቅር ከወረዳው ጀምሮ ጉዳዩ በቀጥታ ወደ ሚመለከታቸው መ/ቤቶችና የስራ ኃላፊዎች በአካል በመቅረብና ለቁጥር የሚታክቱ ደብዳቤዎች በመፃፍ ሁሉም ብዙ ጥረት ማድረጋቸው አስተውቀዋል። ነገር ግን ድካሙ ውጤት ማምጣት አልቻለም። ስለዚህም ለነገ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተናል። በሰልፉም ስለፍትህ የሚያሳስበው የእህቶቹና ልጆቹ መበደል የሚያስጨንቀው ሁሉም በሰልፉ ተገኝቶ ድምጹን እንዲያሰማ ጥሪ አቅርበዋል።

ሒጃቧ ትለብሳለች
ትምህርቷም ትማራለች‼️


╰ ዱንያ ላይ ያልጎደለው ማንም የለም፣
━━━━━━━━━━━━━━━
⎓ሰው ሆኖ ሀሳብ ያልተጫነው አልተፈጠረም፣
⎓ሕይወት ትንሽ ይሁን ትልቅ ከሁሉም ፍጡር የሆነ ነገር ቀንሳለች፣
⎓ሰው ሆኖ የሞላለት አንድም ሰው የለም።

⊖መጥፎ ሰው ማለት ሀሳብ በገባው ሰው ላይ ሌላ ሀሳብ የሚጨምር ነው።
ጭንቀት በወረሰው ላይ ተጨማሪ ጭንቀት የሚለቅ ነው።
⊖ለሰው ችግር መፍትሄ መሆን ባትችሉ እንኳ ችግሩን ከአንድ ወደ ሁለት አታሳድጉ።╯




ባልና ሚስት ይጣሉና ሽማግሌ ይሰበሰባል። ከዚያም ሁለቱም ችግራችሁን ተናገሩ ሲባሉ ...
ባል፦ "እኔ ከስራ ደክሞኝ ስመለስ ማረፍ እፈልጋለሁ። ነገር ግን ልጆችን እያንጫጫች አያሳርፉኝም" አለ
ሽማግሌዎቹም "ሌላስ?" ይሉታል
"እኔ ከስራ ስመለስ ልጅ ያዝ ትለኝና ወጥ ትሰራለች። የልጅ ወተት ታፈላለች። ምናለ ሳልመጣ ጨርሳ ብጠብቀኝ ተቀምጣ እየዋለች" ይላል በንዴት።

ሚስትም በሰዎቹ ፊት "ከዚህ በኃላ በፍፁም አንረብሸውም" ብላ ይቅርታ ስለጠየቀች ሽማግሌዎቹ ትተዋቸው ይሄዳሉ።

በነጋታውም ሚስት ልጆቿን ይዛ እናቷ ቤት ሄደች። ከስራ ሲመጣ ቤቱ ተቆልፏል። ልክ ከፍቶ ሲገባ ቤቱ እጅግ ይቀዘቅዛል። ከሰል ለማቀጣጠል ቢሞክር እምቢ አለው። ልብሱን ደራርቦ ሚስት ሰርታ የነበረውን
ጠራርጎ በላ። ዝምታው ሲጨንቀው ቴሌቪዥን ከፍቶ ለማየት ሞከረ ግን የለመደው የልጆቹ ድምፅ ናፈቀው እና እየከፋው ተኛ።

ጠዋት ሲነሳ ያ የሚጣፍጠው ቁርስና የሚወደው የሚስቱ ፈገግታ የለም። ከፋው። ፊቱን ታጥቦ ወደ ስራው ሄደ። ቁርሱንም ውጪ በላ ግን አላረካውም። ቀኑ እንደከበደው ዋለ። ስልኩን ቢያይም አትደውልለትም። ውሎ ሲመለስ ራቱን ውጭ በልቶ ከጓደኞቹ ጋር ቢያመሽም በመጨረሻ ያ ባዶ ቤት ጠበቀው። ለቅሶ ቤት ይመስል መግባት አስጠላው። ዞር ብሎ ሲያስብ ለካ ያለ ሚስቱ ጎዶሎ ነው።
ለካ ልጆቹ ረባሾቹ ሳይሆኑ አጫዋቾቹና የመንፈስ እርካታው ናቸው።

ከዚያ በኃላ "በእጅ የያዙት ወርቅ ሆናችሁብኝ ጥቅማችሁን ስላልተረዳሁ በጣም በድያችኃለሁ። እባክሽ ይቅር በይኝ ውዷ ሚስቴ!" ብሎ በሽማግሌ ታረቃትና በሰላም ኖሩ።
***
መልዕክቱ፦ ሚስቶች ሸክሞች ሳይሆኑ የቤቱ ተሸካሚዎች፣ ሰራተኞች እና አስተዳዳሪዎች ናቸው። ልጆች የቤቱ ሁከት ፈጣሪዎች ሳይሆኑ ደስታና ሙቀት ፈጣሪዎች ናቸው።
ስለዚህ ደስታ የሚሰጠንን ነገር ከማጣታችን በፊት ቀድመን ለይተን አውቀነው ተገቢውን ቦታ እንስጠው ለማለት ነው።


ሙስሊሟ ተማሪ በአክሱም ትምህርት ቤቶች ሂጃብ ለብሳ እንዳትማር የከለከለው በዋነኛነት የትግራይ ክልል መንግስት  ሲቀጥል የፌዴራሉ አካል ሙሉ ፍላጎት ስለሆነ ብቻና ብቻ ነው። ተጠያቂዎቹም የችግሩም ባለቤቶችም የትግራይና የፌዴራል መንግሥታት ብቻና ብቻ  ናቸው።

ለምን እውነቱን ሸፍኖ ሌላን መውቀስና ማስመሰል አስፈለገ?  ቢፈለግ  እኮ የክልሉ መንግስት በአንድ ቀን በአንድ  መንግስታዊ ትዕዛዝ ብቻ አይደለም ሂጃብን መስጂድ እና የመቀበሪያ ቦታን እንኳን የአክሱም ሙስሊሞች እንዲያገኝ ማድረግ ይችላል።

ታዲያ እውነቱ በዋነኝነት የትግራይ ክልል መንግስት እንዲሁም ሲቀጥል የፌዴራሉ አካል ፍላጎት መሆኑ በግልፅ እየታወቀ  ለምን በጥቂት የአክሱም የሰፈር ፅንፈኞችና ዱርዬዎች ላይ ጥያቄ  ማንሳት አስፈለገን? ለምንስ ዛሬስ እዚያው የማስመሰል ጥያቄዎች ላይ ቆምን?  ለዚያ ነው ማለት ነው ከፌዴራል እስከ ክልሎች ሁሉም መጅሊስ በሚባል ደረጃ መግለጫ ያወጣበትን ሁሉም ሙስሊም የጮኸበትን አንድ ችግር የማይሆን  ተራ ጉዳይን ሰምቶ መልስ የሚሰጥ መንግስታዊ አካል የጠፋው?  መልሳቹ በፍጹም አይደለም የሚል እንደሚሆን ግልፅ ነው ። ታዲያ ከዚህ በላይ መንግስታቶች በሙሉ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ያላቸውን ንቀት እና ሙስሊሙ አሁን ያለበት ተጨባጭ እውነት ለማየት ምን ማስረጃ ይቅረብ?  ስለዚህ የማስመሰል ጥያቄዎችን አቁመን ችግሩን ከስር መሰረቱ ለመንቀል የችግሩን ምክንያት ትቶ ሌላ ቦታ መኳተናችንን ካልቆምን ቀጣዩ ጊዜ እጅግ የከፋ ነው።


Репост из: ትዳር እና ኢስላም 🌷🌹🥀
📣  የመጀመሪያው ፕርግራምተጀመረ 🔈
​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•


📚 ኡስታዝ አቡ ዚክራ ⭐️
      ተ
⭐️
             ጀ
⭐️
                  መ
⭐️
                          ረ
⭐️
ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም!

ሊንኩን ለሌሎችም ሼር አድርጉት‼

 ➘  ➘ ➘ ➘➘ ➘ ➘ ➘  ➘ ➘ ➘➘ ➘
t.me/tdarna_islam?livestream
t.me/tdarna_islam?livestream


Репост из: ትዳር እና ኢስላም 🌷🌹🥀
🤲🤲
📣📣📣😋🥳😄🫣😬
💙ልዩ የዳዕዋህ ፕሮግራም
በትዳርና ኢስላም ቻናል


🎁ዛሬ እሁድ 🎁

የዕለቱ ተጋባዥ ⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️
💙🔤🔤🔠🔤🔤🔤🔤🔤🅰️🔤

💙🅰️🅰️🅰️ 🅰️🅰️🅰️🅰️🅰️


😄ርዕስ በሰአቱ ይነገራል

💙ዛሬ/እሁድ ከምሽቱ 3:00

🔠🔠🔠🔠
🔗@tdarna_islam👈
🔗@tdarna_islam👈
🤲 🤲 🤲


ይህ የሆነው መካ እንደተከፈተች ነው።አብደላህ ኢብን ሰዕድ ኢብን አቢ-ሰርህ ከሰለመ ቡኃላ ቁርዓንን የመመዝገብ ክብር የተሰጠው ሶሃባ የነበረ ሲሆን ለዲኑ ሲል ወደ መዲና ተሰድዶ እያለ በሆነ አጋጣሚ ወደ መካ ይመለስና እዚያው ሲቆይ ከኢስላም ተቀልብሶ ወጥቶ ወደ ቀደመ ጣዖታዊ ኣምልኮቱ ተመልሶ መካ እስክትከፈት ድረስ ኖረ።ነብዩ (ሰ.ዓ.ወ) ድል አድርገው መካን ከፍተው አጠቃላይ ምህረት ሲያደርጉ ጥቂት ሰዎች ይህን እድል ኣገኙም ነበር።ከእነዚያ ሰዎች መካከል አብደላህ ኢብን ሰዕድ ኢብን አቢ-ሰርህ አንዱ ሲሆን መስሊሞች በካዕባ መጋረጃ ላይ ተንጠልጥሎ ቢያገኙትኳ እንዲሰይፉት/እንዲገድሉት ነብዩ (ሰ.ዓ.ወ) ትዕዛዝ አስተላልፈውበት ነበር።

አብደላህ'ም ይህ እንደሚገጥመው ተገንዝቦ ስለነበር በቀጥታ ወደ ኡስማን ኢብን አፋን (ረ.ዓ) በማምራት ከዚህ ጉድ እንዲያወጡት ተማጸናቸው።።አብደላህ እና ኡስማን ኢብን አፋን (ረ.ዓ) የጥቢ ወንድማማቾች ነበሩ።

ኡስማን (ረ.ዓ) አብደላህን ወደ አላህ ነብይ (ሰ.ዓ.ወ) ይዘውት በመምጣት ለደህንነቱ ዋስትና ጠየቁለት።የአላህ ነብይ (ሰ.ዓ.ወ) ግን ለረዢም ሰዓት ዝም ብለው ከቆዩ ቡኃላ በመጨረሻ "ይሁን" አሉ።ይቅርታውን ተቀብለው ዐብደላህ እና ኡስማን (ረ.ዓ) ወጥተው ከሄዱ ቡኃላ የአላህ ነብይ (ሰ.ዓ.ወ) በዙሪያቸው ያሉትን ባልደረቦቻቸውን "ከመካከላችሁ ለረዢም ጊዜ ዝምም ማለቴን ያየ ጮሌ ሰው ተነስቶ አይሰይፈውም/አይገድለውም ነበርን?" አሉ።ባልደረቦቻቸውም በዚህ ጊዜ "የአላህ ነብይ ሆይ! በአይኖችዎ የሆነ ምልክት አያሳዩንም ነበርን?" ሲሏቸው።ነብዩ'ም (ሰ.ዓ.ወ) እንዲህ አሉ ፦ "ነብይ በአይን ጥቅሻ ሰውን አይገድልም።" በሌላ ዘገባ ደግሞ "ለአንድ ነብይ ከዳተኛ አይኖች ሊኖሩት አይገባውም" ማለታቸው ተጠቅሷል።

እዚህ ላይ "ከዳተኛ አይኖች" የተባለው አገላለጽ አንድ ሰው በአንደበቱ የሚናገረው እና በአይኖቹ የሚያሳየው ምልክት ለየቅል ሲሆኑ ነው።ለምሳሌ አንድ ሰው ከአንደበቱ አዎንታዊ ቃላትን እያወጣ በአይኖቹ ግን ከአንደበቱ የማይገጥም ምልክት ሊያሳይ ይችላል።እናም ነብያት እንዲህ እንዲያደርጉ አይፈቀድላቸውም ማለት ነው።

ኢብን ሒሻም (አላህ ይዘንላቸውና) እንደፃፉት "አብደላህ ኢብን-ሰርህ (ረ.ዓ) ከዚያ ቡሃላ ጥሩ ሙስሊም መሆን ችሏል።ዑመር (ረ.ዓ) በኸሊፋነት ዘመናቸው በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ያስቀመጡት ሲሆን ኡስማን'ም (ረ.ዓ) በተመሳሳይ መንግስታቸውን እንዲያገለግል ዕድል ሰጥተውታል።" ብለዋል።ኢብን ከሲር (አላህ ይዘንላቸውና) ደግሞ " አብደላህ ኢብር ሰርህ በቤቱ የፈጅር ሰላትን እየሰገደ (ሱጁድ ላይ ሆኖ) ወይም ሶላቱን አጠናቆ ነው የሞተው" ብለዋል።

ለአለማት ዕዝነት - 794-795


ምድር ገፅታዋን ልትቀይር ተሰናድታለች። ኺላፋውን ለሙስሊሞች ልታስረክብ ተዘጋጅታለች። የሙስሊሞች የከፍታ ዘመን ጅማሮ የኩ#ፍ#ር ኃይላት የሚፍረከረኩባቸው አመታት እነሆ አንድ ብለዋል። በየሀገሩ ምድር መልዕቷን እየሰደደች በምልክቷ እያወራችን ንቁ ትለናለች።

በዚህች ምድር ላይ ሙስሊሞች ዳግም የበላይ ይሆናሉ ኢንሻ አላህ። ቁድስ ነፃ ትወጣለች። ፍትህ ይሰፍናል። ግና ለአጭር ጊዜ ብቻ!!! ከዚያማ ሰማይ ምድሩ የሚናጥበት ፈተና ይቀጥላል። ደጃልና ኢሳ የዕጁጅና መዕጁጅም ይከታተላሉ። ምድር ትሰነጣጠቃለች። ትርገፈገፋለች።

እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ ንቁ

የሆሊውድ ምድር የአሜሪካዋ ሎስአንጀለስ በከባድ የሰደድ እሳት እየነደደች ትገኛለች።  በአራት አቅጣጫ የተነሱትን እነዚህን አውዳሚ  እሳቶች ለመቆጣጥ ከአቅም በላይ ሆኗል። ነዋሪዎቿ ተፈናቅለዋል። ኃብት ንብረታቸውን ትተው ተሰደዋል።


=          Mahi Mahisho


Репост из: ትዳር እና ኢስላም 🌷🌹🥀
😋
📣የዳዕዋህ ፕሮግራም

😓የፕሮግራሙ አቅራቢ፦
1️⃣ኡስታዝ ዐብዱረዛቅ አልባጂ
ርዕስ፦ስለ ተቅዋህ
2️⃣ኡስታዝ አቡ ሒበቲላህ
ርዕስ፦ስለ ሞት
3️⃣ኡስታዝ ኑረዲን አል ዐረቢይ
ርዕስ፦ስለ ሶብር


✈️መድረክ መሪ፦ወንድም አቡ ሑዘይፋህ

0️⃣0️⃣0️⃣የሚተላለፍበት ቻናል፦
📥📥📥📥📥📥
t.me/tdarna_islam

😮ዛሬ እሮብ ከምሽቱ 3:30😓


አረብ ሀገር ላሉ እህቶች ቤተሰብና አፈ ቀላጤ ወንዶች ብራቸውን እየጨረሱባቸው ስለሆነ በተመጣጣኝ ዋጋ የማህበር ቤት እንሰራለን የሚሉ አጭቤዎች መጥተዋል ተጠንቀቁ




እነዚህ ወፎች ጎጃቸው ውስጥ ደርቀው ሞተዋል
ምክንያቱ ደግሞ ምግብ ለማምጣት የወጣችው እናታቸው በአንድ ወንጭፈኛ ተገድላ ነው እነርሱም አቅም ኖሯቸው አይበሩም እሷም ከአንድ ጨካኝ እጅ ላይ ወደቀች.................
ለሌሎች መሞት ምክንያት አትሁን አንድን ሰው ስታጠቃ እና ህልሙን ስታጨናግፍ ከጀርባው የብዙዎችን ህይወት አብረህ እያጨለምክ ነው።

ለማንም ህልም መሞት ምክንያት አትሁን
ቢቻልህ ተስፋ ስጥ። 👌👌👌


ሚስት ባሏን ልትፈትን ፈለገች ፣ ከኔ ተለይቶ ሲያድር ወይም ድንገት ከቤት ሲያጣኝ ምን ይሰማዋል? የሚለውን ለማወቅ አቀደችና ባለቤቷ ከሥራ በሚመለስበት ሰአት ጠብቃ አልጋ ስር ተሸሸገች።

~ በብጣሽ ወረቀት " ቤተሰቦቼ ጋ ሄጃለሁ። አልመጣም አትጠብቀኝ" የሚል ማስታወሻ ፅፋ ኮሞዲኖ ላይ አስቀምጣ አልጋ ስር ገባች።

~ ባል ወደቤት ሲገባ ባለቤቱ የለችም። ወረቀቱን አነበበና እሱም
መልስ ጫር ጫር አድርጎ ወረቀቱን ያገኘበት ቦታ አስቀመጠውና ልብሱን መቀያየር ጀመረ። ልብሱን ቀይሮ እንደጨረሰ ሞባይሉን አነሳና " ሄሎ ፍቅሬ የኔ ማር እንዴት ነሽልኝ ፣ ዛሬ ምርጥ ጊዜ እናሳልፋለን። ባለቤቴ ቤተሰቦቿ ጋ ሄዳለች አትመጣም። …… አንቺ ኮ ማር ነሽ…… እሷን ሳላገባ ባውቅሽ ኖሮ እሷን አላገባም ነበረ … … ከአምስት ደቂቃ በላይ አልቆይም ዝግጁ ሁነሽ ጠብቂኝ መጥቼ ወስድሻለሁ …… ባይ የኔ ጣፋጭ " ብሎ ወሬውን ጨርሶ ተነስቶ ወጣ።

~ ሚስት አልጋ ስር ሆና ቅጥል ብግንግን ብላለች… … ልክ እንደወጣ አፍናው የቆየችውን ለቅሶዋን አፈነዳችው…… ከዚያ ምናባቱ ነው ፅፎ ያስቀመጠው… … አለችና ወረቀቱን አንስታ ስታነበው……
" ቂሎ ባንቺ ቤት መደበቅሽ ነው አይደል…… እግሮችሽን ገና ስገባ ነው ያየሁት…… በይ እራት ገዝቼ መጣሁ እንባሽን ታጥበሽ… ❤❤… እሽቅርቅር ብለሽ ጠብቂኝ " ነበረ የሚለው።         ♥ ፍቅር♥


ከእንቅልፌ የሆነ ነገር ቀሠቀሠኝ :: የመሬት መንቀጥቀጥ መሆኑን አላወቅኩም ነበር።

መሬት ፍጡር ናት ! ትዕግስቷ አላቂ ነው:: ስናበዛው መሰልቸቿ አይቀሬ ነው፡፡ ትክክት ሲላት ..ኧረ ወዲያ .. ብላ አሸቀንጥራ ከላይዋ ላይ ለማራገፍ እየሞከረች ነው። ሚስትህ ብትወሰልትብህ ፣ ጥጋብ ቢጫወተባት ፣ ሁለ ነገሯ ለመኗኗር የማይሆን ሆኖ ብልሽትሽት ብትልብህ ፣ ምን ብትወዳት ፣ የቱንም ያክል ሰፊ ብትሆን እንኳ ከትዳርህ ታርግፋታለህ ! መሬትም ይህንኑ ነው ለማድረግ እየሞከረች ያለችው ::

የሚታየው ፣ የሚሰማው ፣ የሚነገር የሚሰበከው ፣ የሚደነቅ የሚወደሠው ሁሉ ልሽቀትነት ፣ እኩይነት ፣ ብልግና፣ ወራዳነት ፣ ግፍ እና ነውረኝነት ፣ ጋጠወጥነት እና በዳይነት ሲሆን ...

ብልግና ሲወደስ ፣ ግፍ ሲሽሞነምን ፣ አረመኔነት ሲወገን ፣ ነውር ጌጥ ሲሆን ፣ ወራዳነት ሲያስከብር ፣ ጃሂል በሕዝብ ልብ ላይ ሲነግስ ፣ ሽማግሌ ሲረክስ ....

ግድያ ፣ ጭፍጨፋ በሚንበር እና በቤተ መቅደስ ሳይቀር ፅድቅ ሲሆን፣ ዙልም ኢባዳ መስሎ ሲታይ ፣ በአጥንት ቆጠራ የበሰበሰ ህሌና ተሸካሚው ሲበዛ ---

መሬት ይ ስለቻታል። መሬት ትክክት ይላታል። በቃ ደብረናታል 🤔 ወዲያ ከላየ ላይ አራግፍልኝ እያለች ነው!

ደጋግማ ተንገሸገሸች እኮ ! ዝግንን አደረጋትኮ !


በየትኛውም ሁኔታ ሂጃብ ሊከለከል አይገባም"

▣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ለሀሩን ሚዲያ ከገለጹት

- ሀሩን ሚድያ፣ ታህሳስ 25/2017

የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በትግራይ ክልላዊ መንግሥት በአክሱም ከተማ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በሒጃብ ምክንያት እየደረሰባቸው ያለውን የመብት ጥሰት ለምን አላወገዘም ብሎ ሀሩን ሚዲያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለን ጠይቋል።

ዋና ፀሀፊው በምላሻቸው ከኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጥያቄ አልቀረበልንም ነበር ያሉ ሲሆን በትላንትናው ዕለት ግን የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በትግራይ በአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል እንድናወግዝ መጠየቃቸውን ገልፀዋል።

በቀጣይ ሰባቱም የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ አባቶች ውይይት አድርገን የደረስንበትን የምናሳውቅ ይሆናል ሲሉ ለሀሩን ሚድያ ተናግረዋል።

አክለውም የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በትግራይ ክልል ቅርንጫፍ የሌለው በመሆኑ ጉዳዩን ለማጣራት እንደተቸገረ ገልፀው የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዛሬ ያወጣውን መግለጫ አልተመለከትኩትም ብለዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ እንደ ግል አመለካከቴ በየትኛውም ሁኔታ ሂጃብ ሊከለከል አይገባም ያሉ ሲሆን ይህን የሚያደርጉ አካላት አስነዋሪ ተግባር መፈጸማቸውን አክለው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የሰጡትን ምላሽ ከቆይታ በኋላ ወደናንተ ምናደርስ ይሆናል።

© ሀሩን ሚድያ


🌀  ታላቁ ፕርግራማችን ተጀመረ 🔈
​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•


📚 ሀላችሁም ተጋብዛቹኋላ ⭐️
      ተ
⭐️
             ጀ
⭐️
                  መ
⭐️
                          ረ
⭐️
ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም!
ሊንኩን ለሌሎችም ሼር አድርጉት‼

 ➘  ➘ ➘ ➘➘ ➘ ➘ ➘  ➘ ➘ ➘➘ ➘
t.me/merkez_abu_fewzan?livestream
t.me/merkez_abu_fewzan?livestream


ይሄን መፅሃፍ ዱባይ ወይም ኢማራት ላይ ያላችሁ የምትፈልጉ እንብበው።

የምትፈልጉ በኮሜንት መስጫው አውሩኝ።

Показано 20 последних публикаций.