በየትኛውም ሁኔታ ሂጃብ ሊከለከል አይገባም"
▣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ለሀሩን ሚዲያ ከገለጹት
- ሀሩን ሚድያ፣ ታህሳስ 25/2017
የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በትግራይ ክልላዊ መንግሥት በአክሱም ከተማ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በሒጃብ ምክንያት እየደረሰባቸው ያለውን የመብት ጥሰት ለምን አላወገዘም ብሎ ሀሩን ሚዲያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለን ጠይቋል።
ዋና ፀሀፊው በምላሻቸው ከኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጥያቄ አልቀረበልንም ነበር ያሉ ሲሆን በትላንትናው ዕለት ግን የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በትግራይ በአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል እንድናወግዝ መጠየቃቸውን ገልፀዋል።
በቀጣይ ሰባቱም የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ አባቶች ውይይት አድርገን የደረስንበትን የምናሳውቅ ይሆናል ሲሉ ለሀሩን ሚድያ ተናግረዋል።
አክለውም የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በትግራይ ክልል ቅርንጫፍ የሌለው በመሆኑ ጉዳዩን ለማጣራት እንደተቸገረ ገልፀው የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዛሬ ያወጣውን መግለጫ አልተመለከትኩትም ብለዋል።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ እንደ ግል አመለካከቴ በየትኛውም ሁኔታ ሂጃብ ሊከለከል አይገባም ያሉ ሲሆን ይህን የሚያደርጉ አካላት አስነዋሪ ተግባር መፈጸማቸውን አክለው ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የሰጡትን ምላሽ ከቆይታ በኋላ ወደናንተ ምናደርስ ይሆናል።
© ሀሩን ሚድያ