እውቀት ወለድ ክፍል አምስት
✍በ ቅድስት /@Kidymar1
ከፕሮግራም በዋላ ቲጂ ቀድማ ወታ" ጋይስ ሁልሽም ነገ ፈልግሻለው "
ፅናት : አረ ተረጋጊ ሰላም በይን ቅድሚያ
ቲጂ : እሺ ፅኑ love U ነገ እንገናኛለን bye
ቲጂ :ዮዮ አለህ ነገ ፈልጋችዋለሁ ለሚኪም ንገረው
ዮናስ : እንዴ ቲጂ ቾክለሻል
ቲጂ : አዎ ዮዮ ደዉልልኝ ባይ
እየዞረች ላሰበችው አላማ ይጠቅማሉ ያለቻቸውን ጓደኞችዋን ጋበዘች::በግዜ ለመነሳት በግዜ ተኛች ::
ሲነጋ በጠዋት ተነስታ እቅዷን ማከናወን ጀመረች በጠዋቱ ብዙ ስልኮች እየተደወሉ ቀጠሮ እያስያዘች ነው
ዮኒ: ለምን ይመስልሃል ቲጂ የጠራችን?
ሚኪ: ምን አዉቃለሁ ጠንከር ያለ ነገር ይመስላል
አንተ ደሞ እሷ ጠንከር ያለ ነገር ታቃለች?
እንዴት አታቅም?
ሲጀመር የቲማቸው ድምቀት እሷ አደለች?
ሲቀጥል ከፍቅር ጋር ስላንተ ምትሟገት እሷ አደለች?
ይሄን ካልነው ሃሳብ ጋር ምን ያገናኘዋል?
ቁምነገር ብርቋ አደለም ለማለት ብዬ ነው
ቢሆንም የሆነች ቅልብልብ ነገር ስለ ሆነች ሙድ ልትይዝ እንዳይሆን ብዬ ነዋ
እሱን እንግዴ... ሄደን ነው ምናቀው
ሰዓቱ እንደዛው ነው ወይስ....
አዎ ምንም ያለቺኝ የለም ለዚህ በዛው ነው ሚሆነው
-------------
ሁሉም በየፊናው የራሱን ግምት እያስቀመጠ ከሌላው እየተከራከረ ወደ ተጠራበት ይፈሳል ምን ይሆን? ምን ልትል ይሆን? ምን አስባ ይሆን? እየተባባሉ እርስ በእርስ እየጠያየቁ ሁሉም መጡ ትዕግስትም እንደተዘጋጀቺው ሃሳቧን ማብራራት ቀጠለች
እንኳን ደና መጣችሁ ማርፈድን ለሙሽራ ብቻ ያለ ማነው? ብላችሁ ያረፈዳችሁ ደሞ ቆይ እንገናኛለን ዛሬ ግን የተገናኘነው ባንድ ሃሳብ ላይ አዉርተን እንድንወስን ነው::
እና ሃሳቡ ምንድነው ከዛሬ ጀምሮ እስክንመረቅ ድረስ ያለውን excess ወጪ በመቀነስ እንዲሁም በትርፍ ጊዜ ገቢ በማሰባሰብ ጉልበት ሲያስፈልግም በጉልበት በማገዝ አቅማችን እስከቻለ በማድረግ ነገ ለስራ ወይም ለጉብኝት ስንመጣ የምንኮራበት ነገር አስቤ ነው የጠራህዋችሁ እና ሃሳቤን እንዴት አያችሁት?
ይህን ስትናገር ፍቅር በመገረም ታያታለች ወይ ጉድ መድረክ ካገኘ ሁሉም ሰው የመስራት አቅም አለው:: ረባሽ:ፈጣን እና ቅልብልብ የተባለችው እንዲህ ባንዴ ትለወጥ? ይገርማል ትላለች በሃሳቧ
አረ እስኪ አንዴ ለቲጂ ( ሁሉም አንድ ላይ ሞቅ አርገው አጨበጨቡ)
ቲጂ በጣም ደስ የሚል ሃሳብ ነው እርግጠኛ ነኝ ሁሉም የሚስማማበት ሃሳብ ነው እኔም ይህን ዕድል በማግኘቴ ደስ ብሎኛል አመሰግናለሁ አለች አንዷ::
ሌሎችም በየተራ እየተነሱ ሃሳቡን ደግፈው ተናገሩ ወደድዋት አሞገስዋት አደነቋት ደስ አላቸው :: ከውይይቱ በዋላ ፍቅር ጋር ወደ ዶርም ሲመለሱ
ጀግኒት ደስ የሚል ፕሮግራም ነበር
ቲጂ : ወይኔ በስማም ካሰብኩት በላይ ደስ ይል ነበር ::
ፍቅር :ሁሉም እንደተናገሩት ከተገበሩት amazing ነው
ቲጂ : እንደ ጌታ ፍቃድ ይሁን
ስለ ብር ልጆቹ ያላቸው ሃሳብ ግን አይገርምም?
"ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ"ያለው ቤኪ እውነቱን ነው (ሞቅ ያለ ሳቅ )
አረ አንቺ ልጅ ከምነው ሃሳብ እንደሚመጣልሽ እራሱ የኔ ፈጣን
ያው ያንቺ እህት አደለሁ? አለመጎበዝ አልችልም
ፍቅር :ይሁንልሽ እንደዉም አስታወሽኝ ላይብረሪ ሰዓታችን ደርሶአል እኮ እንሂድ
ቲጂ :እሺ ልብስ እንቀይር
ፍቅር :አረ ይሁን ተይው እኔ አልቀይርም
ቲጂ :እሺ ተባብለው ወተው ሄዱ
-----------
በሱ : እንዴት ነሽ? ቲጂ
ቲጂ : ሰላም በሱ ፍቃድ
በሱ :ግን እንደዚህ አሪፍ ሃሳብ ይሆናል ብዬ አልጠበኩም ነበር በጣም አሪፍ ነው
ቲጂ :አረ እኔም አልጠበኩም ከዛ በዋላ ብዙ ስልክ እየተደወለ ነው ጥሩ ሃሳብ እንደሆነ እና ሊሳተፉ እንደሚፈልጉ እየነገሩኝ የነበረው
በሱ :በእዉነት? በጣም አሪፍ ነዋ
ቲጂ : አዎ አሁን ላይብረሪ እየገባሁ ነው ስወጣ ስለ ሃሳቡ በዝርዝር እናወራለን
በሱ : መልካም ነይ
ቲጂ : እሺ
ዮኒ:አንተ የዛሬው ሃሳብ ግን አልገረመህም?
ሚኪ :ቀላል በፊትም የናካት አንተ ነህ እንጂ ልጅቱ ጎብዛለች
ዮኒ:ንቀት ሳይሆን ቁምነገር አታቅም ብዬ ነው
ሚኪ :ዛሬ አሳመነችካ!
ዮኒ: በደንብ!ተገርሞአል ዮናስ ምክንያቱም ለሷ የሰጣት ቦታ ከፍ ብላ ስላገኛት ሲጀመር እንዲው ነው ዛሬ ካገኘኘነው ሰው ጀምሮ እድሜ ልክ እስከምናቀው ሰው ድረስ ከልባችን ቦታ እነሆኝ ብለን እንሰጣለን ከዛ ከፍ ብለው ስናገኝ ሱርፕራይዝ እንሆናለን ከዛ ወርደው ስናገኝ ደሞ እንናደድባቸዋለን ::
ስራውን ቲጂና በሱ በበላይነት እየመሩ ሁሉንም ሞራል እየሰጡ ተጀመረ:: ለሁሉም ኃላፊነት ተከፋፈለ ግማሹ ገቢ አሰባሳቢ ግማሹ ሪሰርች ሰሪ ግማሹ የወረቀት ጉዳዮችን አስፈፃሚ ግማሹን ዕቃ ገዢ ግማሹ ሂሳብ ተቆጣጣሪ አድርገው ሁሉንም ግን በጉልበት አጋዥ እንዲሆኑ አስቀምጡ በየግዜው እየተገናኙ አስፈላጊውን ማሻሻያ ያደርጋሉ:: በዚህ ምደባ ዮናስም ፍቅርም ጥናት መስራቱ ላይ ነው የተመደቡት ዮኒ ፍቅርን የሚያገኝበት ሰፊ በማግኘቱ እጅግ ደስ ብሎታል ቲጂ እና በሱ ተገናኝተው ለመወያየት እንዲመች ሁለቱም ሂሳብ ተቆጣጣሪ ቡድን ውስጥ ገብተዋል::
ከታሰበው በላይ ሆነ::ከክርስቲያን በወጣ ሃሳብ ብዙዎች ተጠቅመዋል የአለም ብርሃን የምድር ጨው ማለት ይሄ ነው:: ተማሪው ካለው ብቻ ሳይሆን ያለውን ያመጣል ማቲዎስ በቅርቡ የማሳትመው ገቢው ለዚህ አላማ ይዋል አለ :: ሌሎችም ቤተሰብ ከሚልክላቸው እንዲሁም እዛው የሚሰሩ ከሚሰሩት እነኤልዱም አገልግሎት ሄደው ካገኙት ለመስጠት አልሳሱም እግዚአብሔር ይመስገን የብዙ ሰዎች ቤት ታደስ የብዙ ሰዎች ስራ ተስተካከለ የብዙዎች ህብረት ጠነከረ አረ
በዚህ ስራ እንደ ዮናስ የተደሰተ ግን አልነበረም ምክንያቱም ሲተኛም ሲነሳም ሲበላም ሲጠጣም ሕልሙ የሆነችው ሴት አብራው ትውላለች ፍቅርም ቢሆን ለዮኒ ያላት ቦታ ጨምሮአል እሱን መስማት እና ማየት ደስ የሚለው ስራዋ ሆኖአል:: እንደውም አንድ ቀን የአንድ አዛውንት ቤት ለማደስ ሲያፈርሱ ዮናስ እጁ ይቆረጣል::ፍቅር ደነገጠች አለቀሰች አበደች ስታለቅስ ያያት ሰው ሞቶ እንጂ እጅ ተቆርጦ አይመስልም በዛ አጋጣሚ እንደወደደችው ታዋቀባት እሷ ግን ግድ አልሰጣትም እሱ ላይ አተኮረች እሱስ ሚፈለገው ያን አደል በደንብ ፍቅሩን አሳያት::ሳታስበው እንዳፈቀረችው ታወቀባት ግድ አልሰጣትም :: አ ጧ እቅዳቸው በመሳካቱ ትግስት እና በሱፍቃድ ደስታችቸው ወደር አቶአል እየተገናኙ ሂሳብም ይሰራሉ እቅድም ያወጣሉ ከዛ ወደ ተግባር በሁለት ወር ተአምር የመሰለ ስራ ነው የተሰራው ከዛ ማጠናቀቅያ አከባቢ ሪፖርት ማዘጋጀት የነሱ ስራ ነበር:: እና እያዘጋጁ ቢሮ ተቀምጠው እየሰሩ እየሳቁ እያለ ድንገት ሰላም ቢሮው አከባቢ ስትደርስ
"አንቺ ጎበዝ ሴት ነሽ አንቺን በማወቄ እድለኛ ነኝ የእዉነት አመሰግናለሁ "
"ኦው በሱዬ ቴንኪው ባንተ እንዲህ መባል እንዴት ደስ እንደሚል " የሚል ድምፅ ትሰማለች እየሳቀች ወደ ኃላ ተመለሰች::
ይቀጥል?
ስለምትሰጡኝ አስተያየት አመሰግናለሁ ::
https://t.me/Gospel_Literaturehttps://t.me/Gospel_Literature