🌹🌹🌹 ሞሮ 🌹🌹🌹
🥀🥀🥀 ክፍል 21 🥀🥀🥀
.......በጥዋት የስልክ ጥሪ ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ ከጥኡም እንቅልፌ የቀሰቀሰኝን ስልክ እየተራገምኩ አይኔን በግድ እያጨናበስኩ ከፍቼ አየሁት ሰምሃል ነበር የደወለችው አንስቼው ሄሎ አልኳት እስካሁን አልተነሳህም በጥዋት ነበር ያልኩህ እኮ ምን ሁነህ ነው ያልተነሳከእ አለችኝ ስልኩን ከጆሮዬ ላይ አንስቼ ሰአቱን አየሁት 11፡45 ይላል። እንዴ ገና 12 ሰአት እንኳን እኮ አልሆነም ምንድነው አልኳት ተነስ ቤተክርስቲያን ደርሰን እንመጣለን አለችኝኛ ስልኩን ዘጋችው። ግማሽ ነቅቼ ግማሽ በእንቅልፍ ልብ ተነስቼ ልብሴን ከለባበስኩ በኃላ ከዶርም ወጥቼ ወደ በግ ተራ ሄድኩ በግ ተራ አከባቢ ስደርስ የአባቴ መኪና እዛው ትናንት ትቻት የሄድኩበት ቦታ ቁጭ ብላለች ደንገጥ አልኩ ትናንት የተፈጠረው ጉድ የአባቴን መኪና ይዤ እንደመጣው እንኳን አስረሳኝ ሮጥ ብዬ ሄጄ አየሁት ቁልፉ መኪናው ውስጥ እንደተንጠለጠለ ነው አዪዪ.... የአንዱ ባለስልጣን መኪና መስሏቸው ፈርተው ነው እንጂማ የኛ መሆኗን ቢያውቁ ጥላዋ ብቻ ነበር ቦታው ላይ እሚገኘው ናዝሬት ከአፍ ውስጥ እሚታኘክ ማስቲካ ባለቤቱ ሳያውቅ እሚሰርቁ ገራሚ ገራሚ አጭቤዎች ያለባት ከተማ ናት። እንዲህ እንዲህ እያስብኩ ሰምሃል ነጠላ ለብሳ ከኃላዬ መጥታ ነካ አደረገዥኝ በዚ ለሊት መንፈስ የነካኝ መስሎኝ በድንጋጤ እንደፌንጣ ዘለልኩ ሰምሃል ነገረስራዬ አስገርሟት ከት ብላ ሳቀች ትናንት እንደዛ ቦጋለች ሆና ዛሬ ስትስቅ ማመን ይከብዳል ማታ ዶርም ኪያር ቦጋለች እያለ ሙድ ሲይዝባት ነበር።
ሰላም ተባብለን ስናበቃ መኪናዋ ውስጥ ገብተን ወደ ዋናው በር አቀናን በር አከባቢ ስንደርስ የት ቤተክርስቲያን ነው ምንሄደው? ብዬ ጠየቅኳት መኪናዋን ለመዘወር እንዲያመቸኝ። ቅድስት ማርያም እንሂድ አለችኝ የመኪናዋን መሪ ወደ ቀኝ ዘወርኩና ወደ አስፓልቱ ወጣን ወደ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን መስመር ይዘን መንገድ ጀመርን ለሊቱ ገና ለቀን ለማስረከብ እየተዘጋጀ ነው በከፊሉ ጨለማ ነው በየመንገዱ ዳር የአስፓልቱን ብርትኳናማ መብራት እየታከኩ የሚታዩት ውሾች ብዙ ናቸው። ሁለታችንም ዝም ተባብለን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ደረስን። መኪናዋን በቤተክርስቲያኑ በስተግራ በኩል አቁመን በዛፍ ወደተከበቡት ፀበል ቤት አከባቢ ሄደን ተቀመጥን የካህናቱ ስርአተ ቅዳሴ በስፒከሩ ጎልቶ ይሰማል በየጥጋጥጉ ነጫጭ ነብሰው የቆሙ ሰዎች አልፎአልፎ ይታያሉ ከኃላ ጥግ ላይ ካሉት የድንጋይ መቀመጫዎች አከባቢ ሄደን ቆመን ማስቀደስ ጀመርን ሰዉ ሲያስቀድስ ሰሙም ቆማ ስትፀልይ እኔ አከባቢውን እቃኛለው የዛፎቹ ቅጠል ርጋፊዎች መሬቱን ሞልተውታል ንፋሱ ከነአቧራው እየጠረገ ከአስፓልቱ መንገድ ላይ ይቸፈችፋቸዋል እንዲህ ተመስጬ እያለ ሰምሃል በሚያምር ቅላፄ ምስለ መንፈስከ! አለች ትንች ከጉልበቷ ሸብረክ ብላ እያጎነበሰች እኔም ፀሎት ላይ መሆኔን ረስቼ ስለነበር ደንገጥ ብዬ ጎንበስ አልኩ ለሰአታት ቅዳሴው ቀጠለ ውስጤ ድክም አለኝ እኔ ብዙ ግዜ ቤተክርስቲያን የመሄድ ልምድ የለኝም ሰምሃል እምታደርጋቸውን ነገሮች እያየው ከሷ እየተከተልኩ አደርጋለው። በስተመጨረሻም ወደ 2፡30 አከባቢ ቅዳሴው አልቆ ምእመኑ ፀበል እየጠጣ ወደየቤቱ መሄድ ጀመረ እኛም ፀበል ጠጥተን ወደቦታችን ተመልሰን ተቀመጥን። ውስጤ አንድ ጥያቄ ይመላለሳል ሰምሃል እንዲ በጥዋት የፈለገችኝ ለምንድነው just ቤተክርስቲያን ደርሶ ለመምጣት ነው ወይስ ሌላ ነገር አለ? ይህ ጥያቄ ከቅድም ጀምሮ ሲከነክነኝ ነበር...
ፀሃፊ - ረምሃይ
🙏 መልካም ንባብ 🙏
✍✍✍ ይቀጥላል✍🏻.........
♥ቶሎ እንዲለቀቅ ላይክ እና ሼር ያድርጉ❤️🙏
:*:*••🆃 🅴 🌸:*:*🌹:*:🌸••🅳 🅰 *
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
Inbox @Teda48 📩✉️📨
For spam @yenehabeshabot
join us🎭 @Habeshapep
🎭 @Habeshapep