╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
.......📓መጅኑኑ_ዲያሪ📓......
✎ ፀሐፊ፦𝕞𝕦𝕜𝕖𝕣𝕖𝕞
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝
┎━─━─━─━─━─━─━─━┒
🌟በ 𝕙𝕒𝕗𝕦 𝕚𝕤𝕝𝕒𝕞𝕚𝕔 𝕡𝕠𝕤𝕥 የተዘጋጀ🌟
┖━─━─━─━─━─━─━─━┚
╔════•| ✿ |•════╗
#ክፍል_ 1⃣7⃣
╚════•| ✿ |•════╝እናቴ የራቀች ለት አባቴም ሲለየኝ፤
ቀን ባሪያ አደረኝ ያኔ እንዳነገሰኝ😞
ሰው ሆኜ መኖር ጀመርኩ ስል እኔን ዝቅ ሊያደርገኝ የሚውተረተር በዛ።ደሜ እየፈሰሰ በውሸት ውንጀላ አንገቴን እንደደፋሁ ከቤት ወጣሁ።መድረሻዬን ሳላውቅ እግሮቼን ከዚያ ቦታ ብቻ ይዘውኝ እንዲሄዱ ዘወርኳቸው።ባዶነት ተሰማኝ።በእያንዳንዱ የእግሮቼ እርምጃዎች ውስጤ እንደ ባዶ ቅል እየጮኸ ወናነቴን ያስተጋባልኛል።ድህነቴን ይዤ የገባሁበት ቤት ውርደትን ከሰውነት ብልዜ ጋር አከናንቦኝ በተሰበሰበ ሰው ፊት አንገቴን አስደፍቶ ከቤት አስወጣኝ።ሳልፈልግ እናቴንና አባቴን አምርሬ ወቀስኳቸው።ምን አለ እዚያ ቤት የገባሁበትን ቀን እግሬን በቆረጠው ብዬ አማረርኩ።ከምንጊዜውም በላይ ጌታዬን አማረርኩ።እጣፈንታዬን አብዝቼ ረገምኩ።መኖሬን ተፀየፍኩት።እግሬም ከትምህርት ቤታችን ጀርባ ወደሚገኘው ጫካ ወሰደኝ።እንደ እብድ እየጮህኩ ማልቀስ ጀመርኩ።ከአላህ ጋር በንግግሮቼ ግብግብ ያዝኩ።የበለዘውን ፊቴን የሚደማውን ጥርስና አፍንጫዬን በእጄ እየጠራረግኩ ለቅሶዬን ማንም በማይጋራኝ የውስጤን ለማንም በማላካፍለው ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ብቻዬን በጨለማ ተቀመጥኩ።ምን ይኑር ምን በማላውቅበት ደን ውስጥ ሞትን ተዳፍሬ በሚያንዘፈዝፈው ብርዱ ተኮራምቼ ጫማዬን ተንተርሼ ጋደም አልኩ።ቦታው በእፅዋት የተከበበ በመሆኑ ንፋሱና ቅዝቃዜው ጥርሴን ያንገጫግጨው ገባ።የገጠመኝ ነገር ትውስ ሲለኝ በጎኔ በተንጋለልኩበት እንባዬ ኮለል እያለ ከፊቴ ላይ ይወርዳል።ጠዋት የጫካው አዕዋፋት ጩኸትና የሚነፍሰው ውርጭ ከእንቅልፌ አነቃኝ።ሰውነቴ በቅዝቃዜው የተነሳ በሰዶ የሰራ ያህል ተሰማኝ።ጎትቼ ከጎልበቴ ላይ ያደረጉትን ቲሸርቴን ወደላይ አውጥቼ የተንተራስኩን ጫማዬን ተጫምቼ ከጫካ ወጣሁ።ገና መነጋጋቱ ነበርና ወዴት እንደምሄድ ግራ ገባኝ።ተማሪዎች እንዳያዩኝ ከትምህርት ቤታችን አካባቢ ራቅ ብዬ ሄድኩ።ቀኑን ሙሉ እህል ውሃ የሚባል ነገር ሳልቀመስ መርዝ እንደቀመሰ ውሻ ከተማውን ስዞር ውዬ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት መለቀቅ ሲጀምሩ ከቀስዋ ጋር የያዝኩት ቀጠሮ ትዝ ሲለኝ ወደ ቦታው መሮጥ ጀመርኩ።
¤°¤°¤°¤°¤°¤°
የክፍሌ በር መንኳኳት ከዲያሪው መንጭቆ አስወጣኝ።
አያቴ ነበረች።እኔም ውጪውን በመስኮቴ አሻግሬ ሳይ ጨላልሞ ነበር።
ክፍሉን ከፍቼ ወጣሁ።
ስትላት ፈቲ ከታች ሆና"እሺ ኡሚ" አለቻት
ብዬ እየተነጫነችኩ ቀልቤ ዲያሪው ጋር እንደሆነ ወረድኩ።ራት ተሰብስበን በልተን ሳያመኝ በመዋሸቴ ደማከሴዬን ተግቼ እንደሌላ ጊዜ አያቴን ሳላጫውታት ወደ ደረጃው ስወጣ
ብዬ ወደ ክፍሌ ገብቼ ካቆምኩበት ቀጠልኩ።
¤°¤°¤°¤°¤°¤°
ከቦታው ላይ ደርሼ ለደቂቃዎች ጠበቅኩ።ግን አልመጣችም።ተስፋ ቆርጬ ልመለስ ስል
ከጀርባ በኩል ተጠራሁ።ዞር ስል ቀስዋ ናት።በልብስ ነበረች።አዩብ እንዳያውቅ ልብስ ለመቀየር እንደሄደችና እንዳረፈደች በመገመት ዞሬ ተጠጋኋት።
ከዚያም ማታ የተፈጠረውን ዘክዝኬ እንደህፃን እያነባሁ ነገርኳት።በመርየም ስራ ተናዳ ስሮቿ ተገታተሩ።አብራኝ አለቀሰች።
ስትለኝ አዕምሮዬ ዳግመኛ መገፋት ካልፈለግክ እግርህ ከሰው ደጅ እንዳይረግጥ ብሎ ሲያስፈራራኝ በፍጥነት 'አይሆንም'አልኳት
ማልቀስ ጀመረች።እኔም ባለችበት ምንም ሳልናገራት የቆሰለ ልቤን ከባዶ ሆዴ ጋር ታቅፌ እንባዬ ቅርር እንዳለ ዞሬ ትቻት ሄድኩኝ።
ይቀጥላል .....❤️🔥
Like 1⃣0⃣0⃣+♥️ካልሆነ ቀጣዩ ክፍል አይለቀቅም🚫
@Hafu_posts🪄