╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
.......📓መጅኑኑ_ዲያሪ📓......
✎ ፀሐፊ፦𝕞𝕦𝕜𝕖𝕣𝕖𝕞
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝
┎━─━─━─━─━─━─━─━┒
🌟በ 𝕙𝕒𝕗𝕦 𝕚𝕤𝕝𝕒𝕞𝕚𝕔 𝕡𝕠𝕤𝕥 የተዘጋጀ🌟
┖━─━─━─━─━─━─━─━┚
╔════•| ✿ |•════╗
#ክፍል_ 1⃣5⃣
╚════•| ✿ |•════╝
ዱንያ እንደዚህ ነች።ማንም ለነገ ህይወቱ ዋስትና የማይዝባት።ከአፍታ በኋላ በሚፈጠረው ነገር ላይ ርዝራዥ ተስፋ እንኳ ማሳደር የማንችልበት ተገለባባጭ አለም ናት።እግሮቼ ከተጣበቁበት አፈር መነሳት ተስኗቸው እንባዎቼ የአይኔን ወሰነ ኬላ አቋርጠው አልፈው ከልብሶቼ ላይ ሲያርፉ ሙቀቱ በመቅፅበት መላ ሰውነቴ ላይ ተሰራጨ።የከሰዓቷ ፀሃይ ከመሃል አናቴ ላይ አርፋ ሰውነቴን በቁሙ ያበስሉት ጀመር።ከድንኳኑ ውስጥ የሚሰማው አንጀት የሚቀላው የዋይታ ድምፅ ከእግር ጥፍሬ እስከ ፀጉሬ እንዲነዝረኝ አደረገኝ።እግሮቼ ወደፊት መሄድን እምቢኝ አሉኝ።ቦርሳዬን አቧራ ከቃመበት መሬት ላይ አንስቼ ወደኋላ አፈገፈግኩ።እምባዬን እያዘራሁ ከትምህርት ቤታችን በታች ወደሚገኝ ጫካ ገባሁ።ከጫካው ውስጥ በአንድ በእድሜ ጠና ብሎ ከተጋደመ ግንድ ላይ ቁጭ ብዬ ሰሚ በሌለበት ብቻዬን እያወራሁ ማልቀስ ጀመርኩ።የውስጤን ለማውጣት ብቻዬን መሆኔ ትልቅ ጥቅም ሰጠኝ።ጡት እንደተከለከለ ህፃን ከልብ ከሚወጣ የሲቃ ድምፅ ጋር እርርርር ብዬ ማልቀስ ገባሁ።በሂደት ጠራራ የነበረው ፀሀይ ያለልምድ በመሃል በጋ ወደ ደመናነት ተቀይሮ እንደኔ የሆዱን ብሶት በፈሳሽ ሊያወራርድ በአስገምጋሚ ድምፁ ማጓራት ሲጀምር ከጫካው ወጥቼ ተመልሼ ከነ አዩብ ቤት ከዚያ የሀዘን ዳስ ከተጣለበት መንደር ከዝናቡ ጋር እየተሽቀዳደምኩ ደረስኩ።ዋይታው በረድ ብሏል።ፈራ ተባ እያልኩ ከድንኳኑ ተጠጓሁ።በሩቁ አይኔን ወርወር ሳደርግ መርየምን ጨምሮ አንዳንድ የትምህርት ቤት ልጆች ላይ አይኔ አረፈ።አንገቴን ደፍቼ ወደ አንዱ ባዶ መቀመጫ ሄጄ ለብቻዬ እንደተቀመጥኩ "ከቀብር እየተመለሱ ነው ወጣቶች ብድግ ብድግ በሉ እጅ አስታጥቡ"ብለው አንድ በእድሜ ጠና ያሉ ሽማግሌ ትዕዛዝ መስጠት ጀመሩ።እኔም ከነሱ ጋር ተቀላቅዬ እጅ ማስታጠብ ጀመርኩ።ህዝቡ ከመጣው ዝናብ ለመሸሽ በሚመስል ሁኔታ ጥድፊያ ላይ ነበር።እኛ ጋር እጃቸውን ተለቃልቀው ገብተው ከውስጥ ከሚገኙ እንስቶችና እናቶች ሰሀን እየተቀበሉ መመገብ ጀመሩ።አዩብ ከሰዎች መሀል በአንድ ወጣት ተደግፎ ገባ።እንኳን እጁን ለመታጠብ በዙሪያው ማን እንኳን እንዳለ ለማየት ፍቃደኛ አልነበረም።በቀጥታ ከጊቢው ውስጥ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤት ይዘውት ገቡ።እኔም በእጄ ጆጉን እንደያዝኩት እንባ እንዳቀረረኝ በአይኔ ሸኘሁት።
የአዛውንቱ ንግግር ከሄድኩበት ጠራኝ።
ነቃ ደንገጥ ለማለት ሞከርኩ።
ብለው የታጠቡበትን እጃቸውን ረገፍ ረገፍ አድርገው መቆምያ ከዘራቸውን ተደግፈው እያነከሱ ገቡ።ማስተናገዳችንን እንደጨረስን እኛን ታጠቡ ብለውን የተዘጋጀውን ምግብ በልተን ከድንኳኑ ተቀመጥን።ሰዉ ከአጠገቡ ካለው ሰው ጋር ስለኢኮኖሚ፣ስለመንግስቱ እንከኖች በእድሜ ገፋ ያሉት ደግሞ ስለእድራቸውና ሀሜት ይዘዋል።እኔም ብቻዬን ስለተቀመጥኩ ዞር ዞር እያልኩ የሁሉንም ወሬ እያማረጥኩ እሰማለሁ።በስተመጨረሻ ሊመሻሽ መሆኑን ሳስተውል ከድንኳኑ ውር ውር እያለች ስታስተናግድ የነበረች የነ አዩብ ቤተሰብ የመሰለችኝን ወጣት ጠርቼ
በድንጋጤ ድምፄን ከፍ አደረግኩት።
ቆጣ አለች።
ድምፄን ቀነስ አድርጌ ነገርኳት።
ባለማመን እንድታረጋግጥልኝ ደግሜ ጠየቅኳት።
ብላ ባለሁበት እየተመናቀረች ጥላኝ ሄደች።እኔም ከሩጫ ባልተናነሰ እርምጃ ወደ መኖሪያ ቤቱ ገባሁ።እንደገባሁ ማሚን ከአልጋዋ ላይ ጥቁር ሻርፕ አድርጋ ሳያት የደስታ እንባ እያነባሁ ከአንገቷ ላይ ጥምጥም አልኩኝ።
ይቀጥላል .....❤️🔥
Like 1⃣0⃣0⃣+♥️ካልሆነ ቀጣዩ ክፍል አይለቀቅም🚫
@Hafu_posts🪄