የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ለመመዘን በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የመስክ ምልከታ ተደረገ፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የተቋሙን የ2ዐ17 በጀት አመት የ6 ወር የዕቅድ አፈፃፀም ያቀረቡ ሲሆን ከሰው ሀብት ልማትና ውጤታማነትን ከማሻሻል ፣ የአገልግሎት አሰጣጡን ምቹ ከማድረግ፣ የህግ ማዕቀፍ ከማሻሻል ፣ ብልሹ አሰራርን ከመከላከል፣ ነፃ የሰዎች እንቅስቃሴን ከማመቻቸትና ከማሻሻል አንፃር፣ የጉዞ ሰነዶች የዜግነትና የመኖሪያ ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥን ከማሻሻል፣ የዲጅታል ቴክኖሎጅን በመጠቀም አገልግሎቱን ከማቀላጠፍ አኳያ፣ የውጭ ዜጐች ቁጥጥርና አገልግሎት ከማሻሻል አንፃር የተሰሩ ስራዎችን እና ወደፊት የዕቅድ አካል አድርጐ ከመስራት አኳያ ተቋሙ የሄደበትን ርቀት አብራርተዋል፡፡
አክለውም አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ቅ/ጽ/ቤት ለመክፈት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የተጠናቀቁ መሆኑን ገልፀው አሁን ላይ የሪፎርም አጀንዳዎችን በመቅረጽና ያሉትን ችግሮች ደግሞ በፍጥነት በመፍታት ከሰው ሀይል፣ ከበጀት፣ ከቴክኖሎጅ አኳያ እያሻሻልን መጠናል ብለዋል፡፡
በመስክ ምልከታ እና በቀረበው ሪፖርት ላይ ከቡድኑ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጐሳ ደምሴ እና አቶ ቢቂላ መዝገቡ ለጥያቄዎች በቂ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም የቡድኑ አባላት ተቋሙ ከዚህ በፊት በርካታ ቅሬታዎች የሚነሱበት ተቋም የነበረ መሆኑን አስታውሰው አሁን ላይ በአጭር ጊዜ ችግሮችን ለመፍታት የተሄደበትን እርቀት አድንቀዋል፡፡ አክለውም በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዬችን የቀሪ ወራት ዕቅድ ላይ በማካተት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ቀንአ ያደታ በበኩላቸው ከአለምአቀፍ ተቋማት ጋር ለመስራት፣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለማስፋት፣ ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር ፣ አገልግሎቱን የተቀላጠፈ ለማድረግ፣ ቴክኖሎጅን ለመጠቀም የተሰራው ስራ የሚያበረታታ መሆኑን ገልፀው ከአገልግሎት አሰጣጥ አኳያ የተጀመሩ የዲጅታል ስራዎች በፍጥነት ወደ ትግበራ እንዲገቡ አሳስበዋል፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
--
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia