"የረመዷን ማስታወሻ!"
ክፍል-➀
አል-ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላሁ ተዓላ) የሚከተለውን ይላሉ፦ “ፆም ግዴታ የሆነው ከሂጅራው ከሁለተኛው አመት በኃላ ነበር። የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘጠኝ (9) ረመዷኖችን ፆመው ነበር ከዚች ዓለም የተለዩት...” [ዛዱል መዓድ (2/30)]
አል-ኢማም አን-ነወዊ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) በተመሳሳይም እንዲህ ይላሉ፦ “የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሕይወት ሳሉ፣ ዘጠኝ (9) ረመዷኖችን ነበር የፆሙት። ይህ ፆም ግዴታ ሆኖ የተደነገገው ከሒጅራው በሁለተኛው ዓመት በወርሃ «ሸዕባን» ላይ ነበር። የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሕይወታቸው ከዚች ዓለም ያለፈው፣ከሒጅራው በ 11ኛው ዓመት በረቢዑል አውል ላይ ነበር...” [አል-መጅሙዕ (6/250)]
አል-ሃፊዝ ኢብኑ ሐጀር (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ ከሂጅራው ሁለተኛው ዓመት «የበድር ጦርነት» የተካሄደበት ጊዜ ነው...” [ተልኺሱል ሀቢር (4/89)]
አል-ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሃመሁላሁ ተዓላ) የሚከተለውን ይላሉ፦ “የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በዚህ በረመዷን ወር በተለያዩ ዒባዳዎች ያሳልፉ ነበር፤ለምሳሌ ከጂብሪል (ዐለይሂ ሰላም) ጋር ሆነው ቁርኣንን ይከልሱ ነበር፤ከሌሎች ወራት በተለየ በዚህ ወር ሶደቃን ይለግሱ ነበር፣አንዲሁም ዚክርን ያበዙ ነበር፣ ኢዕቲካፍም ይገቡ ነበር...” [ሙኽተሰር ዛደል መዓድ (135)]
አል-በይሀቂ (ረሂመሁላህ) በሱነናቸው ላይ ከናፊዕ ተይዞ እንደዘገቡት፡ “ዐብዱሏህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) በረመዷን በቤታቸው ሶላትን ይሰግዱ ነበር...ከዚያ ሰዎች ከመስጂድ ከወጡ በኃላ፣ኢብኑ ዑመር በእቃ ውሃ ይዘው ወደ መስጂድ አን-ነበዊ ይሄዳሉ። ከሄዱበት የንጋት ሶላትን ሳይሰግዱ ከመስጂድ አን-ነበዊ አይወጡም ነበር። [አል-በይሀቂ ሱነኑል ኩብራ (2/494)]
ኢብኑ ረጀብ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ፦ “ዐብዱሏህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ፆማቸውን ከድሆች ጋር እንጂ አያፈጥሩም ነበር። ቤተሰባቸው ከከለከሏቸው ደግሞ ያንን ሌሊት ሳይመገቡ ይውላሉ፤እንዲሁም ኢብኑ ዑመር ምግብን እየተመገቡ፣የቸገረው ችግርተኛ መጥቶ ከጠየቃቸው ከተቀመጡበት ተነስተው ከመዓዱ ያካፍሏቸው ነበር...” [ለጧኢፍ አል-መዓሪፍ (ገፅ: 233)]
📝Authentic & copyright Salafi free PDFs
𝑻𝒓𝒂𝒏𝒔𝒍𝒂𝒕𝒆𝒅 𝒃𝒚: 𝑨𝒃𝒖 𝑯𝒂𝒇𝒔𝒂𝒉
@semirEnglish