የሳዑዲ የጤና ሚኒስቴር በትዊተር እና በፌስቡክ ገፁ በተደጋጋሚ በአማርኛ እና በኦሮምኛ ስለ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሲያስተምር ሳይ እየተደነቅኩ ነው። እኛ ዘንድስ አማራ ክልል በኦሮምኛ፣ ኦሮሚያ ክልል በአማርኛ፣ ወዘተ በተጨማሪነት ለማስተማር ዝግጁ ናቸው? የጤና ሚኒስቴሩስ በተለያዩ ቋንቋዎች ትምህርት ይሰጣል ወይ? በኦሮምኛ፣ በሶማልኛ፣ በትግርኛ፣ በአፋርኛ፣ … ተከታታይ ትምህርት ቢሰጥስ የሚጎረብጣቸው አይኖሩም? ለማንኛውም ሌሎች ያሉበትን ማየት ጥሩ ነው። እራሳችንን ለመታዘብ ይጠቅመናል።