🎖 #የሱልጣን_አልፐርስላን_የኢኽላስ_ውጤት
✍ አሚር ሰይድ
እ.ኤ.አ በ1071 በቱርኮችና በሮማውያን መካከል ወደተደረገው የማላዝጊርት ጦርነት ከማምራቱ በፊት ሱልጣን አልፐርስላን ነጭ የሆነ ንፁህ ጨርቅ በእጁ ይዞ እንዲህ አለ፡- ሸሂድ ለመሆን ልባዊ ምኞቱን ለማሳካት “ይህ ከፈኔ ነው።” ወደ ጦርነት ልዘመት ነዉ ሁለት መልካም እድሎች እንዱን አላጣም። ወይ አሽንፍና በድል እመለሳለሁ፡፡ ካልሆነም ደግሞ ሰማእት ሆኜ ጀነት እገባለሁ፡፡ ከእኔ ጋር መሆን የምትፈልጉም ይህንን ሀሳብ በልባችሁ አስቀምጡ፡፡
በዚህ ጦርነት መካፈል የማትፈልጉ ደግሞ መሄድ ትችላላችሁ፡፡ ዛሬ ምንም ዓይነት ትዕዛዝ የሚስጣችሁ ሱልጣን እዚህ አይገኝም፡፡ እንዲሁም ለመታዘዝ የሚፈልግ ወታደርም መኖር የለበትም፡፡ ዛሬ እኔ ከእናንተ መካከል እንደ አንዱ ስሆን ከእናንተ ጋር የምዘምት ወታደር ነኝ፡፡ ከእኔ ጋር በመሄድ ስትዋጉ የተገደላችሁ ነፍሳችሁን ለአላህ ሰጥታችኋልና ሰማዕታት ትሆናላችሁ፡፡ ሆኖም ግን ሞት ሳያገኛችሁ ድል በማድረግ የተመለሳችሁ ጀግኖች ናችሁ፡፡ እኛን ትታችሁ ወደ ቤታችሁ የምትግቡ ግን መመለሻችሁ ውርደትና የጀሀነም እሳት መሆኑን እወቁ፡፡”
ይህን የመሰለ ኢኽላስ የነበረው ሱልጣን አልፐርስላን ከእርሱ አምስት እጅ የሚበልጥ ስራዊት ይዞ ይጠብቀው የነበረውን ሮማዊ ጀኔራል ድል አደረገው፡፡
ድል ያደረገዉ ጀነሯሉን አንተ በኔ ቦታ ብትሆን ምን ታደርጋለህ??ብሎ ሱልጣን አልፐርስላን ይጠይቀዋል
....አዉሬጄ ለሰዉ መቀጣጫ አድርጌ እገድልህ ነበር ይለዋል ጀነራሉ
....ሱልጣን አልፐርስላን ግን እኔ ግን ቂም ተበቃይ አይደለሁም ብሎ በነፃ ይለቀዋል፡፡ ግን ሱልጣን አልፐርስላን የሰጠዉን ምህረት የእሱ ወገኖች ግን አልሰጡትም አዋርደህናል ብለዉ አይኑን አጥፍተዉ የሞቱ መንስኤ ሆኑበት፡፡
✨ እውነተኛውን መድህን የሚያገኙት ንያቸውን ከልባቸው አስተካክለው የተነሱና ኢኽላሳቸውን ያሳመሩ ብቻ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ኢኽላስ ያላቸው ሰዎች ምንጊዜም ቢሆን ለአደጋ የተጋለጡ ናቸውና፤ ታላቁ የኢስላም አዛዥ ሱልጣን አልፐርስላንም ይህ ዓይነት አደጋ አልቀረለትም ነበር፡፡
በ1072 (እ.ኤ.አ) የማላዝጊርትን ድል ካጣጣመ በኋላ ፊቱን ያዞረው ወደ ማሻሩኒቨር ዘመቻ ነበር፡፡ ከእርሱ ጋር አብረው የተሰለፉ ብዙ ጀግኖች ነበሩ፡፡ አንድ ምሽግ ከበበ፡፡ ግና ዘመቻውን እዳር ማድረስ ሳይችል በአንድ ሙናፊቅ ሸፍጥ በጩቤ ተወጋ፡፡ ገዳዩን የርሱ ወታደሮች ወዲያው ሲገድሉት አልፐርስላን ግን ክፉኛ እንደቆሰለ ለጊዜው ቢተርፍም በ1072 ጥቅምት 25 ቀን በዚሁ አደጋ ሳቢያ ከጌታው ጋር ተገናኘ፡፡ ከመሞቱ በፊት የሚከተሉትን ቃላት ተናግሮ ነበር፡-
✏️✏️ ከጠላት ጋር በምጋጠምበት ጊዜ ልቅና ባለው ጌታዬ አላህ የምጠጋ ስሆን እርዳታውን ይሰጠኝ ዘንድም እለምነዋለሁ፡፡ ትናንት ግን አንድ ተራራ ስወጣ ከሰራዊቴ ብዛት የተነሳ ተራራው ከስሬ ያለ እስኪመስለኝ ድረስ ክፉኛ ኩራት ተሰማኝ። በልቤም ውስጥ እንዲህ የሚል ሀሳብ መጣብኝ፡- 'እኔ የዚህ ዓለም መሪ ነኝ፤ ከእንግዲህ ማን ነው የሚያሸንፈኝ?' በዚህ ሁኔታዬ ምክንያት ኃያሉ አላህ ከባሪያዎቹ መካከል መጥፎ በሆነው ሰው አማካይነት እነሆ! ቅጣቴን ሰጠኝ፡፡ ይህን የመሰለ ሀሳብ በልቤ በማሳደሬ ይምረኝ ዘንድ አላህን እለምነዋለሁ፡፡ እንዲሁም ባለፉት ጊዜያት የስራኋቸውን ስህተቶቼንና ሀጢአቴን ይቅር እንዲለኝ እማፀነዋለሁ፡፡ ከአላህ በስተቀር የሚያመልኩት ጌታ የለም፡፡ ነብዩ ሙሀመድ ﷺየአላህ መልዕክተኛ ናቸው...ብሎ ወደማይቀረዉ አኼራ ሄደ፡፡ አሏህ ኸይር ስራዉንና ሸሂድነቱን ይቀበለዉ፡፡
⚡️⚡️⚡️የኛስ ኢኽላስ መጠኑ ምን ያህል እንደሆነ ፈትሸንዋል???
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group