"ሊቀበለኝ ለማይፈልግ ልቤን አትስጥብኝ" ከፀሎትም አልፎ ልመና ነበር...በቅጡ አላለቀስኩ ይሆን...አጠያየቁን አልቻልኩበትም...እንጃ ግን ዘንድሮም መልሼ ያንኑ ህመም እያስታመምኩ ነው......
ሲጀመር ይታወቀኛል ልቤ ከጥበብ እና ከእውቀት ጋር ይፋለማል ፍልሚያ ቢሉት ፍልሚያ ነው ጥጌን ይዤ ሁለት ሆነው አንድ መነመን ልቤ ሲረታቸው እያየሁ ዝም......
ሞኝነት እና አጉል ተስፋ ያሸመድዱኛል የምፀየፈው ሙቀት ያምረኛል...ለልበ አለት ሙቀት ምን ይበጃል...? ደህና ከጋለ በኋላ ሌላ ልብ ሊያቆስል ካልሆነ በቀር...ጥርሴን የምከፍትባቸው እነዚያ ዜማዎች ሲጎዱኝ ይሰማኛል...ብቻዬንም ፈገግ አለፍ አለፍ እያልኩም ማውራት ይጀማምረኛል...!
ፀሀይቷም ከጎጆዋ ዘልቃ አይን ሁሉ ሲከደን ወገብም ሲያርፍ ውስጤ ያለው ፍርሃት ለሰከንዶች እንዳርፍ አይፈቅድልኝም...ይቀሰቅሰኛል...ይሳለቅብኛል..የሚጠብቅህን አላየህ...ያልተገባህን ወደህ አይደል...?
ምስኪን ብርታቱን እሱ ይበለኝ እንጂ የአሁነኛውስ ቁስል የሚቻል አይመስለኝም...ምን ብሞግትህ ምን ትሰማ...ላንተው ብዬ ባርበደብድህም አትበገርም...ልቦናህ ላይመለስ እንደሄደ ቢገባኝም ነገ ደሞ ብቅ እላለሁ...ብቻዬንስ አልችልም የቀድሞ ቁስሎችህን እና የከዱህን ልቦች እንድታስታውስ ትዝታ ይዤ ነው ምመጣው....!
"እህ" የሚወዱትን መምረጥ ቢቻል ምነኛ እድል በቀናን ነበር...!
ዮሀንስ...🤌🤍 @Jo_21_19
🥀ᴊᴏɪɴ & ꜱʜᴀʀᴇ🥀
🔔@Kurach_Kalat💭
📣@Kurach_Kalat💬